Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Artificial Intelligence Institute

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianaii — Ethiopian Artificial Intelligence Institute E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianaii — Ethiopian Artificial Intelligence Institute
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianaii
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

This is the official Telegram channel of FDRE Artificial Intelligence Institute. The institute is established under the regulation No. 463/2020 with defined powers and responsibilities.

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-11 11:28:46
የባሕር ዳርቻ የማዕበል ሞገዶችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመለየት እንቅስቃሴ በጃፓን

ከአውሮፓውያኑ ሐምሌ ወር መጀመሪያ አንስቶ የሚኖረውን ከፍተኛ ሙቀት ተከትሎ የጃፓን ፓስፊክ ውቅያኖስ የባሕር ዳርቻዎች ሰዎች ይበዙባቸዋል፡፡

የሰው ብዛት እና በባሕር ዳርቻዎቹ የሚከሰተው ሞገድ ተዳምረው ስልሳ በመቶ ለሚሆኑ የመስጠም አደጋዎች መነሻ የመሆኑ ጉዳይ የአካባቢውን ባለሥልጣናት መፍትሔ እንዲሹ አስገድዷል፡፡

ባለሥልጣናቱ ዩጋሃማ ተብሎ በሚጠራው በዚህ የባሕር ዳርቻ የሚከሰቱ የሞት አደጋዎችን ለመከላከል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ወድ ሥራ ማስገባታቸውን ዘጋርዲያን አስነብቧል፡፡

በባሕር ዳርቻዎቹ ዙሪያ በሚገኙ ማማዎች ላይ የተተከሉ ካሜራዎች በሚያደርጉት ቅኝት የመሰል ሞገዶችን ክስተተና በዙሪያቸው ሰዎች መኖር አለመኖራቸውን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱ አማካኝነት ይለያሉ፡፡ በአደጋ ቀጠና ውስጥ ሰዎች ካሉም ሥርዓቱ በአካባበቢው ለሚገኙ የሕይወት አድን ሰራተኞች በስማርት ሰዓታቸው ላይ የማስጠንቀቂያ መልዕክት እንደሚልክ ታውቋል፡፡

በተጨማሪም ይህ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት በባሕር ዳርቻዎቹ የሱናሚ አደጋዎች ቢከሰቱ አካባቢው ላይ ያሉ ሰዎችን አሁናዊ ሁኔታ ለማወቅ እንደሚያገለግልም ተገልጿል፡፡

የጃፓን የሕይወት አድን ማሕበር በቶክዮ ከሚገኘው ቹዎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱን ለማበልፀግ የሚረዱ የባሕር ዳርቻ ሞገዶችን የተመለከተ ዳታ ለስድስት ወራት ሲያሰባስቡ መቆየታቸው ተመላክቷል፡፡
184 views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 08:48:47
የቆዳ በሽታ ምርመራ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያዎች

ሀገራችንን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጫና ከሚፈጥሩ ለሞት የማይዳርጉ በሽታዎች መካከል የቆዳ በሽታ ተጠቃሽ ነው፡፡

ይህን የተረዳው መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ ፒክሽን ሄልዝ የተባለ ጀማሪ ተቋም በማሽን ለርኒንግ እና ኮምፒዩተር ቪዥን የሚታገዝ የቆዳ በሽታ መመርመሪያ መተግበሪያ አስተዋውቋል፡፡

መተግበሪያው የሕክምና ባለሞያዎች የቆዳ በሽታዎችን በቀላሉ ፎቶ በማንሳት የበሽታውን ምንነት ለመለየት እንዲያስችላቸው በማለም መበልፀጉ ተመላክቷል፡፡

መተግበሪያውን ለማበልፀግ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቆዳ ሐኪሞች (ደርማቶሎጂስት) መሣተፋቸው ተገልጿል፡፡ በውጤቱም ከአስራ ስምንት ሀገራት የተውጣጣ የቆዳ በሽታዎችን የሚያመለክት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የፎቶ ስብስቦች መተግበሪያውን ለማስተማር መዋላቸውን መረጃው አመላክቷል፡፡

በተቋሙ መረጃ መሠረት በዓለማችን ላይ በየዓመቱ 2.3 ቢሊዮን ሰዎች ለቆዳ በሽታዎች መፍትሔን በመሻት ወደ ጤና ተቋማት ይሄዳሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ ሁለት ሦስተኛው በዘርፉ ስፔሻሊስት ባልሆኑ ባለሞያዎች ሕክምና የሚደረግላቸው ሲሆን፤ ሃምሳ በመቶዎቹም ለተሳሳተ ምርመራ ተጋላጭ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያም በዘርፉ የሠለጠኑ ስፔሻሊስቶች ከአንድ መቶ ሰባ እንደማይዘሉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ይህም በሀገራችን የጤና ተቋማት ላይ የሚፈጥረውን ጫና የተረዳው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሀገራችን የሚከሰቱ የቆዳ በሽታዎችን መለየት የሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት አበልፅጎ ወደ ስራ ለማስገባት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡
184 views05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 11:18:35

246 views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 09:09:51

254 views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:58:34
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እንኳን ለ1443ኛው የዒድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ! በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን፡፡
294 views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 15:15:29
ሁለት መቶ ቋንቋዎችን መተርጎም የሚችለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

የፌስቡክ እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ ሁለት መቶ አራት ቋንቋዎችን መተርጎም የሚያስችል የላቀ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ማሳካቱን አስታወቀ፡፡

‘No Language Left Behind’ በሚል ስያሜ ሥርዓቱ ሲበለፅግ እንደቆየ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ ገልፀዋል፡፡

ሥርዓቱ በስፋት የማይነገሩ እና በይነ መረብ ላይ ባላቸው እጅግ አነስተኛ ዳታ ምክንያት ለማሽን ትርጉም ከባድ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቋንቋዎች ማካተቱን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በኢንዶኔዢያ፣ በመካከለኛው እና ደቡባዊ አፍሪካ የሚነገሩ ቋንቋዎች የትርጉም ሥርዓቱ ካካተታቸው መካከል በመሆን በመረጃው ተጠቅሰዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የሥርዓቱን ወደ ስራ መግባት ይፋ ባደረጉበት ገለጻቸው በሥራ ላይ ባሉ ሌሎች የማሽን ትርጉም ሥርዓቶች ያልተካተቱ ቋንቋዎች መካተታቸውን አብራርተዋል፡፡

በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሚናገሯቸው ቋንቋዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው ትርጉም ለማቅረብ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ብልሀቶች ጥቅም ላይ መዋላቸውንም ጨምረው አመላክተዋል፡፡

ኩባንያው ይህን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የትርጉም ሥርዓት ከራሱ የማሕበራዊ ትስስር መድረኮች ባሻገር ዊኪፒዲያ የተባለው ድረ-ገጽም ተጠቃሚ እንዲሆን በትብብር እየሰራ ስለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ቬንቸር ቢት በተባለው ድረ-ገጽ መረጃ መሠረት የጉግል ተመሳሳይ ሥርዓት አንድ መቶ ሰላሳ ሦስት ቋንቋዎችን ብቻ ያካትታል፡፡ በሌላ በኩል የማይክሮሶፍት መተርጎሚያዎች ከመቶ በጥቂቱ የተሻገሩ ቋንቋዎችን ያካተቱ ስለመሆናቸው መረጃው ያመላክታል፡፡
310 views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 13:13:11
ስለራሱ ጥናታዊ ጽሁፍ እንዲጽፍ የተጠየቀው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

የምርምር ሥራዎች እና መረጃዎችን በማሳተም የሚታወቀው የሳይንቲፊክ አሜሪካ መጽሔት ድረ-ገጽ ከሰሞኑ አንድ አስገራሚ ጉዳይ አስነብቧል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፤ አልሚራ ኦስማኖቪክ ተንስትሮም የተባለች ስዊድናዊት ተመራማሪ GPT-3 (Generative Pre-trained Transformer 3) የተባለውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ለመፈተን ታስባለች፡፡

የሚቀርብለትን ጥቂት ዓረፍተ ነገር ተቀብሎ ሰፊ ጽሁፍ ለሚያቀርበው ለዚህ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ተመራማሪዋ “አጋዥ ግብዓቶችን እና ማጠቀሻዎችን ያካተተ ስለ GPT-3 በአምስት መቶ ቃላት ጥናታዊ ጽሁፍ ጻፍ” ስትል ትዕዛዝ ትሰጣለች፡፡

ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ እሷን ጨምሮ ብዙዎችን ያስገረመው እና አሁን ላይ በሳይንስ ጆርናሎች ለሕትመት እንዲበቃ በዘርፉ ምሁራን እየተገመገመ ያለውን ጽሁፍ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱ ያቀረበው፡፡

ሥርዓቱ ጽሁፉን መጻፍ እንደጀመረ “በአግራሞት ቀጥ ብዬ ቀረሁ” ትላለች ተመራማሪዋ፡፡ የአግራሞቷን ምንጭ ስታብራራም በትምህርታዊ ቋንቋ የተደራጀ እና በበቂ ሁኔታ የተደገፉ ማጣቀሻዎችን በትክክለኛው ቦታ ያስቀመጠ ጥናታዊ ጽሁፍ መመልከቷ እንደነበር ታብራራለች፡፡

ከሰጠችው ግልፅ ያልሆነ መመሪያ አንጻር ብዙ እንዳልጠበቀች የምትናገረው ተመራማሪዋ ይህ የዲፕ ለርኒንግ ስልተ ቀመር ስለራሱ ጥናታዊ ጽሁፍ ሲጽፍ በአግራሞት ከመመልከት በቀር አማራጭ አልነበራትም፡፡

#GPT3 መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ሰን ፍራንሲስኮ ባደረገው ኦፕን ኤ.አይ የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የምርምር ተቋም የበለፀገ ሥርዓት ነው፡፡
266 views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 09:07:34
አንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለሽልማት ያዘጋጀው የሁዋዌ የፈጠራ ውድድር

የቻይናው የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ በየዓመቱ የሚያካሂደውን ዓለም አቀፍ የፈጠራ ውድድር ዘንድሮም ከተሻለ የሽልማት ገንዘብ መጠን ጋር ለተወዳዳሪዎች ክፍት አድርጓል፡፡

#AppsUP ተብሎ የሚታወቀው ዓመታዊ ውድድር ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በዋናነትም የሞባይል መተግበሪያ ፈጠራዎች ላይ ያተኩራል፡፡

#TogetherWeInnovate በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው መርሃ ግብር ከሞባይል መተግበሪያዎች ባሻገር አዳዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አድማሶችን ለመዳሰስ ይረዳል ያለውን በዘርፉ የሚደረግ ውድድር ይፋ አድርጓል፡፡

ሁዋዌ ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቧቸውን የላቁ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መፍትሔዎች ከውድድሩ በማሰባሰብ ለተጠቃሚዎች የማቅረብ ተስፋ መሰነቁን የኩባንያው ድረ-ገጽ ያስረዳል፡፡

በተለያዩ ዘርፎች ለሚደረገው ፉክክር በአጠቃላይ አንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ለሽልማት መዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡

በአፍሪካ፣ ቻይና፣ ኤዢያ ፓስፊክ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውሮፓ የሚገኙ ፍላጎቱ ያላቸው ተወዳዳሪዎች እስከ አውሮፓውያኑ ጥቅምት 9፤ 2022 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደሚችሉ መረጃው አመላክቷል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና የውድድሩ ተሳታፊ ለመሆን ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡ https://bit.ly/3RiB5Xl
294 views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:32:33

322 views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:58:04

325 views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ