Get Mystery Box with random crypto!

መፅሐፍ ቅዱስን የማንበብ ልምድና ክፉ ልማድ ሻምበሉ እንዲህ ሲል አጫወተኝ 'በወጣትነቴ የጦር ሰራ | Ethiopian orthodox mezemur

መፅሐፍ ቅዱስን የማንበብ ልምድና ክፉ ልማድ

ሻምበሉ እንዲህ ሲል አጫወተኝ "በወጣትነቴ የጦር ሰራዊቱን አገለግል ነበር ። ስራዬን ጠንቅቄ የማውቅ አዛዥ ኮማንደሮች የሚወዱኝ 10 አለቃ ነበርኩ ። በሰአቱ ግን እኔም ጓደኞቼም ወጣት ነበርን እና በሚያሳዝን ሁኔታ ሃይለኛ ጠጪ ሆኜ  በመጠጥ ሱስ ተያዝኩ። ራሴን መቆጣጠር በምችልበት ሰአት ጥሩ ሰራተኛ ነኝ ግን ከ6 ሳምንት በላይ መጠጥ ሳልጠጣ መቆየት አልችልም ነበር። ለብዙ ጊዜ ታገሱኝ ግን በመጨረሻ በስካር መንፈስ  አዛዥ ኮማንደሩን ተሳደብኩ እና ያም ጥፋት  "መጠጥ አቁሜ ራሴን ማስተካከል ካልቻልኩ ሌላ የበለጠ  ትልቅ ቅጣት እንደሚጠብቀኝ በማስጠንቀቅ ካለሁበት የስልጣን እርከን ተሽሬ ወታደር አርገው ወደ የጦር ስፍራ አዘዋወሩኝ ። እዛም ሄጄ እራሴን ከዚ አሰቃቂ ችግር ለማራቅ ብሞክርም ከዚ ሱስ ግን መላቀቅ አልቻልኩም ነበር ። በመጨረሻ ራሴን ማስተካከል ስላቃተኝ  ድጋሚ ካጠፋሁ እንደምታሰር ተወስኖብኝ አስቸጋሪ ሰአት ላይ ደረስኩኝ።

አንድ ቀን እዛው የጦር ሰራዊቱ ያረፈበት  ቦታ አካባቢ ተቀምጬ ሳስብ ሳይታሰብ አንድ መነኩሴ ለቤተክርስቲያን ምጽዋት ለመሰብሰብ ወደ እኛ መጡ እና የቻሉትን ሁሉ ሰብስቦ እኔ ጋር ሲደርስ "ምን ሆነህ የተከዝከው  ? " ብሎ ጠየቁኝና መነጋገር ጀመርን እኔም ያለሁበትን ሁኔታ፣  ብሶቴን ሁሉ ነገርኳቸው። መነኩሴውም ካደመጡኝ በኋላ ያለሁበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ተረድተው አዘኑልኝ ። እንዲ ብለውም አጫወቱኝ " አንተ ያሳለፍከው ነገር ሁሉ አንድ ወንድሜም የገጠመው ችግር  ነው ። እናም ከዚ ሱስ ውስጥ እንዲወጣ የረዱት  የንስሃ አባቱ ናቸው ። የንስሃ አባቱ መጽሐፍ ቅዱስ ይሰጡትና ሁሌ የመጠጥ ፍላጎት ሲመጣበት መጽሐፍ ቅዱስ ገልጦ እንዲያነብ ይመክሩታል። ወንድሜም ያንን ተግሳጽ  ተቀብሎ  ሁሌ ፍላጎቱ ሲመጣበት የመጽሐፍ ቅዱስ ምእራፍ ማንበብ ይጀምራል ። በአጭር ጊዜም የአልኮል ሱስ ለቀቀው ። ምንም ዓይነት አልኮል መጠጣት ካቆመ አሁን 15 ዓመት ሆኖታል ። አንተም ለምን እንዲ አታረግም? ያስተውሃል ያንንም ታያለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እኔ ስላለኝ ነገ አመጣልሃለሁ" አሉኝ

እኔም መነኩሴውን ካደመጥኩ በኋላ ስንት መድኃኒት ሞክሬ ብዙ ስታገል ኖሬ ከዚ ሱስ ያላዳነኝ የርስዎ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ይረዳኛል ? " ብዬ መነኩሴውን ጠየኳቸው ። ይህንን ያልኩት ግን በሕይወቴ አንድም ቀን መጽሐፍ ቅዱስ አንብቤ ስለማላቅ ነበረ።መነኩሴው ግን "እንዲ አትበል በእርግጠኝነት ይረዳሃል " ብለውኝ ተለያየን።

በቀጣዩ ቀን መነኩሴው መጽሐፍ ቀሰዱሱን ይዘውልኝ መጡ ። ገልጬው አየሁት የተወሰነ  አንብቤ ስላልገባኝ " የቤተክርስቲያን መጽሐፍት እና ቃላቶችን አንብቤ ስለማላውቅ አንዲቷ ቃል እንኳን ምን ለማለት እንደፈለገ አልገባኝም ልቀበልዎት አልችልም ይቅርታ" አልኳቸው ። እሷቸው ግን " መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉት ቃላት በሙሉ ኃያል ናቸው ምክንያቱም ቃሉ የራሱ የአምላካችን የእግዚአብሔር ቃል ነው ። መጀመርያ ባትረዳቸውም ችግር የለውም ዝም ብለህ ተግተህ አንብብ። አንድ ቅዱስ እንዲ ይላሉ "የእግዚአብሔርን ቃል ባትረዳውም ሰይጣን ግን ተረድቶ በፊትህ መቆም አይቻለውም የወድቃል " ያንተ ሱስ በእርግጠኝነት የሰይጣን ሥራ ነው። አንድ ነገርም ልጨምርልህ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ቅዱስ በተቀመጠበት ቦታ ክፉ መንፈስ እንኳን መቅረብ አይቻለውም ወጥመዱን  እንዳይዘረጋ ያረገዋል ብለው መጽሐፍ ቅዱሱን ሰጡኝ ።

በሰአቱ ለመነኩሴው ስንት ብር እንደሰጠኋቸው ትዝ አይለኝም ብቻ መጽሐፍ ቅዱሱን ተቀብዬ ከሌሎች እቃዎቼ ጋር ትንሿ ሻንጣዬ ውስጥ አስቀምጬው ረሳሁት። ከትንሽ ቀናት በኋላ ለመቋቋም በማልችለው ሁኔታ  ወይን የመጠጣት ፍላጎት አደረብኝና ወደ ቡና ቤት ለመሄድ ተቻኩዬ ሻንጣዬን ስከፍት መነኩሴው የሰጡኝ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ዓይኖቼ አረፉ እና መነኩሴው የነገሩኝ በሙሉ ትዝ አለኝ እና መጽሀፍ ቅዱሱን ገልጬ የመጀመርያውን ምእራፍ ምንም ሳይገባኝ አነበብኩት። መነኩሴው  "ባይገባህም ዝም ብለህ ተግተህ አንብብ" ያሉኝ ትዝ አለኝና ሁለተኛውን ምእራፍ ማነበብ ቀጠልኩ እና በትንሹም መረዳት ቻልኩ ። ለምን ሶስተኛውን ምእራፍ  አልቀጥልም ? ብዬ አሰብኩ ። ሶስተኛውን ምእራፍ እንደጀመርኩ ወደ መኝታ እንድንሄድ የሚያውጀው የጦር ስፍራው ደውል ተደወለና ለመውጣት ሰአቱ ስለረፈደብኝ ሳልወጣ ቀረሁ።

ጠዋት ስነሳ ግን መጠጥ ለመጠጣት ልሄድ ተዘጋጅቼ ነበር ግን "መጽሐፍ ቅዱስ ባነብ ምን ይፈጠር ይሆን ? " የሚል ሃሳብ መጣብኝ እና አነበብኩ...በድጋሚ ሳልወጣ ቀረሁ። በድጋሚ የመጠጣት ፍላጎቱ መጣብኝ አሁንም  አነበብኩ ጥሩ የሆነ ስሜት ተሰማኝ ። ይህም ስሜት አበረታኝ ሁሌ ለመጠጣት ሳስብ መጽሐፍ ቅዱሴን አነሳና የተወሰኑ ምእራፎችን አነባለሁ ። ይህን ሳደርግ ፍላጎቴን ለመቋቋም  ይቀለኛል ። እንዲ እያረኩ 4ቱን ወንጌል አንብቤ ስጨርስ የመጠጥ ፍላጎቴ ሙሉ ለሙሉ ጠፍቶ ነበር ። አሁን ጭራሽ ለአልኮል ጥላቻ ነው የሚሰማኝ። ይኸው 20 ዓመት ሆነኝ ቅንጣት ያክል አልኮል መጠጣት ካቆምኩ ። በሰአቱ ሁሉም ሰው በለውጤ ተገርሞ ነበር ። ከ3 ዓመት በኋላ ወደ አለቅነት ከፍ አልኩኝ በተደጋጋሚ እየተሾምኩ አዛዥ ኮማንደር ድረስ ለመድረስ በቃሁ። መልካም ሴትንም አግብቼ ኑሮ መሰረትኩ አሁን እግዚአብሔር ይመስገን ጥሩ ሕይወት አለን። ሲኖረን ለድሆች  እንመጸውታለን መንፈሳዊ ጉዞም እንሄዳለን። ልጄም መልከመልካም ወጣት እና ፖሊስ ሆኖልኛል። ያኔ ከመጠጥ ሱስ እነደተላቀቅኩ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የፈለገ ስራ ቢበዛብኝ እንኳን አንድ የወንጌል ምእራፍ ሳላነብ አላድርም ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁ ። እና አንዳንዴ ስራዬ ብክን አርጎኝ ወደቤት ስመጣ ለራሴ የገባሁትን ቃል ላለማፍረስ ጋደም ብዬ ሚስቴ ወይም ልጄ እንዲያነቡልኝ አረጋለሁ። ምስጋና ለአምላካችን ይሁን እና ይሄን መጽሐፍ ቅዱስ በብር አስጠርዤው በሄድኩበት ቦታ ሁሉ በኪሴ እይዘዋለሁ። " ብሎ አጫወተኝ ።

The WAY of a PILGRIM
ሽራፊ ታሪኮች ከወርቃማ ገጾች
#ኦርቶዶክሳዊ ወጣት