Get Mystery Box with random crypto!

ጃፓናዊው ቢሊየነር ጠፈር ላይ ጎልፍ የመጫወት ዕቅድ እንዳለው ገለጸ 8 ታህሳስ 2021 ማኤዛዋ | Ethio cyber

ጃፓናዊው ቢሊየነር ጠፈር ላይ ጎልፍ የመጫወት ዕቅድ እንዳለው ገለጸ

8 ታህሳስ 2021 ማኤዛዋ ትናት ረቡዕ ወደ ጠፈር ያቀናው ከሩሲያዊው ጠፈርተኛ አሌክሳንድር ሚሱረኪን እና ለዩቲዩብ ቻናሉ ቪዲዮ ከሚቀርጽለት ዮዞ ሂራኖ ጋር ነው።

ጃፓናዊው ቢሊየነር ዩሳኩ ማኤዛዋ ለጉብኝት ወደ ዓለም አቀፉ የሕዋ ምርምር ተቋም ያቀና ሲሆን ይህም በቅርብ ዓመታት ወደ ጠፈር ለጉብኝት የተጓዘ የመጀመሪያው ሰው ያደርገዋል።

ጃፓናዊውን ቢሊነር የያዘችው ሩሲያ ሰራሿ ሮኬት ከካዛኪስታን ተወንጭፋለች። ዩሳኩ ማኤዛዋ በዓለም አቀፉ የሕዋ ተቋም ለ12 ቀናት ይቆያል።

ይህ የቢሊየነሩ ጉዞ ብዙ ከተነገረለት እና እአአ 2023 ላይ ወደ ጨረቃ ለማድረግ ካቀደው በራራ በፊት የተከናወነ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።

Via - Bbc Amharic

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer