Get Mystery Box with random crypto!

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በአንድ አካል ሁለት ጭንቅላት ያላቸው ልጆች ተወለዱ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በአንድ አካል ሁለት ጭንቅላት ያላቸው ልጆች ተወለዱ

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንድ አካል ጭንቅላታቸው የተያያዙ መንታ ልጆች አንዲት እናት መገላገሏን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው እለት ከምሽቱ 3፡30 ገደማ የወለደችው እናት እድሜዋ 40 ዓመት ሲሆን የአምስት ልጆች እናት መሆኗ ተገልፆል፡፡

ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱት ህፃናቶቹ እና እናትየው በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል

በሆስፒታሉ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ እንደሆነ እና ወደ አዲስ አበባ ሪፈር እንደሚደረጉ ነገር ግን ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ መሆኑን  በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቨ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ሁለት እና ሦስት መንትያ ልጆች ተወልደው ቢታወቅም ይህ ክስተት  የመጀመሪያ ነው ሲሉ ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በደምቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ሁለት ጭንቅላት ያለላቸው ልጆች መወለዳቸው ይታወሳል፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል