Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_orthodox
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 30.50K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡
ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot
Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-03-26 23:11:09
@Ethiopian_Orthodox
656 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 23:11:09 በቅርቡ በተቋቋመው በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፤ በአገልጋዮቿ እና በምእመናን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ ።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በተለያየ ዘመን በተነሱ ቅዱሳን ክርስትና እንዲሰበክ በማድረግ ለሺህ ዓመታት የሀገሪቱ የሃይማኖት፣ የታሪክ እና የሞራል ምንጭ ሆና ኖራለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን ራሷ የሆነው ክርስቶስን በመስበክ ያላመኑትን ከማሳመን፣ ያመኑትን ከማፅናት እና የፀኑትን ከመቀደስ ውጪ ሌላ ምድራዊ ዓላማ ሳይኖራት ነገስታቱንም ሆነ ምዕመኑን እኩል ንስሀ አባት መድባ አና ንስሀ አቀብላ፣ ቀድሳ አቁርባ እና ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩም ለሁሉም እኩል ፍትሃት አድርጋ የምትሸኝ ሰውን በፆታው፣ በቋንቋው፣ በነገዱ እና በማንነቱ አድሎ ሳታደርግ የኖረች ናት። ሆኖም ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን ውስጥ ያለአንዳች ማስረጃ የተፈጠሩ የሀሰት ትርክቶች እና እነዚህን ትርክቶች መሠረት ተደርገው በሰፊው ሲነዙ የነበሩ ሀሰተኛ መረጃዎች ቤተ ክርስቲያንን ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል፡፡

አሁን አሁን የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እና ምእመናን በሃይማኖታቸው ብቻ ተለይተው በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ባሉ አካላት ካህናት አባቶቻችን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ስጋና ደሙን ቀድሰውና አክብረው ለሰዎች ድህነት ይሆኑ ዘንድ በተሰጣቸው ስልጣነ ክህነት ምእመናን ለርስት መንግሥተ ሰማያት የሚያበቁ ሁነው ሳለ በተለያዩ ጊዜ ለሞት እና ለእንግልት እንዲሁም ለስደት እና ለእስራት ሲዳረጉ ማዬት የእለት ተእለት ተግባር ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡

በአዲሱ መንግስታዊ መዋቅራዊ አደረጃጀት በአዲስ አበባ ዙርያ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ በሜጢ ሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን የነበሩት ቄስ አባይ መለሰ በመጋቢት ፲ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ከቅዳሴ ወጥተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲሄዱ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተፈጸመባቸው ድብደባ ሕይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን ተረድተናል፡፡
መንግሥት የዜጎችን በሰላም ወጥቶ የመግባት ደህንነት የማስጠበቅ እና ዋስትና የመስጠት እንዲሁም ጭካኔ እና አረመኔያዊ ከሆኑ ጥቃቶች የመጠበቅ መንግሥታዊ ኃላፊነት ሊኖርበት ይህንን ባለመወጣቱ ምክንያት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እና ዜጎች በሕይወት የመኖር መብት በየእለቱ እየተሸረሸረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሀገረ ስብከታችን በቀሲስ አብይ መለስ ሞት የተሰማንን መሪር ኃዘን እየገለጽን የሚመለከተው የፌዴራል፤ የአዲስ አበባ ከተማ እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የፍትህ አካል ጉዳዩን ልዩ ትኩረት በመስጠት ተገቢውን ምርምራ በማድረግ ይህንን አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበትን የግድያ ወንጀል የፈጸሙ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ስር የሚተዳደሩ ቁጥራቸው ከዐሥራ ሦስት በላይ የሆኑ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በአዲሱ የከተማ ድንበር ማካለል ወደ ኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ክልል ውስጥ የተካለሉ ቢሆኑም ለዓመታት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገንብተው መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጡ ከቆዩ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ

፩ የኤርቱ ሞጀ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናትን ለማፍረስ ተሞክሮ ከእነዚህ ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በመሉ በአፍራሽ ግብረ ሀይል እንዲፈርስ ከመደረጉም በላይ የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያን በውስጡ ከሚገኙ ንዋያተ ቅድሳት ጋር በሙሉ እንዲቃጠሉ እና እንዲወድሙ ተደርጓል፡፡

፪. በኤርቱ ሞጆ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን አጥሩን ማፍረስ ተጀምሮ ምእመናን እና የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ባደረጉት ርብርብ የማፍረስ : ሒደቱ ለጊዜው ቢቆምም አሁንም ይህን ቤተ ክርስቲያንም ሆነ በሸገር ከተማ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ስለሆነም ለሀገር ባለውለታ የሆነችን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በማሳደድ እና በማውደም ታሪካዊ መሠረቷን ለመናድ እና ከሌሎች ቤተ እምነቶች በመነጠል በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተፈጸመ ያለው አድሏዊ እና ኢ-ሕገ መንግስታዊ የሆነው ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም እንዲደረግ እያሳሰብን የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥትም የድርጊቱን ፈጻሚ አካላት ላይ ተገቢውን እርምት እንዲወስድ ስንል እንጠይቃለን፤

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሚመለከተው ባለስልጣን አካል በየካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በገነተ ጽጌ ቅዱስ
ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን እና ሕገ ወጥ ተግባርን በተመለከተ የድርጊቱን ፈጻሚ አካላትን በ፭ ቀናት ጊዜ ውስጥ ተለይተው በሕግ ተጠያቂ በማድረግ ለሕዝብ እንዲያሳጡት ጥሪ ያስተላለፈች ቢሆንም ይህ መግለጫ አስከሚሰጥ ድረስ ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑ አካላት ተለይተው ተጠያቂ አለመሆናቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችውን ጥያቄ ምላሽ ሊሰጥ ያልቻለ በመሆኑ የድርጊቱን መነሻ ምክንያት የደረሰውን ጉዳት እና የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ ለሕዝብ ይፋ የሚያደርግ የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ በማዋቀር ወደሥራ የተገባ መሆኑን እያሳወቅን ኮሚቴው የደረሰበትን ጥቅል መረጃ በአጭር ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ሪፖርቱን የሚያቀርብ እና የድርጊቱ ፈጻሚዎች ቤተ ክርስቲያንን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ እና አጥፊዎችም ለድርጊታቸው ተገቢውን ሕጋዊ ቅጣት እንዲያገኙ እየሠራን መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም፡

፩. መንግሥት የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በመሆናቸው ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ በመንገድ ላይ ተደብድበው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የተደረጉት የቄስ ዐብይ መለሰ ገዳዮችን ተከታትሎ ለፍርድ እንዲያቀርብ እና ችግሩን ከሥር ከመሠረቱ በመፍታት የአገልጋዮችንና የምእመናን መብት እንዲያስከብር
፪. በሸገር ከተማ አስተዳደር እየተፈፀመ ያለው አብያተ ክርስቲያናትን የማፍረስ ድርጊት በአስቸኴይ እንዲቆም እንዲደረግ፣

፫. የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ቦታ ተመላሽ እንዲያደርግ እና የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያንም በራሱ ወጪ እንዲያሠራ እንዲደረግ እንጠይቃለን።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናን እና ምእመናት እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ አባቶች ዘመነ ቤተ ክርስቲያንን በጉልበታችን፤ በዕውቀታችን እና በገንዘባችን የምናገለግልበት ብቻ ሳይሆን በአካላችን፣ በጤናችን እና በሕይወታችንም መስዋዕትነትን የምንከፍልበት የሰማዕትነት ዘመን ነው፡፡ ይህ የሰማዕትነት መከራም በሀገራችንና በየቤታችን እየመጣ ያለ የመከራ ዘመን በመሆኑ አብዝቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ፤ ሥጋችንን በጾም እና በስግደት በመግራት ከአባቶቻችሁ አባታዊ መመሪያ በመቀበል በሃይማኖታችሁ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር ሀገራችንን እና ህዝቦቿን ይባርክ ።
መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም

@Ethiopian_Orthodox
668 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 10:41:32
የሁለቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ክቡር አስክሬን ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በክብር ደርሷል።

ኢኦተቤ ቴቪ መጋቢት ፲፯ ፳፻፲፭ ዓ/ም

መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ክቡር አስከሬን በክብር ካረፈበት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በቤተሰቦቻቸው እና በምእመናን ታጅቦ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በክብር የገባ ሲሆን ፤ሌሊት የማህሌትና የሰዓታት ቁመት ሲከወን አድሯል።
መጋቢት ፲፮ ቀን በዛሬው ዕለትም ከጠዋቱ 2:30 በክብር ካረፈበት ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት ዘማርያን እንዲሁም በወዳጅ ዘመዶቻቸው ክቡር አስክሬናቸው ታጅቦ ስርዓተ ቀብሩ ወደሚከወንበት ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ደርሷል።
በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ፓትርያርክ እንዲሁም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሥርዓተ ጸሎት ሥርዓተ ቀብራቸው እንደሚፈፀም ታውቋል።
የብፁዓን አባቶቻችን በረከት ይደርብን።

ዕሌኒ ክፍሌ

Eotc Tv
@Ethiopian_Orthodox
1.9K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 21:48:43 "ገብር ኄር"
በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.2K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 21:48:42
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.1K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 21:48:42 ተብለን ወደ ውርደት አዘቅት እንዳንላክ መጠንቀቁ አይከፋም፡፡ የመሾም የመሻር የማሳደግና የማውረድ ሥልጣን የእግዚአብሔር ነውና፡፡ “ከእናንተ መካከል አንዱን እንኳ እንዳናስቸግር ቀንም ሌሊትም እንሠራ ነበር” (፩ኛ ተሰ. ፪፥፱) በጎና ታማኝ አገልጋዮች ሆነን እንድንገኝ ጠንክረን ልንሠራ ይገባናል፡፡

 በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-፪ኛ ጢሞ ፪፥፩-፲፮
-፩ኛ ጴጥ ፭፥፩-፲፪
-የሐዋ ሥራ ፩፥፮-፱

ምስባኩም፦ መዝ ፴፱፥፰
"ከመ እግበር ፈቃድከ መከርኩ አምላኪየ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ"
"አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድኩ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው በታላቅ ጉባዔ ጽድቅህን አወራሁ"

ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፭፥፲፬-፴፩

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.0K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 21:48:42 የመጽሐፍ ቅዱስ መተርጉማን አባቶች የዚህን ምሳሌያዊ ታሪክ ምስጢር ሲያስተምሩ የአገልጋዮቹ ጌታ የፍጡራን ጌታ የሆነ የእግዚአብሔር ምሳሌ እንደሆነ እንዲሁም ሦስቱ አገልጋዮች በተለያየ ደረጃ ያሉ ምዕመናንን እንደሚወክሉ ያስተምራሉ፡፡

ከዚህ የወንጌል ክፍል ምን እንማራለን?

ከተጠቀሰው ታሪክ የምንማራቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዓበይት የሆኑትን ሁለቱን እንመልከታቸው፡፡

ለእያንዳንዳችን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ እንዳለ እንረዳበታለን

እግዚአብሔር እያንዳንዳችን በሃይማኖት ሆነን የምናፈራውን ፍሬ ይፈልጋል፡፡ ምንም እንኳን ከእኛ ፍሬን ቢፈልግም ያን ፍሬ ማፍራት የምንችልበትን ኃይል ግን የእግዚአብሔርን ልጅነት ካገኘንበት ከዕለተ ጥምቀት ጀምሮ እንደሚያስፈልገን መጠን እየሰጠን ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበልናቸው ስጦታዎች በቁጥር እጅግ ብዙ ቢሆኑም በዓይነታቸው ግን ለሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው እያንዳንዱ ክርስቲያን ዳግመኛ በመወለድ ምስጢር ያገኘው የእግዚአብሔር ልጅነት ጸጋና ከልጅነት ጋር በተያያዘ የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው (ዮሐ.3፥3)። ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድና እንደ ሰውየው አቅም ለተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ማስፈፀሚያ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ትንቢት መናገር ፣ በተለያዩ ልሳናት መናገር ፣ አጋንንትን ማስወጣት … የመሳሰሉት ከዚህኛው ዓይነት ስጦታ የሚመደቡ ናቸው (1ኛ ቆሮ.12፥4)፡፡

በመጀመሪያውም ይሁን በሁለተኛው ዓይነት ስጦታ ተቀባዮች ዘንድ ግን ብዙ የሚያሳዝኑ ችግሮች አሉ፡፡ በዳግመኛ መወለድ ምሥጢር (በ40 ና 80 ቀን ጥምቀት) ስላገኘነው የልጅነት ጸጋ ጊዜ ሰጥቶ የሚያስብ ክርስቲያን ማግኘት በዚህ ዘመን በጣም አዳጋች ነው፡፡ በዓመት ውስጥ ክርስቲያንነቱ ለጥምቀት በዓልና ለመስቀል ደመራ ካልሆነ ትዝ የማይለው ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ የከፋው ደግሞ ከቤተ ዘመድ አንድ ሰው ምናልባትም ራሱም ሊሆን ይችላል ነፍሱ ከሥጋው ካልተለየች ወደ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ብቅ አይልም፡፡

እግዚአብሔር ለእኛ የልጅነትን ጸጋ በመስጠቱ ለእኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅሩን አሳይቶናል፡፡ ምክንያቱም ልጅነታችን ዋጋ ተከፍሎበታልና፡፡ እንዲሁ በቀላሉ አይደለም ልጆች የተባልነው፡፡ እኛ ልጅነትን እንድንቀበል አምላክ መከራን ተቀብሏል፡፡ የጥምቀታችን ውሃ የፈሰሰው በጦር ከተወጋው ከጌታ ጎን ነው (ዮሐ.19፥24)፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ይሄንን ሁሉ ሲያመለክት ”የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ፡፡” (1ኛ ዮሐ.3-1) እኛ ልጆቹ እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ካሳየን የአባትነት ፍቅር በተጨማሪ ልጆቹ ስለመሆናችን የገባልንም ተስፋ ከአዕምሮ በላይ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ምዕመናን በላከው መልእክቱ ”እንኪያስ እናንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይደላችሁም፡፡ ልጆች ከሆናችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ፡፡” (ገላ.4:7) በማለት  ስለሚጠብቀን ተስፋ ነግሮናል፡፡

ስለዚህ በጣም ልንጠነቀቅበት የሚገባን የመጀመሪያው መክሊታችን ልጅነታችን መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል፡፡ በዚህም መክሊት እንድንሰራ የታዘዝናቸውን ምግባራት እንድናፈራ የሚጠበቅብንን ፍሬዎች ማፍራት አለብን፡፡ ያለበለዚያ መክሊቱን እንደቀበረው ሰው መሆናችን ነው፡፡

እያንዳንዱ ስጦታ እንደሚያስጠይቅ እንረዳለን

እግዚአብሔር ያለ አንድ አላማ ለሰዎች ሓላፊነትን የሚያሰከትል ስጦታ አልሰጠም አይሰጥምም፡፡ ማንም ከእግዚአብሔር የተቀበለ ሰው የተሰጠው ስጦታ ለሆነ አላማ ነውና ጥያቄ አለበት፡፡ ጠያቂው ደግሞ የስጦታው ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ይሁን ማን ግን ስለተሰጠው መክሊት ባለቤቱ ከፊቱ አቁሞ እንደሚጠይቀው መዘንጋት የለበትም፡፡እንግዲህ በአጠቃላይ መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ሰጥቶናል፡፡ በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ የሰማናትን ቃለ እግዚአብሔር ለሌላው ማሰማት ይገባናል ፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፡፡ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ በመሆኑም እርሱ በሰጠን የአገልግሎት በር ጸጋ በታማኝነት በማገልገል በሕይወት ዘመናችን ሁሉ መንፈሳዊውን ሀብት የምናተርፍ እንሆን ዘንድ የተላለፈልን አምላካዊ ምክር ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የተጠራነው ፍሬ ልናፈራና ሌላውንም ልናተርፍ መልካም ሥራን ልንሠራ እንጂ የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል የኃጢአት ባሮች ልንሆን አይደለም፡፡ መጽሐፍ እንደሚነግረን  ¨ሁሉ እንደተጠራ እንዲሁ ይኑር” (፩ኛ ቆሮ. ፯፥፳) ይላልና።

አሁን ባለንበት ወቅት በጎና ታማኝ አገልጋይ መሆን እንዳንችል ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ የችግሮቹም መሠረታዊ ምንጭ በተጠሩበት ጸንቶ መቆም ፈጽሞ አለመቻልና ለሥጋዊ ጥቅም ብቻ በማድላት ሓላፊነትን መዘንጋት ናቸው፡፡ በሥጋዊ አምሮት ፍላጎትና ምርጫ ውስጥ ደግሞ መንፈሳዊ ጸጋንና በረከትን ለማግኘት የሚያስችለንን የታማኝነት ሥራን መሥራት አይቻልምና በታማኝነት ከምናድነው ሰው ይልቅ መክሊታችንን በመቅበር ባለመታመን መሰናክል የምንሆንበት ሰው ሊበዛ እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ በመሆኑም ከእርሱ ዘንድ እንደ ዓቅማችን የተሰጠንን መንፈሳዊ ዕውቀት ሀብትና አገልግሎት ለሌላው በማድረስ መክሊታችንን ልናበዛ የምንችለውና አገልግሎታችን ወይም ክርስትናችን ውጤታማ የሚሆነው ምርጫችንን አውቀን እንደቃሉ ሆነንና ጸንተን ስንገኝ ብቻ ነው፡፡ ይህ ባለመሆኑ ነው ዛሬ ብዙዎቻችን በሕይወታችን ሌላውን ማትረፍ አቅቶን በእግዚአብሔርና በሰውም ዘንድ በሚያስወቅስ የስንፍና መንገድ ላይ ቆመን የምንገኘው፡፡ ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው “ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ” (ማቴ. ፳፬፥፵፪) ብሎናል፡፡

ቃሉን የሰማንና የምናውቅ ሁላችን በሞቱ ላዳነን፣ በልጅነት ጸጋም ላከበረን፣ በትንሣኤውም ላረጋጋን፣ በመስቀሉ ጥልን ገድሎ ከራሱ ጋር ላስታረቀን፣ በውኂዘ ደሙም ሕይወትን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ በረከትንና ዘለዓለማዊ ደስታን ለሰጠን አምላካችን በመታዘዝ አቅማችን በሚፈቅደው አገልግሎት ጸንቶ መገኘት ተገቢ ነው፡፡ በአገልግሎት የመጽናት ምልክቱ ደግሞ አትራፊነት ነው፡፡ ቅዱሳን ነቢያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ በአትራፊነት ይታወቃሉ፡፡ ለማትረፍ ግን ራሳቸውን ለእውነት ለአገልግሎት ለመከራ አሳልፈው በመስጠት ነው፤ በትንሹ መታመን ሲባል የእኛ አገልግሎት ከፈጣሪ ቸርነት ጋር ስለማይመጣጠን ነው፤ በብዙ እሾምሃለሁ ማለቱም በመንግሥተ ሰማያት ለዘለዓለም ከብሮ መኖርን ነው፡፡

ከቅዱሳን ነቢያትም ሐዋርያትም ሰብአ አርድእትም ሊቃውንትም የሰማነውና ያየነው እውነት ምንጊዜም ትጉህ ሠራተኛ የሚሠራው መልካም ሥራ ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንም ለሀገርም የሚሰጠው ጥቅም እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘመን ልዑል እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን፤ ምእመናንን፤ ሀገርንና ሕዝብን ለመምራት የጠራንና የመረጠን፤ በአገልግሎት ዐደባባይ ያስቀመጠን ሰዎች እጅግ ዕድለኞች ነን፤ ምክንያቱም የሕዝብን ችግርና አቤቱታ ሰምቶ ተቀብሎ መፍትሔ መስጠት ትርፋማነት ነውና፤ ትርፋማነት ደግሞ ወደ ትልቁ የሹመት መሰላል መውጣት ነው፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ አገልግሎታችን ተደናቅፎ የሕዝባችን ችግር ሳይፈታ ቀርቶ የአገልግሎታችን ተቆጣጣሪ አምላካችን ቢጎበኘን “አንተ ሰነፍ አገልጋይ”
1.8K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 21:48:42 ገብር ኄር
የዐብይ ጾም ስድስተኛ እሑድ(ሳምንት)


ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን ”ገብርኄር” የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርኄር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ. 25:14-30 ነው፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የዛሬው ወንጌል አስተማሪ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በተለይ ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ሓላፊነት የእገሌና የእገሊት ተበሎ ባይወሰንም ቤተ ክርስቲያን ባላት የአገልግሎት መዋቅር መሠረት የሓላፊነትን ቦታ ይዘው ለሚያገለግሉ ሰዎች አትኩሮት ሊሰጡባቸው የሚገባቸውን ነጥቦች ይጠቁማል፡፡ ይህን ለማየት ያመቸን ዘንድ ከታሪኩ የመጀመያ ክፍል በመነሣት ዋና ዋና የሆኑ ዐሳቦችን በአትኩሮት መመርመር  ጠቃሚ ነው፡፡

በምሳሌያዊው ታሪክ መጀመሪያ ላይ የምናገኘው አንድ መንገድ ሊጀምር ያሰበ ሰው ከመሔዱ በፊት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት እንዲሁም ለሌላኛው አንድ መክሊት ነግደው ያተርፉበት ዘንድ እንደሰጣቸው ነው፡፡ ገና ከታሪኩ መጀመሪያ እንደምንረዳው የአገልጋዮቹ ጌታ ምንም እንኳን እርሱ ለመንገድ ቢዘጋጅም ሀብቱ ግን በተዘጋ ቤት ውስጥ ተቆልፎበት እንዲቀመጥ አልፈለገም፡፡ በዚህም አገልጋዮቹን ጠርቶ ገንዘቡን በአደራ ተቀብለው እንዲያተርፉበት ማዘዙን እንደማስረጃ ልናቀርብ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ማትረፍ በመፈለጉ ብቻ ገንዘቡን ያለአግባብ አልበተነም፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ቀረቤታ የነበራቸውን አገልጋዮቹን ጠርቶ ያውም እንደየችሎታቸው መጠን ሓላፊነቱ ሳይከብዳቸው እንዲሠሩበት ገንዘቡን አከፋፈላቸው፡፡

ይህ ጌታ ቅንነትና ርኅራኄ የበዛለት እንደሆነ የሚያመላክተን ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለአገልጋዮቹ ሓላፊነትን ቢሰጥም እንኳን ከእነርሱ ጋር በነበረው ቀረቤታ ማን ምን መሥራት ይችላል የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው እንደ ሓላፊነት የመሸከም አቅማቸው አምስት ሁለት አንድ እያደረገ መስጠቱ ነው፡፡ ምናልባት ስስት ባልተላቀቀው ስሜት ለሚያስብ ሰው የዚህ ጌታ መክሊት አሰጣጥ አድልዎ ያለበት ሊመስለው ይችላል፡፡ ታሪኩን እስከ መጨረሻው ብንከታተለው ግን የሚያሳየን የባለ መክሊቱን ባለቤት ቅንነት ነው፡፡ ቀጥለን እንደምናነበው ይህ ጌታ ለአገልጋዮቹ አትርፉበት ብሎ መክሊቱን ሰጥቷቸው በሔደበት ሀገር አልቀረም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ በተሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው እንደመጣ እናነባለን፡፡ ስለዚህ አገልጋዮቹ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩ እንደሚጠይቃቸው እያወቀ ከአቅማቸው በላይ የሆነ መክሊትን በመስጠት ምን ሠርተው የተሰጣቸውን መክሊት ያህል ማትረፍ እንደሚችሉ በማሰብ እንዲጨነቁ አልፈለገም፡፡ በተቃራኒው የምናየው ያለምንም ጭንቀት ከአእምሯቸው በላይ ሳይሆን ባላቸው ኀይል ተጠቅመው መሥራትና ማትረፍ የሚችሉትን ያህል መክሊት እንደሰጣቸው ነው፡፡

ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው ሲመጣ አምስት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ አምስት እንዲሁም ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ ሁለት መክሊት አትርፎ ጌታቸው ፊት እንደቆሙ ያ ጌታም በእነዚህ አገልጋዮቹ ታማኝነት ተደስቶ ወደ ደስታው እንዳስገባቸው እናያለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ያ አንድ መክሊት ተቀብሎ የነበረው ምድርን ቆፍሮ ያተርፍባት ዘንድ የተሰጠችውን መክሊት እንደቀበረ ከዚህም አልፎ ምን አደረክባት ተብሎ ሲጠየቅ የአመጽ ንግግር እንደተናገረ በዚህ ከፊቱ ያዘነው ጌታውም ያን ክፉ አገልጋይ እንዲቀጣ እንዳደረገው አናነባለን፡፡

በዚህኛው ክፍል ከተጠቀሰው ታሪክ ሦስቱን አካላት ማለት የመክሊቱን ሰጪ ጌታ፣ በጎ የተባሉ አገልጋዮችና ክፉ እና ሰነፍ የተባለውን አገልጋይ በተናጥል እንመልከታቸው፡፡

1. የአገልጋዮቹ ጌታ፡–

ይህ ሰው ለገንዘቡ ጠንቃቃ ከመሆኑ ባሻገር በአገልጋዮቹ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው እናያለን፡፡ በክፉው አገልጋይ ላይ ባለመታዘዙ ምክንያት የፈረደበትን ፍርድ /ልቅሶና ጥርስ ማፏጨት ወዳለበት በውጪ ወዳለ ጨለማ እንደአወጡት/ ስንመለከት የሚያሳየን የአገልጋዮቹን ጌታ ታላቅ ሥልጣን ነው፡፡ ምንም እንኳን ሥልጣኑ ጽኑ ቢሆንም ይህ ጌታ ፍርዱ ግን በእውነት ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ደግሞ በድካማቸው ታግዘው በተሰጣቸው መክሊት ላተረፉት በጎ አገልጋዮች የሰጣቸውን ፍጹም ደስታ መጥቀስ ይቻላል፡፡

2. በጎ አገልጋዮች:-

በአገልጋዮቹ ጌታ በጎ አገልጋዮች የተባሉት አምስት መክሊት የተቀበለውና ሁለት መክሊት የተቀበለው ናቸው፡፡ እዚህ ጋር ማስተዋል የሚገባው እነዚህ ሁለቱ አገልጋዮች በጎ አገልጋዮች ለመባል ያበቃቸው አስቀድመው ብዙ ወይንም የተሻለ ቁጥር ያለው መክሊት ለመቀበል መብቃታቸው አይደለም፡፡ ጉዳዩ የመክሊቱ ቁጥር ሳይሆን በተሰጣቸው መክሊት መጠን የሚገባቸውን ያህል ደክመው ማትረፍ መቻላቸው ነው፡፡ ወይንም ያ ባለ አንድ መክሊት አገልጋይ ከሁለቱ ያሳነሰው ከአንድ በላይ መክሊት መቀበል የማይችል መሆኑ ሳይሆን በዚያችው በአንዷ መክሊት እንኳን መሥራት አለመቻሉ ነው፡፡

3. ክፉና ሰነፍ አገልጋይ:-

ይህ ሰው የተጠቀሱ ሦስት መሠረታዊ ችግሮች አሉበት፡፡

የአገልጋዮቹ ጌታ ወደ መንገድ ሊሔድ በተዘጋጀበት ወቅት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደችሎታቸው ገንዘቡን ሲሰጣቸው አትርፈው እንዲቆዩት ነው፡፡ ከላይ እንደተነገጋገርነው እንደ አቅማቸው መስጠቱም አቅማቸው በሚፈቅደው የሥራ ደረጃ እንዲሰማሩ በማሰብ ነበር፡፡ ይህ ሰነፍ አገልጋይ ግን ያደረገው ከታዘዘበት ዓላማ በተቃራኒው መልኩ ነው፡፡ ሊሠራበት የሚገባውን መክሊት ቀበረው፡፡ ይህም ለጌታው ትዕዛዝ ያለውን ቸልተኝነት ያሳያል፡፡

ጌታው በመጣ ጊዜ አመጽ የተመላበት የሐሰት ንግግር ተናግሯል፡- ከሔደበት ቦታ ተመልሶ ጌታው በተሰጠው መክሊት ምን እንዳደረገ ሲጠይቀው «አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበሰብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ ስለፈራሁም ሔድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፡፡» ሲል መለሰለት፡፡ ይህ ንግግር ከአመጽ ንግግርነቱ በተጨማሪ ውሸት አለበት፡፡ ምክንያቱም እርሱ እንዳለው ጌታው ካልዘራበት የሚያጭድ ካልበተነበት የሚሰበሰብ ጨካኝ ሰው ቢሆን ኖሮ ያደርግ የነበረው ምንም መክሊት ሳይሰጠው ከነትርፉ ሁለት መክሊቶችን ይጠይቀው ነበር፡፡ ነገር ግን ተጽፎ የምናነበው ትርፉን ከመጠየቅ በፊት አንድ መክሊት ሰጥቶት እንደበረ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አስቀድሞ ገንዘቡን ዘርቶ ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ጌታ ዘርቷልና ማጨድ ይገባዋል፤ በትኗልና መሰብሰብም መብቱ ነው፡፡

እርሱ መሥራት ሲሳነው እንኳን ዕድሉን ለሌሎች አልሰጠም፡- ይህ ሰው የተሰጠው መክሊት በትርፍ ሊመለስ እንደሚገባው ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ምክንያቱም ገና ሲቀበል ከጌታው የተቀበለው ትዕዛዝ ነውና፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን መውጣት መውረዱ ቢከብደውም ወጥተው ወርደው ማትረፍ ለሚችሉ ሰዎች አለመስጠቱ ተጨማሪ ጥፋቱ ነው፡፡ ይህን እንዳያደርግ ያሰረው ደግሞ ውስጡ የተቀረጸው የአመጽ መንፈስ ነው፡፡ ጌታው መጥቶ ስለ ትርፉ ሲጠይቀው የሚመልስለትን ረብ የለሽ ምክንያት እንደ መከላከያ አድርጎ ማሰቡ አእምሮው ሌላ አማራጭ እንዳያስብ የዘጋበት ይመስላል፡፡
1.9K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 17:49:08
@Ethiopian_Orthodox
877 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 17:49:08 5. የተከበራችሁ በትግራይ ክልል የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያን በአባቶቻችሁ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ጸንታ እስከአሁን መቆየቷን ለእናንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ በመሆኑም በአገራችን በተከሰተው ፖለቲካዊ ችግር ዘመናትን በጽናት የተሻገረችውን እናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አንድነቷ መፍረስ ሲኖዶሳዊ ልዕልናዋ መጣስ የሌለበት መሆኑን በጽናት እንደምታምኑ እምነታችን የጸና ነው፡፡
ስለሆነም በሚያልፍ ችግር የማያልፍ ታሪክ ጥለን ማለፍ ስለሌለብን እንደቀደሙ አባቶቻችሁ አበው ሊቃውንት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ አንድነት አስፈላጊውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል በጽናት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቀደሙ አባቶቻችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

6. የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስቱም በክልሉ ተፈጥሮ የቆየው ችግር በሰላማዊ መንገድ በውይይት በመፈታቱ እናት ቤተ ክርስቲያን የተሰማትን ደስታ እየገለጸች አስቀድሞ ችግሩ ከመከሰቱ በፊት አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን የተመራው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለቀረበው የሰላም ጥሪ እናት ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛውን ሚና እንደተጫወተች እናስታውሳለን፡፡
በመሆኑም በተከሰተው ችግር የተፈጠሩ ጉድለቶች ካለ ጉድለቶችን ለማረምና ችግሮቹን ለመፍታት ቤተ ክርስቲያናችን ያላትን የጸና አቋም እየገለጽን በክልሉ የተከሰተውን ተቋማዊ አንድነትን የሚጥስና ቀኖና የጣሰ አደረጃጀት እንዲቆም የበኩሉን ሚና በመጫወት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ አንድነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም መላው በትግራይ ክልል የምትገኙ ምእመናንና ምእመናት በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተከሰተው ፈተና እንዲወገድና አንድነቷ ጸንቶ እንዲኖር በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ ስታግዙ እንደቆያችሁት ሁሉ አሁንም በክልሉ የተከሰተውን ቀኖናዊ ጥሰትና ሕገወጥ አደረጃጀት ቆሞ እናት ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷ ጸንታ እንድትኖር እንደአሁን ቀደሙ በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እየጠየቅን የኢፌዴሪ መንግስትም እንደአሁን ቀደሙ በሲኖዶሳዊ አንድነት ላይና በቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀት ላይ የተጋረጠው ችግር ልዩ ትኩረት በመስተጠና የበኩሉን ሚና በመጫወት የቤተ ክርስቲያናችንን ሲኖዶሳዊ አንድንትና ነባር መዋቅራዊ አደረጃጀት ጸንቶ እንዲኖር አገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
መጋቤት 15 ቀን 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

@Ethiopian_Orthodox
885 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ