Get Mystery Box with random crypto!

​ጊዜ እና በጊዜ መጓዝ ማለት ምን ማለት ነው በአሁን ዘመን እንቆቅልሽ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ጊዜ | Ethio cyber

​ጊዜ እና በጊዜ መጓዝ ማለት ምን ማለት ነው

በአሁን ዘመን እንቆቅልሽ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ጊዜ ሲሆን በየዘመኑ የሚመጡ ሳይንቲስቶች ብዙ ብለውለታል የሚገረመው ነገረ ጊዜን በተመለከት አሁንም ድረስ ደፍሮ ይሄ ነው ብሎ የሚናገረ ሰው አለመኖሩ ነው ጊዜ አንፃራዊ ነው ከማለት ውጭ።

ጊዜ ወደ ፊት ብቻ ለምን ይሄዳል ? መቼ ጀመር ? መቼስ ያቆማል? ጊዜ ከስበት ጋር ያለው ግንኙነት ምንድነው ከፍጥነት ጋርስ ያለው ግንኙት ምንድነው በብርሃን ፍጥነት ብንጓዝ ጊዜ ይቆማል ወይስ ወደ ዋላ ይቆጥራል? ጊዜ ወደ ዋላ መመልስ ይችላል? በጊዜ ጉዳይ እንዚህ ጥያቄዎች አሁንም ድረስ ሳይንሳዊ ማስረጃ መስጠት ያልተቻለባቸው ጥያቄዎች ናቸው።

በጊዜ መጓዝ ማለት ምን ማለት ነው ?

በጊዜ መጓዝ ማለት አሁን ካለነበት ሰአት ወደፊት ወይም ወደዋላ መሄድ ነው ወደፊት የምንሄደ ከሆነ የወደፊቱን ሂደን ማየት እንችላለን ወደ ትክክለኛው ቦታ በመመለስ የወደፊቱን በተንበይ ወይም መናገር እንችላን ወይም የሆንን ቴክኖሎጂ በማምጣት ሰዎች ሳይጠቀሙት መጠቅም እንችላለን ለዚህም ጥሩ ማሰረጃ የሚሆኑት ስልክ ባልተፈጠረበት ዘመን ስልክ ሲያወሩ የሚታዩ ሰዎች መኖራቸው ነው።

በጊዜ ወደ ዋላ መጓዝ ደግሞ አሁን ካለንበት ሰአት ወደ ዋላ በመሄድ ከዚህ በፊት የነበረውን ክስተት መመልከት መቻል ነው ምን አልባት ከዚህ በፊት የተበላሹብንን ነገረ ወደ ዋላ በመሄድ ማስተካክል እንችል ይሆናል።

በምን አይነት መንገድ ነው በጊዜ መጓዝ የሚቻለው?

በጊዜ ለመጓዝ ትልቅ ማሽን መሰራት አለበት ተብሎ ይታሰባል ይሄ ማሽን በእንግልዘኛው "time machine" ይባላል ሌላኛው አማራጭ ደግሞ ዎርምኦልን መጠቀም ነው የሆነው ሁኖ ሳይንቲስቶች እስከ 2100 ድረስ በጊዜ መጓዝን እውን ለማድረግ እየሰሩ ነው።

በርግጥ ይሄ በጊዜ በጓዝ በአሁኑ ዘመን በእሳቤ ደረጃ ብቻ የሚገኝ ነገረ ሲሆን በውስጡም ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ አብዛኞቹ ባአሁኑ ዘመን የሚገኙ ሊቃዎንትም እብደት ወይም የማይቻል የሚሉት አይነት እሳቤ ነው።

ጥንት ጥንት የሰው ልጆች ኢንተርኔትን እና ሙባይል ስልክን የማይታሰብ ቴክኖሎጂ ብለውት ነበር በአሁኑ ዘመን ግን ተሰርቷል የወደፊቱ የሰው ልጆች ይሄንን "time machine" ሰርተው በጊዜ ይጓዙ ይሆን የብዞች ጥያቄ ነው

ሰለ ጊዜ እና በጊዜ መጓዝን በተመለከተ በዩቲዩብ በሰፊው ተብራርቷል ይመልከቱ
"subscribe"

https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk0kcS_JlWRVD9i9H2xeNTh4