Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology )

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotechnollogy — ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology )
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotechnollogy — ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology )
የሰርጥ አድራሻ: @ethiotechnollogy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.74K
የሰርጥ መግለጫ

✔️በቻናላችን✔️
✅ 📲 የAndroid መተግበሪያ
✅ 💻 የPC SoftWare
✅ 📌 አዲስ ለሆኑ የቴክኖሎጂ ምርቶች ልዩ ዘገባ

👉ለአስተያየትና ሌሎች ፕሮግራሞችን ለማግኘት ይቀላቀላሉ
@Ethiotechnology
You tube link
👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCcyO8Yt4swWlW5pzIu8YAPw

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-16 12:16:54
ከጨዋታ ውጭ እንቅስቃሴዎችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመለየት ያቀደው የ2022 የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ

በኳታር በሚካሄደው የ2022ቱ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድሮች ላይ ከጨዋታ ውጭ የሆኑ የተጫዋች እንቅስቃሴዎችን ለመለየት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጥቅም ላይ እንደሚያውል ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳደር አካል ፊፋ አስታዋቀ፡፡

ዳኞች ከጨዋታ ውጭ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ የሚሰጡትን ውሳኔ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የጎለበቱ ካሜራዎችን በመጠቀም የተሻለ ለማድረግ ፊፋ ማቀዱን ዘቨርጅ ዘግቧል፡፡

ቴክኖሎጂው ኳስ ላይ በሚገጠም መጠቆሚያ (ሴንሰር) አማካኝነት እና የስቴዲየሙ ጣራ ላይ በሚገጠሙ እንቅስቃሴ አነፍናፊ አስራ ሁለት ካሜራዎች አማካኝነት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

ካሜራዎቹ ማሽን ለርኒንግን በመጠቀም በተጫዋቾች ሰውነት ላይ የሚገኙ ሃያ ዘጠኝ ነጥቦችን በመከታተል እና ከኳሱ መጠቆሚያዎች የሚገኘውን ዳታ በማቀናጀት ውጤቱን ያሳውቃሉ፡፡

ሥርዓቱ በዚህ መልክ የሚገኘውን ውጤት መቆጣጠሪያ ክፍል ለሚገኙ አካላት ይልካል፡፡ ይህንን መረጃም ከመቆጣጠሪያ ክፍሉ ወደ ዳኛው እንዲደርስ በማድረግ ትክክለኛ ውሳኔ እንዲሰጥ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህ ሂደት በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ እንደሚከናወን መረጃው አትቷል፡፡
2.5K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 16:21:08 ኤሎን መስክ ከ44 ቢሊዮን ዶላር የትዊተር ግዢ ስምምነት እራሱን አገለለ

የዓለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ኤሎን መስክ በርካታ የግዢ ስምምነቶች አልተከበሩም በማለት በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ለመግዛት ደርሶት ከነበረው ስምምነት እራሱን እያገለለ መሆኑ ተገለጸ።

ከሁለት ወራት በፊት የትዊተር ቦርድ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኩን በ44 ቢሊዮን ዶላር ለኤሎን መስክ ለመሸጥ ተስማምቶ ነበር።

መስክ ከትዊተር ግዢ ራሱን ያገለለው የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያው ሐሰተኛ የሆኑ የትዊተር አካውንቶች ምን ያህል እንደሆኑ በቂ መረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ነው ብሏል።

ትዊተር በበኩሉ የግዢ ስምምነቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ሕጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ አማራጮችን እያጤንኩ ነው ብሏል።

“የትዊተር ቦርድ ከመስክ ጋር በተደረሰው ዋጋ እና ደንቦች መሠረት ስምምነቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ጽኑ ፍላጎት አለው” ሲሉ የትዊተር ቦርድ ሰብሳቢ ብሬት ቴይለር በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

በፎርብስ መጽሔት መረጃ መሠረት 273.6 ቢሊዮን የሚገመት የተጣራ ሃብት ያለው ኤሎን መስክ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ነው።

ይህም በዋነኝነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች በሆነው ቴስላ ውስጥ ባለው ድርሻ እና ስፔስ ኤክስ የተባለውን የህዋ በረራ ፕሮግራም ተቋም በኩል በሚያገኘው ገቢ ነው።

መስክ ትዊተርን ለመግዛት ከስምምነት መድረሱ በተገለጸበት ወቅት፤ የማኅበራዊ ትስስር መድረኩን ደንብ እና የአጠቃቀም መመሪያዎችን በማላለት ሰዎች በተሻለ ነጻነት እና አነስተኛ ገደብ ሃሳባቸውን መግለጽ እንዲችሉ ይፈቀዳሉ ግምቶች በስፋት ተነስተው ነበር።

“ነፃ ንግግር የዲሞክራሲ መሠረት ነው፤ ትዊተር ደግሞ ለሰው ልጅ የወደፊት ሕይወት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ክርክር የሚደረግበት የዲጂታል አደባባይ ነው” ሲል ኤሎን መስክ ስምምነቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫ ገልጾ ነበር።

ትዊትር የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ከማኅበራዊ መድረኩ ማገዱን መስክ አጥብቆ ተቃውሞ ነበር።

ሐሰተኛ አካውንቶች

መስክ ግንቦት ወር ላይ ‘ስፓም’ እና ሐሰተኛ የሆኑ አካውንቶችን በተመለከተ መረጃ እስኪገኝ ድረስ የግዢው ስምምነት “ባለበት እንዲቆም” ተደርጓል ብሎ ነበር።

ትዊተር ከአጠቃላይ ተጠቃሚዎቹ የሐተሰኛ አካውንቶች ቁጥር ከ5 በመቶ ያልዘለለ ነው ቢልም፣ መስክ ግን ማረጋገጫ እንዲሰጠው ሲጠይቅ ቆይቷል። መስክ ይህ ቁጥር ከ20 በመቶ ያለነሰ ነው ብሎ ያምናል።

የኤሎን መስክ ጠበቆች ትዊተር ይህን ማረጋገጫ ማቅረብ አልቻለም ይላሉ።

ስፓም አካውንቶች አንድ ተመሳሳይ የሆነ መረጃ ያለ ተቀባዩ ፍቃድ እና እውቅና ለበርካታ ሰዎች የሚልኩ አካውንቶች ሲሆኑ፣ ሐሰተኛ አካውንቶች ደግሞ ትክክለኛ ባለሆነ ማንነት የሚከፈቱ አካውንቶች ናቸው።

ሐሙስ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም. ትዊትር በየቀኑ መሰል 1 ሚሊዮን አካውንቶች አስወግዳለሁ ሲል መግለጫ አውጥቶ ነበር።
2.6K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:58:59 በክሮም ብሮዉዘር ላይ አደገኛ ክፍተት መገኘቱን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ብሮዉዘሩን እንዲያዘምኑ ጉግል አሳሰበ

አዲስ አበባ ፡ ሰኔ 29/2014፡ ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል በክሮም ብሮዉዘሩ (chrome browser) ላይ ተጠቃሚዎችን ለከፍተኛ የሳይበር ጥቃት የሚያጋልጥ ክፍተት መገኘቱን ተከትሎ አስቸኳይ የክፍተት መሙያ አቅርቧል።

ኩባንያዉ ለክፍተቱ መሙያ የክሮም እትም #Chrome_103.0.5060.114 ያቀረበ ሲሆን ይህም ለማይክሮሶፍት ዊንዶዉስ ተጠቃሚዎች የሚሆን መሆኑ ጠቁሟል።

ይህ የደህንነት ማዘመኛ በጉግል ኩባንያ የቀረበለት ክፍተት ከዚህ በፊት ያልተለየ እና የመረጃ መንታፊዎች በተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚያስችላቸዉ መሆኑን ጉግል ይፋ አድርጓል።

ይህ ቀደሞ ያልተለየ የሳይበር ጥቃት አጋላጭ ክፍተት #zero_day_vulnerability በክሮም ብሮዉዘር ላይ ሲደርሰ የፈረንጆቹ 2022 ከገባ ወዲህ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑም ታዉቋል።
በመሆኑም የክሮም ብሮዉዘር ተጠቃሚዎች የክፍተቱን አደገኛነት በመረዳት በአስቸኳይ የመረጃ ማፈላለጊያዉን እንዲያዘምኑ ጉግል መክሯል።
2.9K views19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 19:34:30

3.1K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 18:46:18 ለኮምፒውተር ቫይረስ ጥቃት መጋለጥዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ?

ስራዎችን ስናከናዉን የኮምፒዉተራችን ቀርፋፋ መሆን ፣ የተለያዩ አፕሊኬሽኖች አገልግሎት መቋረጥ እና የኮምፒዉተራችን በድንገት ስራ ማቆም አንዳንድ ጊዜ በቫይረስ የመጠቃታችን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገርግን እነዚህ ምልክቶች ብቻ ሁል ጊዜ በቫይረስ ለመጠቃታችን ማረጋገጫ አይሆኑም፡፡
በመሆኑም የእርስዎ ኮምፒውተር የቫይረስ ጥቃት ሰለባ መሆኑን ለማወቅ ከታች የተዘረዘሩ ምልክቶች በኮምፒዉተርዎ ሊስተዋሉ ይችላሉ፡-

. ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡

. የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም /Slow System/፡ በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን(applications)ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት ካሳየ የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን ሊያመለክት ይችላል።

. ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴ( Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃትዎ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

. ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ፡ ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች /drive/ ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

. ልዩ መልእክቶች፡ በተለያዩ መልእክቶች ወደ እርስዎ የመልእክት መለዋወጫዎች ሲገቡ እና ፋይሎችን በሚከፍቱበት ጊዜ ካልተከፈተ የተፈጠረ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

. መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ፡- ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመድረስ እየሞከሩ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡

. የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ /Random Network Activity/ ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

. የተሳሳቱ የኢ-ሜይል መልእክቶች፡- እርስዎ ለማንም ኢ-ሜይል ባይልኩም ከእርስዎ የኢ-ሜይል አድራሻ ለእርስዎ ኢ-ሜይል መልእክት ከደረስዎ የእርስዎ ስርዓተ ኮምፒውተር ተጥሷል (ወይም የኢ-ሜይል የይለፍ ቃልዎ እንደተሰረቀ የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው)

. የአይፒ አድራሻዎ በበይነ-መረብ ፕሮቶኮል አድራሻ በጥቁር መዝገብ ከተቀመጠ/Blacklisted IP Address/ የእርስዎ የአይፒ አድራሻ በጥቁር መዝገብ መያዙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከደረሰዎት ኮምፒተርዎ በጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት፡፡

. ያልተጠበቀ የፀረ-ቫይረስ አገልግሎት መቆም፡- ብዙ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር /malware/ ፕሮግራሞች ፀረ-ቫይረስ አገልግሎት የማስተጓጎል ወይም ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተልእኮ በመያዝ የተቀየሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ቫይረስ ስርዓትዎ በድንገት የማይሠራ ከሆነ የኮምፒውተር ስርዓቱ ትልቅ ችግር ላይ መውደቁን የሚያሳይ በመሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል፡፡
2.7K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 10:40:15 ዋው ምርጥ website ከ amazon በእጥፍ እቃ የሚቀንስበት እኛም እያስመጣን ነው
ከ Ali express ባለቤትነቱ Alibaba ከሆነው እቃ ማስመጣት ለሚትፈልጉ ከስር ባለው ሊንክ በመግባት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ

Win up to US $200.00 every day #AliExpressbonus #BonusBuddies
You could win the jackpot too!
https://a.aliexpress.com/_mMzZRpu
2.5K viewsedited  07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 16:11:12 ለኮምፒውተር ቫይረስ ጥቃት መጋለጥዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ?

ስራዎችን ስናከናዉን የኮምፒዉተራችን ቀርፋፋ መሆን ፣ የተለያዩ አፕሊኬሽኖች አገልግሎት መቋረጥ እና የኮምፒዉተራችን በድንገት ስራ ማቆም አንዳንድ ጊዜ በቫይረስ የመጠቃታችን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገርግን እነዚህ ምልክቶች ብቻ ሁል ጊዜ በቫይረስ ለመጠቃታችን ማረጋገጫ አይሆኑም፡፡
በመሆኑም የእርስዎ ኮምፒውተር የቫይረስ ጥቃት ሰለባ መሆኑን ለማወቅ ከታች የተዘረዘሩ ምልክቶች በኮምፒዉተርዎ ሊስተዋሉ ይችላሉ፡-

. ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡

. የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም /Slow System/፡ በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን(applications)ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት ካሳየ የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን ሊያመለክት ይችላል።

. ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴ( Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃትዎ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

. ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ፡ ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች /drive/ ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

. ልዩ መልእክቶች፡ በተለያዩ መልእክቶች ወደ እርስዎ የመልእክት መለዋወጫዎች ሲገቡ እና ፋይሎችን በሚከፍቱበት ጊዜ ካልተከፈተ የተፈጠረ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

. መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ፡- ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመድረስ እየሞከሩ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡

. የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ /Random Network Activity/ ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

. የተሳሳቱ የኢ-ሜይል መልእክቶች፡- እርስዎ ለማንም ኢ-ሜይል ባይልኩም ከእርስዎ የኢ-ሜይል አድራሻ ለእርስዎ ኢ-ሜይል መልእክት ከደረስዎ የእርስዎ ስርዓተ ኮምፒውተር ተጥሷል (ወይም የኢ-ሜይል የይለፍ ቃልዎ እንደተሰረቀ የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው)

. የአይፒ አድራሻዎ በበይነ-መረብ ፕሮቶኮል አድራሻ በጥቁር መዝገብ ከተቀመጠ/Blacklisted IP Address/ የእርስዎ የአይፒ አድራሻ በጥቁር መዝገብ መያዙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከደረሰዎት ኮምፒተርዎ በጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት፡፡

. ያልተጠበቀ የፀረ-ቫይረስ አገልግሎት መቆም፡- ብዙ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር /malware/ ፕሮግራሞች ፀረ-ቫይረስ አገልግሎት የማስተጓጎል ወይም ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተልእኮ በመያዝ የተቀየሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ቫይረስ ስርዓትዎ በድንገት የማይሠራ ከሆነ የኮምፒውተር ስርዓቱ ትልቅ ችግር ላይ መውደቁን የሚያሳይ በመሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል፡፡
3.1K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 17:01:47 ነፃ online course መማር ለምትፈልጉ መልካም ዜና ... በዚህ website በነፃ certificate በማግኘት በተለያዪ website ላይ በሰዓት የሚሰሩበት ብዙ ስራዎችን መስራት ትችላላችሁ
ከስር ባለው ሊንክ በመግባት መማር ትችላላችሁ።

https://simpli-web.app.link/e/biAiS7DGXqb
3.0K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 09:31:51

3.2K views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 06:58:49 በጣም በአጭር ጊዜ ጣጣ ሳይበዛ vip መቀበል ትችላላችሁ ።
AOL ይባላላል።
3 ቀን የጋበዛችሁት ሰው መስራት አለበት የሚል ህግ የለውም በአጭር ጊዜ vip ማግኘት ትችላላችሁ።
አሁኑኑ ተመዝግበው ሳይዘገይ የዚህ እድል ተቋዳሽ ይሁኑ።
ለመመዝገብ ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
https://aol518.com/#/pages/register?code=3527389

የሚትቀላቀሉ ልጆች በ @malle65 ላይ contact ያድርጉ በግሩፕ አብረን እንድንሰራ
2.9K views03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ