Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian orthodox mezemur

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianorthodoxmezmu — Ethiopian orthodox mezemur E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianorthodoxmezmu — Ethiopian orthodox mezemur
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianorthodoxmezmu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 171
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወ ወልድ ወ መንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ይህ channel በቤታችን ሆነን መዝሙሮችን እድናጠና
የተዘጋጀ ስለሆነ ለሌሎች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት
ተከታዮች ቻናላችንን በመጋበዝ በቤታቸው መዝሙሮችን
እንዲያተኑ እናግዛቸው።
የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅር ምህረት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-26 15:00:50
48 viewsTéWõMî, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 16:48:49 #ኦ_ሚካኤል

ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል/2/
ስንጠራህ ድረስልን ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል

ዘንዶው ጠላታችን ከፊታችን ቆሟል
ከባህር ሊጥለን አድፍጦ ያደባል
የመላዕክት አለቃ እርዳን በፀሎትህ
ጥበቃህ አይራቀን በቀን በሌሊት/2/

ክርስትና ኑሮ እጅጉን ከብዶናል
የጌታን ውለታ ፍቅሩን ዘንግተናል
አፅናኙ መልዐክ ከፊታችን ቅደም
በመንገድህ ምራን እንድንሆን ሰላም/2/

የጌታ ባለሟል የህዝብ እረኛ
ባህሩን አሻግረን ቅረበን ወደ እኛ
ከጌታህ አማልደን መልዐከ ራማ
የልጆችህን ቃል ድምፃችንን ስማ

በሚያስፈራው ዘመን ሰላም በሌለበት
ባስጨናቂው ጊዜ ፍቅር በጠፋበት
የፍቅርን ወንጌል ቃሉንም ስበከን
ሚካኤል ተራዳን ድረስም አፅናናን

ዘ/ዲ ሱራፌል ስዩም
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
72 viewsTéWõMî, 13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 16:48:49 ​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ።

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
53 viewsTéWõMî, 13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 16:48:48
ያለውና የነበረው የሚመጣው

አንዲት በአረብ ሀገር የእስልምና እምነት ተከታይ የነበረች ሴት ወደ አንድ የግብፅ ካህን ጋር በመሄድ አባቴ አጥምቁኝ አለቻቸው።

ካህኑም አንቺ የእስልምና እምነት ተከታይ ነሽ
እናም አስቀድመሽ ልትማሪ ልታምኚ ይገባል አሏት
እርሷም እኔ ክርስቲያን ነኝ ሁሉን ነገር ራሱ ክርስቶስ አስተምሮኛል አንድታጠምቁኝ እፈልጋለሁ አለቻቸው።

ካህኑም በመገረም ለመሆኑ በማን ስም ነው የምትጠመቂው አሏት?

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማናቸው?

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ልዩ ሦስትነት ያላቸው አንድ አምላክ ነው።
"አብ አምላክ ነው። ወልድ አምላክ ነው። መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው። ግን ሦስት አምላክ አይባልም አንድ ልዩ አምላክ ነው። አለች

"ይህን እንዴት አወቅሽ?

በራዕይ ዩሐንስ ላይ፦
“ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” ራእይ 1፥8

ይህ ስለ ጊዜ የተነገረ ነው፦

ትላንትም ጊዜ ነው። ዛሬም ጊዜ ነው። ነገም ጊዜ ነው። ነገር ግን ትላንት ዛሬ አይደለም። ዛሬም ትላንት ወይንም ነገ አይደለም። ነገም ትላንት ወይንም ዛሬ አይደለም። ሦስቱም ግን ጊዜ ናቸው። ነገር ግን በአንድ ላይ የተጨፈለቁ አይደሉም። ትላንት ለብቻ ነው፣ ዛሬ ለብቻው ነው።፣ነገም ለብቻው ነው።

እንዲሁም፦

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው።
ነገር ግን አብ፥ ወልድ አይደለም፣ መንፈስ ቅዱስም አብ አይደለም። ሦስቱም በህልውና አንድ አምላክ ሆነው ይኖራሉ እንጂ።

እንዲህ አድርጎ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮኛል አለቻቸው።

ካህኑም እጅግ በመደነቅ ከልብ ለሚፈልጉት ለልበ ንፁሐን ምሥጢርን የሚገለጥ ክርስቶስን እያደነቁ አጠመቋት።
47 viewsTéWõMî, 13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 16:04:58
በሰው ፊት አንድ ሰው ቢቆምልህ ማንኛውም ነገር ታደርጋለህ በእጅጉ በማመስገን ትናገራለ። ካህን ግን በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልሃል። ውለታውን ግን አታስብም። እርሱ ለአንተ ይፀልያል በጥምቀት የሚገኘውን መንፈሳዊ ስጦታ እንድታገኝ በማድረግ ያገለግልሃል። ሆኖም እርሱ የአንተ መነጋገሪያ ርዕስ ከመሆን ውጪ ምንም ያገኘው ነገር የለም። እናም የአንተን አቁሳይ ንግግሮች ታግሦ ይኖራል።

ክርስቶስን የሚያፈቅር ቄሱን ምንም ይሁን ምን ያፈቅረዋል። ምክንያቱም አስፈሪውን ምሥጢራት ያገኘው በእርሱ በኩል ነውና። ዘላለማዊ ልደት የተወለድከው በእርሱ በኩል ነው።
ሁሉም ነገር የተከናወነው በእነርሱ እጆች ነው። ስለዚህም ስለ ሥራቸው በፍቅር ከመጠን ይልቅ አክብሯቸው። ክርስቶስን የምታፈቅሩት ከሆነ "ስለ ሥራቸው ስትሉ ከእነርሱ ጋር በሰላም ኹኑ።" /1ተሰ 5፤12/

[የዕለቱ መና - ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ።]
73 viewsTéWõMî, 13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 15:59:33 እስካሁን ዘጠና ዘጠኝ ሰዎች ገድያለሁ አንተ መቶኛው ትሆናለህ!

አንድ ካህን በሞቃታማ ዕለት ብቻቸውን ጭር ባለ ጎዳና ላይ ሲሔዱ አንድ መሣሪያ ያነገተ የሚያስፈራ ሰው ድንገት ከዛፎች መሃል ዘልሎ ወጣና ከፊታቸው ቆመ።

ቄሱ ላይ አፍጥጦ "እስካሁን ዘጠና ዘጠኝ ሰዎች ገድያለሁ አንተ መቶኛው ትሆናለህ!" አላቸው።

ካህኑም መልሰው "ለመሞት ዝግጁ ነኝ ፣ ነገር ግን በጣም ስለጠማኝ ትንሽ ውኃ ሥጠኝና ትገድለኛለህ" አሉት። ነፍሰ ገዳዩ ለአፍታ ግራ ከተጋባ በኋላ በቄሱ ላይ መሣሪያውን እንደደገነ በዛፎቹ መካከል ካለው ምሽጉ ውስጥ በኩባያ ውኃ አምጥቶ እንዲጠጡ ሠጣቸው።

ካህኑ ውኃውን እየጠጡ እያለ ግን ሽፍታው ድንገት በልብ ድካም ሕይወቱ አለፈች።

የዚህን ሰው ነፍስ ወደ ገነት ለመውሰድ መላእክት በመጡ ጊዜ አጋንንት ነፍሱ የእኛ ፈንታ ናት ብለው ተከራከሯቸው። "ይህ ሰው ዘጠና ዘጠኝ ሰዎችን የገደለ ሲሆን እጅግ ብዙ ትንንሽ ኃጢአቶችንም ፈጽሟል። ነፍሱ የሚገባው ለእኛ ነው" አሉ።

መላእክቱ ግን እንዲህ ብለው ለአጋንንቱ መለሱላቸው "ያደረገው እንዳለ ሆኖ ይህ ሰው ከሠራቸው ኃጢአቶች የበለጠ የሚመዝኑ በክርስቶስ ወንጌል የታዘዙ ሁለት ታላላቅ ተግባራትን ፈጽሟል። የመጀመሪያው ዘጠና ዘጠኝ ሰው እንደገደለ ለካህን መናዘዙ ሲሆን ሁለተኛው ለተጠማ ውኃ ማጠጣቱ ነው!" አሏቸው።

የትኛውንም ያህል ቢደጋገም እንኳን ከእግዚአብሔር ምሕረት ሊበልጥ የሚችል ኃጢአት የለም!

ቅዱስ ኒኮላይ ቬሊሚሮቪች (St. Nicholai Velimirovich)
ምንጭ: Anicent Christian Wisdom

ትርጉም: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
54 viewsTéWõMî, 12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 22:34:37 አቤቱ ግሩም ምክርህን ትመክረኝ ዘንድ ዳግመኛ አይኖቼን ወደ አንተ እነሳለሁ በእንባም አለምንሃለሁ ሌሎች መሆን ያለባቸውን ሳውቅ እና ስናገር እኔ መሆን ያለብኝ እንደየጠፋኝ ለአንተ 'የታመኑልህ ወዳጆችህን' መምሰልን ፍፁም ደስ የሚያሰኝህን የትዕዛዝህን መንገድ መከተልን መሻትን ከልቤ አትሰውር። እንደ አለም ሀሳብ የሆነ ሕይወትን አትስጠኝ ። ይልቁኑም በአደባባዮችህ መጣልን አትንፈገኝ።

ኃጥዕ ወልድከ ተክለፃድቅ
50 viewsTéWõMî, 19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 22:30:54 ​​#የቀጠለ

ሐዋርያት የጾሙት ጾም የኢየሱስ ክርሰቶስን ፈለግ መከተላቸውን የሚያሳይነው፡፡ መምህራቸውና አምላካቸው ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሌላ ሥራ ሳይጀምር ወደ ገዳመ ቆርንቶስ ገብቶ እንደጾመ ሁሉ እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቁ በኋላ አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸውና ወደየሀገረ ስብከቶቻቸው ከመበተናቸው በፊት እግዚአብሔር መንገዳቸውን የተቃና ሥራቸውንም የተሳካ ያደርግላቸው ዘንድ ጾመዋል፡፡

ይህን ጾም ሐዋርያት ጾመው በረከት ያገኙበት ከመሆኑ ባሻገር ጌታችን ጾሞ ጹሙ እንዳላቸው እነርሱም ደግሞ ተከታይዎቻቸውን ያንኑ መልዕክት የደገሙበት ነው፡፡ በክርስቶስ ደም መሰረት ላይ እና በሐዋርያት ትምህርትና ትውፊት ላይ የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያናችንም ይህንን ጾም በዐዋጅ እንድንጾመው ሥርዓት ሠርታልናለች፡፡

ጾሙ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት እንደመሆኑ መጠን ከጌታ ትንሣኤ ከሃምሳኛው ቀን በኋላ ማለትም ከጰራቅሊጦስ ዕሁድ ማግስት ሰኞ ጀምሮ በቅዱስ ጳውሎስና በቅዱስ ጴጥርስ በዓለ እረፍት መታሰቢያ በሆነው ሐምሌ አምስት ቀን ፍጻሜውን ያገኛል፡፡ የቀናቱ ብዛትም በዐቢይ ጾም መባቻ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ጾሙን የበረከት፣ የንስሐ ፣ ደዌን ማራቂያ፣ ዲያቢሎስን ድል መንሻ ያድርግልን!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
45 viewsTéWõMî, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 22:30:54 ​​ጾመ ሐዋርያት/የሰኔ ጾም

ጾመ ሐዋርያት ሐዋርያት በጽራሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ወደ አገልግሎት ከመግባታቸውና ወደ ሀገረ ስብከታቸው ከመበተናቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ የጾሙበትም ምክንያት በማርቆስ ፪፥፳ እና በማቴወስ ፱፥፲፬ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ይኸውም የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው እኛና ፈሪሳዊያን ብዙ ጊዜ የምንጾመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጾሙት ስለ ምንድን ነው? አሉት፡፡ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡-ሚዜወች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ያን ጊዜ ይጾማሉ፡፡››ብሎ እንደመለሰላቸው፡፡

በዚህ ምሳሌያዊ አነጋገር ሙሽራ የተባለው ካባ በመደረብ ፈንታ ዕርቃኑን ሆኖ በአክሊል ፈንታ የእሾህ አክሊል ደፍቶ በሚዜወቹ ፈንታ በጠላት ተከቦ በመዝሙርና በደስታ ፈንታ በልቅሶና በዋይታ ታጂቦ በክብር ዙፋን መቀመጥ ፈንታ በመስቀል ተሰቅሎ በጭንካር ተወጥሮ በቀራንይዎ አደባባይ ስለ እኛ የተሞሸረው/የተሰቀለው/ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሚዜዎቹ የተባሉት ደግሞ ምንም እንኳን በሰርጉ እለት ከአንዱ በቀር (ከወንጌላዊ ዮሐንስ/ ከጎኑ ባይገኙም ኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው በሕይወትም በሞትም ሙሽራውን/ኢየሱስ ክርስቶስን/ የመሰሉ ሐዋርያት ናቸው፡፡

ይወሰዳል መባሉም እርገቱን ለመናገር ሲሆን ከዚያ በኋላ ይጾማሉ መባላቸው ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ሲያርግ መንፈስ ቅዱስ ይመጣልና፡፡ በዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ጉዳይ ጾም በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ በሐዲስ ኪዳንም የቀጠለ ሥርዓት መሆኑን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረ ስለመሆኑ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት እና አይሁድ ብዙ ጊዜ ይጾሙ እንደነበረ ተጽፏል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት"እናንተና አይሀድ የጾማችሁት ባለማወቅ ወይም በስህተት ስለሆነ ደቀ መዛሙርቴ አይጾሙም" አላለም፡፡ ነገር ግን ለጊዜው ከእኔ ጋር ናቸው ደስ ሊላቸው ይገባል፡፡ ከሄድኩ በኋላ ግን ይጾማሉ ብሏል፡፡ ይኸውም ጾም ከአዳም ጀምሮ እስከ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና ደቀ መዛሙርቱ ከዚያም በክርስቶስ ታድሶና ተቀድሶ ለደቀ መዛሙርቱ የተሰጠ ከዚያም ለእኛ ለተከታይዮቻቸው የተላለፈ ሥርዓት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ለጊዜው ሐዋርያት ሊጾሙበት ያልቻሉበት ምክንት ሊቃውንት ሲያብራሩ ፡-አንደኛ ጾም ሐዘን ነውና ሐዘኑም ኃላፊነትን ከመሸከም ጋር ተያያዥነት ያለው ነውና፡፡ ምክናያቱም መጾም አላማው ንስሐ እንደመሆኑ እንደ ቅዱስ ዳዊት ለግል ኃጢያት አሊያም እንደነነዌ ሰዎች ስለሀገር ጥፋት የሚያለቅሱበት የሚያዝኑበት ሁኔታ አለው፡፡ ክርስቶስ ደግሞ በስጋው ወራት ከአምላክነቱና ከሁሉ አባትነቱ ባሻገር ለሐዋርይት እንደ ሥጋ አባትም ወንድምም በመሆን የእነርሱን ኃላፊነት ተሸክሞላቸዋልና እርሱ በአካለ ሥጋ በአጠገባቸው እስካለ ድረስ ማዘን አልተገባቸውም፡፡

በሁለተኛነት ደግሞ ጾም ኃላፊነት ነው፡፡ኃላፊነቱን ለመሸከም ደግሞ ኃይል የሚሆናቸው መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋቸው ነበርና መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ እንዲጾሙ ጊዜ ሰጣቸው፡፡ ሦስተኛው ምክነያት አይሁድ ይጾሙት የነበረው በብሉይ ኪዳን ስርዓት ውስጥ ሆነው ነበር፡፡ ሐዋርያት ደግሞ የሐዲስ ኪዳን ልጆች ስለሆኑ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው አሊያም አዲሱ ሰው በተባለው በክርስቶስ ደም ተጽናንተውና ሥጋውንና ደሙን ተቀብለው አዲሱን ሰው ለብሰው በአዲስ መንፈስና ኃይል በአዲስ ስርዓት መጾም ስለነበረባቸው በጊዜው አልጾሙም ነበር፡፡/ማቴ ፱፥፲፮-፲፯/

ይቀጥላል
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
40 viewsTéWõMî, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 21:09:30
በዓለ #ጰራቅሊጦስ_ሀብተ_መንፈስ_ ቅዱስ ለሐዋርያት የተሰጠበት፤ ብዙ ሺሕ ምእመናን #የሥላሴን ልጅነት ያገኙበት ዕለት በመኾኑ ‹የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓሉ ከዘጠኙ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው
#እንኳን_ለበዓለ_ጰራቅሊጦስ_በሰላም_አደረሳችሁ

#መልካም_ዕለተ_ሰንበት

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ ለማግኘት //

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
44 viewsTéWõMî, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ