Get Mystery Box with random crypto!

ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም: ተነስቷል በዚህ የለም(2): መድኃኔዓለም ሞት | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም:
ተነስቷል በዚህ የለም(2):
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ:
ኃያል ነው ማይረታ ማኅተሙን የፈታ:
የትንሳኤው ጌታ።
*አዝ*
ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና:
ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው በበገና:
ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን ምንዘምረው:
መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው :
ዳንን የምንልው።
*አዝ*
ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘለዓለም:
በመቃብር ሞት ይይዝህ ዘንድ ከቶ አልቻለም:
ኃይለኛውን በኃይል አስረኸው ላይፈታ:
ዘመርንልህ አሸናፊ ነህ የእኛ ጌታ:
ከፍ በል በእልልታ።
*አዝ*
ሞቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር:
ጌትነትህ ሥራህ ይኖራል ሲመሰከር:
ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ:
ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጠላት ፈራ:
ዕፁብ ያንተ ሥራ።
*አዝ*
መስክሩለት የምስራች ነው ታላቅ ዜና:
መላዕክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና:
ከተማዋ አንዳች ሆናለች በለሊቱ:
በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወኅኒ ቤቱ:
ከበሮውን ምቱ።

በዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox