Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_orthodox
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 30.48K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡
ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot
Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-08 22:37:01 ሆሣዕና
የዐብይ ጾም ስምንተኛ እሑድ(ሳምንት)


ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው፡፡
ሆሣዕና ከጌታችን የአምላካችን ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ ጌታችን  አምላካችን  መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክርስቶስ  ከኢየሩሳሌም  ወደ  ቤተ  መቅደስ  ለመግባት  በፈለገ  ጊዜ  ደቀ መዛሙርቱን  ወደ ፊታችው ባለው ሀገር "ሂዱና አህያ ከውርጭላዋ ጋራ ታስራ ታገኛላችው ፈታችው እምጡልኝ። 'ምን ታደርጋላችሁ?'  የሚላችሁ  ሰው  ካለ  'ጌታቸው  ይፈልጋቸዋል'  በሉ"  ብሎ  ላካቸው  ከዚህ  በኋላ  ደቀ  መዛሙርቱ እንዳዘዛቸው  ሄደው  ፈተው  አመጡለት  በዚያም  የተሰበሰቡት  ሁሉ  በአህዮች  ላይ  ልብሳቸውን  ጎዘጎዙለት  ጌታችንም በሁለቱ  አህዮች  ላይ  ተቀመጠ  ከሌሎቹ  እንስሳት  አህዮችን  መርጦ  በአህዮች  ተቀምጧል፡ አህዮች  በመጽሐፍ  ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸውና።

የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች። (ዘሁል 22+28)
ጌታችን በተወለደ ጊዜ አህዮች ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን ገብረዋል። (ቅዳሴ ማርያም)
የሆሣዕና እህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል: 'ለምን የተዋረዱት አህዮችን መረጠ?' ቢባል:-
፩. ደመናን አዝዞ : ነፋስን ጠቅሶ : በእሳት  መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ሲሆን ነገር  ግን የመጣው ትሕትናን  ለማስተማር : የትሕትና  ጌታ  መሆኑን  ለመግለጽ ነውና በአህያ ተቀመጠ።
፪.  ትንቢቱን  ለመፈጸም  <<አንቺ  የጽዮን  ልጅ  ሆይ  እጅግ  ደስ  ይበልሽ  አንቺ  የኢየሩሳሌም  ልጅ  ሆይ  እልል  በዪ  እነሆ  ንጉሥሽ  ጻድቅና አዳኝ  ነው  ትሁትም  ሁኖ  በአህያም  በውርንጭላቱ  ላይ  ተቀምጦ  ወደ  አንቺ  ይመጣል  ሰረገላውንም  ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል>> ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈጸም ነው። ዘካ ፱÷፩
፫.  ምሳሌውን  ለመግለጽ
ምሳሌ-  ቀድሞ  ነቢያት  ዘመነ  ጸብእ  ከሆነ  በፈረስ  ተቀምጠው  ዘገር  ነጥቀው  ይታያሉ  ዘመነ  ሰላም  ከሆነ  በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና ጌታችንም ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል።
፬.  ምሥጢሩን  ለመግለጽ
ምሥጢር-  በአህያ  የተቀመጠ  ሸሽቶ  አያመልጥም  አሳዶም  አይዝም  እሱም  ካልፈለጋችሁኝ  አልገኝም  ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል።
ህድግት የእስራኤል ምሳሌ ህድግት ቀንበር መሸከም የለመደች ናት= እስራኤልም ህግ መጠበቅ ለምደዋልና
እዋል  የአህዛብ  ምሳሌ
እዋል  ቀንበር መሸከም አልለመደችም=አህዛብም ህግ መጠበቅ አልለመዱምና (አንድም)  ህድግት  የኦሪት  ምሳሌ ህድግት ቀንበር መሸከም እንደለመደች=ኦሪትም የተለመደች ህግናትና
እዋል  የወንጌል ምሳሌ
እዋል  ቀንበር መሸከም አልለመደችም=ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ህግ ናትና
በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ ፲፮ ምእራፍ ነው ፲፬ቱን ምእራፍ በእግሩ ሂዶ ሁለቱን ምእራፍ በአህያይቱ ሂዷል በውርጭላይቱ ሁኖ ፫ ጊዜ ቤተ መቅደሱን ዙሯል ፲፬  ምእራፍ የአስርቱ  ትእዛዛትና  የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ፤ አስሩ  ምእራፍ የአስርቱ ትአዛዛት፣ አራቱ  ምእራፍ የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ ነው፣ አራቱ  ኪዳናት የሚባሉት እነዚህ ናቸው፦ ኪዳነ  ኖህ  :  ክህነተ  መልከ  ጼዴቅ  :ግዝረተ  አብርሀም  እና ጥምቀተ ዮንሐስ ናቸው፡፡
በአህያይቱ  ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል::
ልብስ  በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ  ሲሉ።
በአህያዋ  ላይ  ኳርቻ  ሳያደርጉ  ልብስ  አንጥፈውለታል :-
ኳርቻ  ይቆረቁራል  ልብስ  አይቆረቁርም  የማትቆረቁር  ህግ ሰራህልን  ሲሉ  ነው። 
ስለምን ልብሳቸውን አነጠፉለት ቢባል ? በእዩ  ልማድ ነው ፡
እዩ  የተባለው  ሰው  በእስራኤል  ላይ  ሲነግሥ  እስራኤል  ልብሳቸውን  አንጥፈውለት  ነበረና  በዚያ  ልማድ አንጥፈውለታል እኩሌቶቱ ደግሞ ዘንባባ አንጥፈውለታል ።
በዕለተ  ሆሳዕና  እስራኤላውያን  ለምን  የዘንባባ  ዝንጣፊ፤  የቴምር  ዛፍ  ዝንጣፊ  እና  የወይራ  ዛፍ  ዝንጣፊ  ይዘው  ዘመሩ?  (ማቴ. ፳፩÷፩-፲፯፣  ማር. ፲፩÷፩-፲፣  ሉቃ.  ፲፱÷፳፱-፴፰፣  ዮሐ. ፲፪÷፲፪-፲፭)
የዘንባባ ዝንጣፊ
ዘንባባ የድል ምልክት የደስታ መግለጫ የምስጋና መስጫ ነው፡፡
ይስሃቅ  በተወለደ  ጊዜ  አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል።
ይስሐቅም ያእቆብን በወለደ ጊዜ    አምላኩን በዘንባባ አመስግኗል።
እስራኤል  ከግብጽ  በወጡ  ጊዜ  በዘንባባ  ንሴብሆ  እያሉ  እህተ  ሙሴ  ማርያም  ከበሮ  እየመታች  አምላካቸውን አመስግነዋል፡፡
ዮዲት  እስራኤልን  እየገደለ  ያስቸገረው  ሆለፎርኒስን  አንገቱን  ቆርጣ  በገደለችው  ጊዜ  እስራኤል  ዮዲት  መዋኢት  ዮዲት ኀያሊት  ብለው በዘንባባ አመስግነዋታልና።
ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው።
ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው።
ዘንባባ  የነፃነት  ምልክት  ነው  ከባርነት  ነፃ  የምታወጣን  አንተነህ  ሲሉ  ነው  አኛም  ይህን  በማሰብ  ዘንባባ  ይዘን ሆሳእና  በአርያም  እያልን እለቱን  እናስባለን፡፡
የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ
የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ህይወታችንን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር  ፍሬ  የሚገኘው  ከዛፉ  ከፍታ  ላይ  ነው:-  አንተ  አምላካችን  ልዑለ  ባህሪ  ነህ  ከፍ  ከፍ  ያልክ  አምላክ  ነህ  ሲሉ ነው።
የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።
የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ
የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።
ከፊት ከኋላ ያሉት "ሆሣዕና በዓርያም ለዳዊት ልጅ መድኀኒት መባል ይገባዋል" እያሉ አመስግነውታል የምስጋና ጌታም በአህዮች ተቀምጦ ወደ መቅደስ ገብቷል።

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-ዕብ ፱፥፲፩ እስከ ፍጻሜ
-፩ጴጥ ፬፥፩-፲፪
-ሐዋ ፳፰፥፲፩ እስከ ፍጻሜ

ምስባኩም፦ መዝ፰፥፪
"እመ አፈ ደቂቅ ወሕጻናት አስተዳሎከ ስብሐተ በእንተ ጸላኢ ከመትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ" "ከሕጻናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህልኝ፡፡ ስለ ጠላትና ቂመኛን ለማጥፋት"

ወንጌሉም፦ ዮሐ፭፥፲፩-፲፫
ቅዳሴ ፦ ዘጎርጎርዮስ (ነአኵቶ)[በዕዝል ዜማ]

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
742 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 01:06:30
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.4K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 22:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 01:06:30 መጋቢት ፳፱
በዓለ ወልድ (የጌታችን ጽንሰት)

መጋቢት ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የከበረ መልአክ ገብርኤል የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል፦  ኤልሳቤጥ ከፀነሰች በኋላ በስድተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ።

የድንግሊቱም ስም ማርያም ነው። መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት። እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች።

መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።

እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም። 

ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው።መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም እነሆኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው።

ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል ወልድ ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ በቅድስት ድንግል ማርያም ማሕፀን አደረ ፅንስ ሆኖ ኖረ።

በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና። ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኵር ናት በእርሷም የዓለም ድኅነት ተጀምሮዋልና።

ዳመኛም በዚህች እለት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽንሰት በተጨማሪ የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፣የቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሐ፣ የቅዱስ ኢያሱ ነቢይ፣ የቅዱስ ላሊበላ፣ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጽንሰታቸው ታስቦ ይውላል፡፡

መጽሐፈ ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.4K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 22:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 09:16:52
መድኃኔዓለም ክርስቶስ
በቀራንዮ ስቁል(፪)
በለኒ መሐርኩከ
በለኒ መሐርኩኪ
በእንተ ማርያም ድንግል።
እስመ ሔር አልቦ እንበሌከ ቃል(፪)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
624 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 09:16:52
"መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል።
በለኒ መሐርኩከ/በለኒ መሐርኩኪ በእንተ ማርያም ድንግል።
እስመ ኢኀሎ ሔር እንበሌከ ቃል።"

"ከአንተ (ከቃል) በቀር ቸር የለምና በቀራንዮ የተሰቀልህ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ! ስለ ማርያም ድንግል (ስለ እናትህ) ብለህ ምሬሀለሁ/ምሬሻለሁ በለኝ።"
(መልክአ መድኃኔ ዓለም)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
606 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 09:16:51 የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ይስሐቅ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ያዕቆብ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮብ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሙሴ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳዊት ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤርሚያስ ‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅኤል ‹‹አምላክ ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳንኤል ነጭ ሐር ለብሶ ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤልያስ ከሞት በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅያስ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ምናሴ ችንካሮችህን ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮስያስ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ከእሳት ምድጃ ያዳናች የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አብያና ሲላ ፌንቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አሞፅ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዘካርያስ በተራራዎች መካከል ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዕዝራ በአርፋድ በረሃ ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ስምዖን በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዮሴፍ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ኢያቄምና ሐና ሆይ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ያላችሁ ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ፣ አንድ ልጇ ሙቷልና፡፡ የለመለመ የሥጋ ሞት ሕንፃ የተጀመረበት የአቤል ተከታዩ፣ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ሔዋንን ከጥፋት ያዳናት የተገደለ መድኃኒታችን ነው፡፡ የናቡቴ ጓደኛው የተገፋው መድኃኒታችን ነው፡፡ አቤል ስለሚስቱ ሞተ፡፡ ናቡቴም ስለ ወይኑ ቦታ ሞተ፡፡ መድኃኒታችን ግን በቀኙ ያነጻት ዘንድ ስለቤተክርስቲያን ሞተ፡፡ ነፍሳችሁን ይወስዷታልና መውረዱንም አላወቁምና ስለ ወገኖቹ ኃጢአት እስከ ሞት ደረሰ ብሎ ስለ እርሱ የተናገረ አባቱን እንስማው፡፡ ሙሴም እርሱን ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፣ በሚመጣበት ቀንም አላወቁትም አለ፡፡ ዕዝራ በባሕር ጥልቅ ያለውን ማወቅ እንዳይችሉ ወልድንም ማወቅ እንዲሁ ሆነባቸው አለ፡፡ ጳውሎስም ብታውቁትስ ኖሮ የክብርን ጌታ እግዚአብሔርን ባልሰቀላችሁት ነበር አለ፡፡

በመሰደድ፣ ያለምንም በደልም በፍርድ አደባባይ በመቆም መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣ አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ኑ፡፡

‹‹የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደጻፈልን (1ኛ ጴጥ 2፡21) እርሱ ንጹሕ ባሕርይ ሲሆን ወደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ለተጠመቅን ለእኛ ለተነሣሕያን ለሁላችን አብነት የሆነን መድኃኒታችን ስለእኛ ሞቷልና ሞቱን እናስብ ዘንድ ኑ በቤቱ ተሰብስበን እናልቅስለት፡፡ መታሰያውንም እናድርግለት፡፡ ጌታችን ሞቶ ተቀብሮ ካረገ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳን አባቶቻችን ለእነ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ለእነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደነገራቸው የሞቱን መታሰቢያ የሚያደርግ ኃጠአተኛ እንኳ ቢሆን ሲኦልን አያያትም፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ሲኦል ራሷ አፍ አውጥታ ‹‹ይህችን ነፍስ ወደኔ አታምጡብኝ›› ብላ ትጮሃለች እንጂ ችላ አትቀበለውም፡፡

የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በድርብ በፍታና በመቶ ወቄት ሽቱ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ሊቀብሩት ቢሉ ጌታችን ያን ጊዜ ዐይኑን ክፍቶ ‹‹በሰውነቴ መዋቲ ብሆን በመለኮቴ ሕያው ነኝ እንጂ ምነው እንደ እሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ ትገንዙኛላችሁን?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜም ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በታላቅ ድንዳጤ ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ! እንግዲያስ ምን እያልን እንገንዝህ?›› አሉት፡፡ መድኃኒታችንም እንዲህ እያላችሁ ገንዙኝ አላቸው፡- ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ› እያላችሁ ገንዛችሁ ቅበሩኝ አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለወዳጆቹ ለ12ቱ ሐዋርያት፣ ለ72ቱ አርድእት፣ ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡

ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡
የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
462 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 09:16:51 መጋቢት ፳፯
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ


መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደሲኦል ወረደች።

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት በሥጋ ተሰቅሏልና ሞቱን በአንክሮ እናዘክር ዘንድ የልቡናችን ዐይን ወደ ቀራንዮ እናንሳ! እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን ልባቸውን አስቶታልና እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደመርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንስተው ‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው በራሱ ላይ ደፉበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በ73ቱ ስቁረት አግብተው በጌታችን በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊለ ሦኩን በራሱ ላይ አድርገው ሲያበቁ ከቤት ወደ አደባባይ እያመላለሱ ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ ከዚህ በኋላ ክፉዎች አይሁድ ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸው ደግሞ እንደ ወስፌ የሆኑ 5 ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡

ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለም ክርስቶስን እንደያዙት የኋሊት አስረው አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ አስረው የፊተኞቹ ሲጎትቱት የኋለኞቹ እየለቀቁት የኋለኞቹም በተራቸው ሲጎትቱት የፊተኞቹ ይለቁታል፡፤ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውል በእግሩ ሲረግጠው ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ስለዚህ ንግግርህ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡

ክፉዎች አይሁድ መድኃኒታችንን በሁለት ግንዶች መካከል አድርገው 65 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡ ቀያፋ በሚመረምረው ጊዜ ጌታችን ‹‹አምላነቴን አንተው ራስህ ተናገርኽ›› ቢለው አይሁድ በእጃቸው ሲመቱት እጃቸውን ቢያማቸው ድንጋይ ጨብጠው 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡ አይሁድ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ሲወስዱት ‹‹ምናልባት ጲላጦስ ባይፈርድበት እንኳ እንዳይቆጨን›› ብለው 305 ጊዜ በሽመል ደብድበውታል፡፡ በአምላክነቱ ቻለው እንጂ የአንዱ ምት ብቻ በገደለው ነበር፡፡ በርባን የይሁዳ የሚስቱ ወንድም (አማቹ) ስለነበር እርሱ እንደፊታለትም ከዋጋው ከ30ው ብር ጋር አብሮ ተደራድሮበት ነበር፡፡
ሰይጣን ልባቸውን ለክፋት ያስጨከናቸው ክፉዎች አይሁድ በጲላጦስ አደባባይ የጌታችንን ፂሙን 80 ጊዜ ነጭተውታል፡፡ ጲላጦስ እንደ ሕጋቸው 41 ብቻ ገርፈው እንዲለቁት ቢያዝም ክፉዎች አይሁድ ግን ጌታችንን ሲገርፉት ‹‹አሠቃቂ ግርፋቱን አይተን ልባችን እንዳይራራ›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሰርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነስቶ እስከ 60 እና 70 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደዛኛው ሁሉ በተራው 60 እና 70 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡

የመድኃኔዓለም ወገኖች ሆይ! የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡

ዳግመኛም በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ (ዮሐንስ ወንጌል ላይ ምዕራፍ 18 ከቁጥር አንድ ጀምሮ ይመለከቷል፡፡) እናም የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ ባጠፋቸው ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ጌታችን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡

ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡

በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን ሙቷልና፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሔር ‹‹በሴም ቤት ይደር›› ብሎ አብ ስለራሱ የተናገረለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አብርሃም ቃልኪዳን የገባልህን
500 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 21:54:04 "ኒቆዲሞስ"
በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

ኒቆዲሞስ/፪/ክቡር፣/፪/
ለሊቱን በብርሃን የሚማር መምህር፣/፪/

በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ፣
በመከራው ጽናት ይህን ዓለም ናቀ፣
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ፣
የትዕቢትን ጅረት : በትህትና : ተዋርዶ አደረቀ።

°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ፣
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የዓቢ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°

ፍርሀትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ፣
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ፣
የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ፣
ከመቅደሱ አንቀጽ : ላይረሳ : አምድ ሆኖ ታጠረ።

°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ፣
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የዓቢ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°

ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች፣
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች፣
ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች፣
እንደ ኒቆዲሞስ : ነፍስህም : ተምራ ተመለሰ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ፣
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የዓቢ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
950 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 21:53:44
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
853 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 21:53:44 ኒቆዲሞስ
የዐብይ ጾም ሰባተኛ እሑድ(ሳምንት)


ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የነበረው ሰው ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ምልክት አሳየን›› እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ጌታችን ስለ ሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ እያስረዳ ቢያስተምራቸውም እነርሱ ግን አልገባቸውም ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ጌታችን በተአምራቱ የታመሙትን ሲፈውስ
‹‹ሕጋችን ተሻረ›› ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ዅሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ቢፈራ፣ አንድም ጊዜ ባያደርሰው እንደ ባልንጀሮቹ ክርስቶስን ሳይቃወም በሌሊት ወደ ጌታችን ዘንድ እየሔደ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ፣ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ ኒቆዲሞስ ሰምቶ፣ ተመልክቶ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ከጌታው፣ ከመምህሩ ከክርስቶስ ዘንድ በሌሊት ይገሰግስ ነበር (ዮሐ. ፫፥፩)፡፡ ምስክርነቱንም እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ፤
‹‹መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከኾነ
በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል
የለምና፤›› (ዮሐ. ፱፥፳፬፤ ሐዋ. ፲፥፴፰)፡፡
ይህን ምስክርነቱን በሚሰጥበት ጊዜም ጎዶሎን የሚሞላ፤ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፤ ከምድራዊ ዕውቀት ወደ ሰማያዊው ምሥጢር የሚያሸጋግር አምላክ ‹‹ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን
መንግሥት ለማየት አይችልም፤›› በማለት የአይሁድ መምህር ለኾነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ
ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ
ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?›› በማለት ጥያቄ አቅርቧል (ዮሐ. ፫፥፮፤ ፩ኛጴጥ. ፩፥፳፫)፡፡
‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ
ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ
አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም
የተወለደ መንፈስ ነውና፤›› (ኤፌ. ፭፥፳፮) በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ቢያስረዳውም ምሥጢሩ ከአቅሙ በላይ ስለ ኾነበት እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡
አበ ብዙኃን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ ለመማለድ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምሥጢር ከአምላኩ በጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስም፡- ‹‹አንተ የእስራኤል
መምህራቸው ኾነህ ሳለ ይህን ነገር አታውቅምን?
በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁ በሰማይ
ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ
ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም …
ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ
እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመነበት ዅሉ ለዘለዓለም ሕያው ኾኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም ...፤›› እያለ ሰው በመብል ምክንያት የአምላኩን ትእዛዝ አፍርሶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ፣ ስመ ክርስትናን፣ ሀብተ ወልድን ለመስጠት ጌታችን መምጣቱን አስረዳው (ዮሐ. ፫፥፲፬)፡፡ ይህን የክርስቶስን የማዳን ሥራና በሥጋ መገለጥም
‹‹ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ
ወኢተረከ ዐመፃ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ
እጓለ እመሕያው፤ ልቤን ፈተንኸው፡፡ በሌሊትም
ጐበኘኸኝ፤ ፈተንከኝም፡፡ ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን
ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤›› (መዝ. ፲፮፥፫) በማለት ቅዱስ ዳዊት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማዛመድ አመሥጥሮታል፡፡
በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሔዶ መማርን ይፈራ እንዳልነበረ ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ፡፡ ‹‹ወአልቦ ፍርኃት
ውስተ ተፋቅሮትነ፤ ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ
ይጥላል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፯፥፶፰፤ ፩ኛዮሐ. ፬፥፲፰)፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ፣
ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል›› (ማር. ፲፮፥፮) በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንኾን ዘንድ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

 በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-ሮሜ ፯፥፩-፱
-፩ኛ ዮሐ ፬፥፲፰ እስከ ፍጻሜ
-የሐዋ ሥራ ፭፥፴፬ እስከ ፍጻሜ

ምስባኩም፦ መዝ ፲፮፥፫
"ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመጻ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለእመሕያው"
"ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘህብኝም የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው"

ወንጌሉም፦ ዮሐ ፫፥፩-፳

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
899 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ