Get Mystery Box with random crypto!

'ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!' ይህ ሰላምታ ለሃምሳ ቀናት ይዘልቃል። የዚህ ሰላምታ ልውውጥ ታሪክ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!"

ይህ ሰላምታ ለሃምሳ ቀናት ይዘልቃል። የዚህ ሰላምታ ልውውጥ ታሪክ የሚጀምረው ከመጀመሪያዋ ምዕተ ዓመት ከነበረችው ከጥንት ክርስቲያኖች ጀምሮ ሲሆን ለትንሳኤ በዓል ብቻ ሳይሆን ሁሌም ሲገናኙ አይሁዳውያን "ሻሎም" ወይም ሰላም ብለው ሰላምታ እንደሚለዋወጡት ሁሉ ክርስቲያኖቹም "ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል" ብለው ሰላምታ ሲሰጡ መላሹ ደግሞ "በአማን ተንስአ እሙታን ፤በእውነት ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል" በማለት ይመልሳል።

ይህ ሰላምታ በሁሉም በምስራቁም በምዕራቡም ኦርቶዶክሳውያን ብሎም በአንግሊካንም ቤተክርስቲያን ከትንሳኤው ጋር የፋሲካ ሰሞን ሰላምታ እንደሆነ ቆይቷል። አሁንም የሚተገበር ሰላምታ ነው። ነገር ግን መቼ እንደሆነ ባይታወቅም ሰላምታው ከዘወትር ሰላምታ ወደ ዘመነ ፋሲካ ብቻ ሰላምታ ተለወጠ።

በምዕራቦቹ ክርስቲያኖች ሰላምታ ሰጪው Christ is Risen!" ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ወይም "The Lord is Risen!" እግዚእ ተንስአ እሙታን ሲል ሰላምታ መላሹም "Truly, He is Risen," በአማን ተንስአ፤በእውነት ተነስቷል "Indeed, He is Risen," ወይም በእርግጥ ተነስቷል "He is Risen Indeed እርግጥ ነው ከሙታን ተነስቷል ይላል።
Christ is Risen!" or "The Lord is Risen!", and the response is "Truly, He is Risen," "Indeed, He is Risen," or "He is Risen Indeed.

ይህ ሰላምታ ከሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት የእኛ ቤተክርስቲያን የሚለየው ረዘም ብሎ "ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ ዓግአዞ ለአዳም፤ ሰላም፤ እምይእዜሰ፤ ኮነ ፍሰሀ ወሰላም በማለት በጥልቅ ሚስጢር ሰላምታ ላይ ይውላል።

በዚህም የሀገርኛ ነገረ ክርስቶስ ትምህርት (Ethiopic Christology)እድገትን አንድ ማሳያም አድርገን መውሰድ እንችላለን። የጌታ ሞትና ትንሳኤ በቤተክርስቲያን ታሪክም ይሁን በነገረ መለኮት አስተምህሮ እድገት(Development of theological teachings) ትልቁን ስፍራ ይይዛል። በስልታዊ ነገረ መለኮት (Systematic Theology) ትምህርት ውስጥ "ዶግማ አይቀየርም ነገር ግን ያድጋል" የሚባለው ለዚህ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ በ367 ዓ.ም በዛሬዋ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፈው ቃለ ምዕዳን (ልፋፈ ጽድቅ) በ45ኛ ደብዳቤው የኦርቶዶስክ ቤተክርስቲያን በቀኖና የምትቀበላቸውን በዝርዝር 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍትን መሆኑን ያወጀበት ቀን ነው። ከዚያም ወደ ሁሉም መንበረ ፕትርክናዎች (Patriarchate) ልኳል።

Priest : Christ is risen from the dead!
ካህን : ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
People : By the highest power and authority!
ሕዝብ : በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
Priest : He chained Satan!
ካህን : አሰሮ ለሰይጣን!
People : Freed Adam!
ሕዝብ : አግዐዞ ለአዳም!
Priest : Peace!
ካህን : ሰላም!
People : Henceforth!
ሕዝብ : እምይእዜሰ!
Priest : Is!
ካህን : ኮነ!
People : Joy and Peace!
ሕዝብ : ፍስሐ ወሰላም

መልካም በዓል!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox