Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ ወጣት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianorthodoxyouth — ኦርቶዶክሳዊ ወጣት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianorthodoxyouth — ኦርቶዶክሳዊ ወጣት
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianorthodoxyouth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.29K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክሳዊ ወጣት አንተ ነህ! አንቺ ነሽ! እኛ ነን! ይህ ለኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች የተዘጋጀ ቤት ነው እዚህ ና Join አድርግ ቤተክርስቲያን ትፈልግሀለች ና አብረን እንሰራለን። የተማርነው እናስተምራለን ያልተማርነው እንማራለን። ቤተክርስቲያንህን ትወዳለህ? አናግረን ምንም አይኑርህ ግድ የለም በምን ላገልግል በለን።
እንወያይ @Eorthodoxbot
@ethiopianorthodoxyouth

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-11-04 22:23:31

የተሳትፎ ጥያቄዎች

ቀድመው ለሚመልሱ 2 መላሾች የ 25 ብር ካርድ ይሸለማሉ!

1. የ 2015 ዓ.ም የዘመነ ጽጌ ማሕሌት ' ተፈጸመ ' መቼ ይውላል?

2.”……እምነት ያለ ሥራ  የሞተ ነው"  ያለው ሐዋርያ ማን ነው?

3.የጌታችን የመድኃኔዓለም ጥንተ በዓለ ስቅለቱ ጥቅምት 27 እንደሚከበር ይታወቃል::  የተለወጠው በዓል ( የዕለተ ስቅለቱ ተውላጥ) መቼ ይከበራል?

4. የአባታችን ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ) ታኅሳስ 24 
ለ) ጥቅምት 24
ሐ) ነሐሴ 24
መ) ኅዳር 24

5.“ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።”. የሚለው ጥቅስ በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ይገኛል?

መልሱን በ @Eorthodoxbot ብቻ ይላኩ!
1.5K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 21:41:29 አንቺን የያዘ ሰው

አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል
በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል
ዘር መከር ባይኖው ጎተራው ባይሞላ
ሁሉምይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ

አዝ--------------//
በረከትሽ ብዙ የደናግል ገንዘብ
የምስኪናን እናት የርሁባን ቀለብ
ለሁሉ መጋቢ ጸ ጋሽ የማይጎድል
ስምሽ ጥዑም ምግብ ከረሀብ
የሚያስጥል/2/

አዝ--------------//
አንቺ ብትመጪ ከምስኪኗ ቤቴ
እንደ መጥምቁ እናት በዛልኝ ሐሴቴ
የአዲስ ኪዳን ቁርባን መንበር ጠረጴዛ
ጽድቅን አሸተትን የሕይወትሽን መዓዛ/2/

አዝ--------------//
ልቤ ተጠራጥሮ ኪዳንሽን ካልከዳ
ልመናም አልወርድም አልይዝም አቁማዳ
ሁሉን እየሞላሽ መመገብ ታውቂያለሽ
ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋና ሀብት አለሽ/2/

አዝ--------------//
የእግዚአብሔር ማረፊያ ኮረባዊት ዋሻ
የህይወት ውሃ ምንጭ የህግ መፍሰሻ
ነበልባል ተዋህዶሽ ሙሴ አንቺን አይቷል
1.5K viewsedited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 19:07:50
'ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
              
                 መዝሙር 34፥11

በሣምንታዊ የዓርብ ጉባዔያችን እንደተለመደው ከምሽት 3፡30 ጀምሮ በቴሌግራም Voice chat ሁላችንም እንገናኝ።

የዕለቱ መርሐግብራት

ዝማሬ
ትምህርት
ከመፃሕፍት
የተሳትፎ ጥያቄዎች

ሌሎች ወንድምና እኅቶችን በመጋበዝ እንድንታደም ይሁን!

@ethiopianorthodoxyouthh
@ethiopianorthodoxyouthh
1.6K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 13:57:35
2.0K views10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 06:02:09 የሣምንታዊ የዓርብ መርሐግብር ጥያቄ መልሶች

1.አባ ፅጌ ድንግል (አባ ብርሃን) አባ ገብረ ማርያም
2.ኒቆላዎስ
3. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ
4.3 ዓመት ከ6 ወር ጌታችንን ይዛ ከቅዱስ ዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር.
5 ማቴ 6፡ 29 ሉቃ 12: 27


የዕለቱ አሸናፊዎች
1. Y...
2. Addis Fekadu

በተሳትፎ አይለዩን

ስልክ በ @EOrthodoxbot ይላኩልን
2.3K viewsedited  03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 21:26:03 https://t.me/ethiopianorthodoxyouthh?videochat=79696a9dd4ce15df82
1.8K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 18:35:56
'ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
              
                 መዝሙር 34፥11

በሣምንታዊ የዓርብ ጉባዔያችን እንደተለመደው ከምሽት 3፡30 ጀምሮ በቴሌግራም Voice chat ሁላችንም እንገናኝ።

የዕለቱ መርሐግብራት

ዝማሬ
ትምህርት
ከመፃሕፍት
የተሳትፎ ጥያቄዎች

ሌሎች ወንድምና እኅቶችን በመጋበዝ እንድንታደም ይሁን!

@ethiopianorthodoxyouthh
@ethiopianorthodoxyouthh
1.8K viewsedited  15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 13:23:09 ኦ ሚካኤል!

ሚካኤል ሆይ፤ የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም አጠራርህ ጋር ለተባበረ ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡ የእግዚብሔር የምክሩ አበጋዝ ሆይ፤ የተቸገሩትን፣ የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ፤ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ በፍጥነት ድረስልኝ፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ ለሰው ልጅ ይቅርታን ለማስገኘት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅበው ለሚማልዱ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ሚካኤል ሆይ፤ በጠላት ተማርከው ለሚጨነቁና ለሚሰቃዩት ዋስ ጠበቃቸው አንተ ነህና፡፡ በእኔ ላይ የሚተበትቡትን የጠላቶቼን የምክር መረብ በጣጥሰህ ጣልልኝ፡፡ ነፍሴንም ሥጋዬንም ለአንተ አደራ ሰጥቻለሁና፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር ክርክር በተደረገ ጊዜ የዘለፋ ቃል ላልተናገረ አንደበትህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡር መልአክ ሆይ፤ ክብርህ ከመላእክት ሁሉ ክብር ከፍ ያለ ነውና፤ በሥነ ሥዕልህ ፊት ቆሜ ልመናዬን በማቀርብበት ጊዜ ሁሉ አይዞህ አለሁልህ በማለት ፈጥነህ ድምጽህን አሰማኝ፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ የፍጥረታት ሁሉ መጠለያ ለሆኑ ክንፎችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡር የሰማውያን ካህናት አለቃ ሆይ፤ ከእለት እኪት አድነን፤ ከጥፋት ሁሉ ሰውረን፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ የመብረቅ መስቀል ምልክት ያለበት በትረ ወርቅ ለጨበጡ እጆችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ሊቀ መላእክት ሆይ፤ በገዳመ ራማ የምትኖር የዋህ ርግብ ወይም ዋልያ አንተ ነህና፤ የሕጻናት እድገት በነጋው በነጋው እንዲጨምር ጽድቅህ በእኔ በባርያህ ላይ እድገቷን ታሳይ፤ ትግለጽ፡፡

ሚካኤል ሆይ፤ ቂም በቀል የሌለበት የርህራሄ እና የየዋህነት መዝገብ ለሆነ ልቡናህ ሰላም እላለሁ፡፡ የሰማያዊያን ኃያላት አለቃ ሚካኤል ሆይ፤ የእስራኤልን ልጆች ባሕሩን ከፍለህ በባሕር መካከል እንዳሳለፍካቸው፤ እኔንም አገልጋይህን ከስውር ወጥመድ ሰውረህ በሰላም አሳልፈኝ፡፡

አማላጃችን ሚካኤል ሆይ፣ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ፣ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህኮ፡፡ የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህኮ፡፡ ይልቁንም የልዑላን ልዑል አንተ ነህና፤ በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታህ በቸርነትህ ድረስልኝ፣ አትራቀኝ፡፡
2.1K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 13:22:19
1.7K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ