Get Mystery Box with random crypto!

​​#የቀጠለ ሐዋርያት የጾሙት ጾም የኢየሱስ ክርሰቶስን ፈለግ መከተላቸውን የሚያሳይነው፡፡ መምህራ | Ethiopian orthodox mezemur

​​#የቀጠለ

ሐዋርያት የጾሙት ጾም የኢየሱስ ክርሰቶስን ፈለግ መከተላቸውን የሚያሳይነው፡፡ መምህራቸውና አምላካቸው ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሌላ ሥራ ሳይጀምር ወደ ገዳመ ቆርንቶስ ገብቶ እንደጾመ ሁሉ እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቁ በኋላ አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸውና ወደየሀገረ ስብከቶቻቸው ከመበተናቸው በፊት እግዚአብሔር መንገዳቸውን የተቃና ሥራቸውንም የተሳካ ያደርግላቸው ዘንድ ጾመዋል፡፡

ይህን ጾም ሐዋርያት ጾመው በረከት ያገኙበት ከመሆኑ ባሻገር ጌታችን ጾሞ ጹሙ እንዳላቸው እነርሱም ደግሞ ተከታይዎቻቸውን ያንኑ መልዕክት የደገሙበት ነው፡፡ በክርስቶስ ደም መሰረት ላይ እና በሐዋርያት ትምህርትና ትውፊት ላይ የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያናችንም ይህንን ጾም በዐዋጅ እንድንጾመው ሥርዓት ሠርታልናለች፡፡

ጾሙ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት እንደመሆኑ መጠን ከጌታ ትንሣኤ ከሃምሳኛው ቀን በኋላ ማለትም ከጰራቅሊጦስ ዕሁድ ማግስት ሰኞ ጀምሮ በቅዱስ ጳውሎስና በቅዱስ ጴጥርስ በዓለ እረፍት መታሰቢያ በሆነው ሐምሌ አምስት ቀን ፍጻሜውን ያገኛል፡፡ የቀናቱ ብዛትም በዐቢይ ጾም መባቻ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ጾሙን የበረከት፣ የንስሐ ፣ ደዌን ማራቂያ፣ ዲያቢሎስን ድል መንሻ ያድርግልን!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur