Get Mystery Box with random crypto!

በሐሰተኛ አጥማቂያን ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ተጠየቀ፡፡ በ41ኛው የመንበረ ፓትር | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በሐሰተኛ አጥማቂያን ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ተጠየቀ፡፡

በ41ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የውሳኔ ሃሳብ እና የአቋም መግለጫ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈበት ወቅት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተደብቀው መዋቅሯን በመጠቀም የራሳቸውን የግል ፍላጎት ለማርካት የሚጥሩ ቢጽ ሃሳውያን አጥማቂ ነን፣ የዓለም ብርሃን ነን በሚሉ እና በልዩ ልዩ ስያሜ በየአህጉረ ስብከቱ ባሉ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን አዳራሾች ምእመኑን ግራ በሚያጋቡ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥናት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡

አጠቃላይ የጉባኤው የውሳኔ ሃሳብ እና የአቋም መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ጥንታዊት ታሪካዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ችግሮች ለመፍታት እና በተለይም መሠረታዊ ተልእኮ የሆነውን ስብከተ ወንጌልን በተገቢው መንገድ በማስፋፋት፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በምእመናኖቻችን መካከል ግንዛቤ አግኝተው ይበልጥ እንዲደራጅ፣ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች በሃይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉና የነገዪቱ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ እንዲሆኑ፣ በልማቱም አቅጣጫ ለህብረተሰቡ ሁሉ ግንባር ቀደም ምሳሌ ሆና የልማት ውጤት ለማሳየት የቤተ ክርስቲያን የገቢ ምንጭ ከመፍጠር ጋር ገቢዋ ወቅታዊና ዘመናዊ በሆነ የአመዘጋገብ ስልት ለመጠበቅ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ት/ቤቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ከማዕከል እስከ አጥቢያ ያለው የቤተ ክርስቲያን ግንኙነት ካለፈው ጊዜ ይልቅ ወደፊት የተሻለ እንዲሆን፣ በተለይም ማንኛውም መንፈሳዊም ሆነ ዘመናዊ እንቅሳቃሴ ከግቡ ለማድረስ ለዚህም በቤተ ክርስቲያናችን ያለው የመልካም አስተዳደር ሥራ እንዲፋጠን ለማድረግ በዚህ 41ኛ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ጉባኤ በተሰጡ ትምህርቶች እና በተደረጉ ውይይት ግንዛቤ ተወስዷል፡፡ በመሆኑም
1. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በውጭ ሀገር እና በተለይም በሀገር ውስጥ ያከናወኑት መንፈሳዊ፣ ሐዋርያዊ እና ማኅበራዊ ተልእኮ ይልቁንም በሀገር ላይ የደረሰውን የሰላም እጦት፣ የኑሮ ውድነት፣ የወረርሽኝ በሽታን አስመልክቶ ያለመታከት ሀገርና ሕዝብን ለማረጋጋት ያከናወኑት የሰላም ተልእኮ ቤተ ክርስቲያናችን ክብሯ ሰላሟ እና አንድነቷ እንደተጠበቀ እንዲኖር በማረጋገጥ አባታዊ አመራር ያከናወኑበት በጀት ዓመት በመሆኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ልዕልና ብቻ ሳይሆን የሀገራችን ኢትዮጵያንም ክብርና ሀገረ እግዚአብሔርነትን ያንጸባረቀ በመሆኑ ጉባኤው በታላቅ አድናቆት በሙሉ ልብ ተቀብሎታል፡፡
2. የቤተ ክርስቲያናችን 4ኛው ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የሽኝት እና የቀብር ስነ ሥርዓት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት የተከናወነ ሲሆን በሥርዓቱ ላይ ክብርት የኢፌዴሪ ፕሬዘደንት ሣህለ ወርቅዘውዴ የአበባ ጉንጉን ማኖራቸው፣ ክቡር የኤፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) በሰጡት ጥብቅ አመራር የቅዱስነታቸውን የሽኝት ፕሮግራም በደመቀ ሥነ ስርዓት ከመካሄዱም ሌላ የፌደራሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸው ለተካሄደው የሽኝት ሥነ ስርዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ ለሰጡት አመራር በአጠቃላይ ከተማ አስተዳደሩ ላደረገው አጠቃላይ ድጋፍ ከቤተ ክርስቲያናችን ምሥጋና ማግኘቱን በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ሪፖርት ተካቶ የቀረበውን ጉባኤው በምልዓት በአድናቆት ተቀብሎታል፡፡
3. ቤተ ክርስቲያን የሚፈለግባትንና ጊዜው የሚጠይቀውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ተልእኮ እንድትወጣ ለማስቻል የሚያዝ ጠንካራ የአስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት እንዳለባት ወቅቱ የሚጠይቀው ነው፡፡ በመሆኑም እስካሁን የተገለጸው የመሻሻል ጅምር በመሆኑ ጉባኤው ተገንዝቧል፡፡ ቢሆንም እያንዳንዱ መምሪያና ተቋም የበላይ አካል ክትትል ሳይለየው ራሱን ችሎ ኃላፊነቱን በተጠያቂነት ሲወጣ ባለመታየቱ መልካም አስተዳደርን በማስፈን ጭምር የተቀላጠፈ ፍትሕና ርት የተመላ አስተዳደር ይታይ ዘንድ ማንኛውም መንፈሳዊም ሆነ ዘመናዊውን እንቅስቃሴ ከግቡ ለማድረስ መልካም አስተዳደር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በመሆኑ የሥራ ቦታዎችን በመልካም አስተዳደር እና አቅም ግንባታ የተደራጁ እንዲሆኑ፤ ሥራ እና ሠራተኛን በማገናኘት እንዲሠራ በመጠየቅ ጉባኤው በጎ ሐሳቡን ለግሷል፡፡ በመሆኑም የሥራ ተነሳሽነት ያለው ከተገልጋይነት ይልቅ አገልጋይነትን እንዲሁም ግልጽነትን ተጠያቂነትንና ታማኝነትን መርህ ያደረገ መልካም አስተዳደር እንዲጠናከር ተግተን እንሠራለን፡፡
4. የሰበካ ጉባኤ መጠናከር የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና ዋስትና ከመሆኑም በላይ በሮቿ ተከፍተው አምላክ አደራዋን ሕዝባዊ አገልግሎቷን ለመፈጸም የቻለችበት ህያው ተቋማችን መሆኑን ከልባችን ስለምናምን የማደራጃ መምሪያው ክትትልና ግምገማ ሳይለየን ከብፁዓን አባቶች ቡራኬና አመራር እየተቀበልን ከፍተኛ የሥራ ውጤት ለማስገኘት እያንዳንዷ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋ እና መብቷ ተጠብቆ አስተዋጽዖውን በማሳደግ ግዴታዋን መወጣት ትችል ዘንድ በስብከተ ወንጌል መንፈሳዊ መሳሪያነት ከፍተኛ የመመካከር እና የማሳመን ተልእኳችንን ለመወጣት ቃል ገብተናል፡፡
5. ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በጉባኤው መክፈቻ ባሰሙት ቃለ ምዕዳን የሰበካ ጉባኤ አመሠራረት እና ጉዞ አሁን ያለበት ደረጃ ትክክል ነው ወይስ የሚቀረው አለ? የቀረው ካለስ ለምን አናስተካክለውም? ለወደፊትስ የሰበካ ጉባኤ ሀብተ በረከት እንደሚፈለገው በፍጥነት አድጎ ለሕዝቡ ተደራሽ እስከሚሆን ለምን አናደርሰውም? በሚል ትክክለኛና ሙያዊ ጥናት ተካሂዶ የማሻሻል ሥራ እንዲሠራ ያስገነዘቡትን ጉባኤው በምልዓት ተቀብሎ በሥራ እንዲተረጎም እያሳሰበ ለተግባራዊነቱም የየድርሻችንን ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡
6. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕልውናዋ ከታወቀበት ዘመን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በትምህርት በኩል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረገችው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ሐዋርያዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በሙሉ ሊፈጸም የሚችለው ከአብነት ት/ቤት ከሚገኝ የእውቀት በረከት ነው፡፡ የአብነት ት/ቤቶች በብዛት የሚገኙት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በመሆኑና ለእነዚህም በቂ በጀት አለመመደቡና ይልቁንም በአብዛኛው አህገረ ስብከት ት/ቤቶች አለመኖራቸው ት/ቤቱ ባለበትም ቢሆን ትምህርቱ ወቅታዊና ዘመናዊ በሆነ መልኩ ካለመካሄዱም በላይ ለስብከተ ወንጌል ት/ት ትኩረት አለመሠጠቱ በጉባኤው ተወስቷል፡፡ በመሆኑም የአብነት ት/ቤቶቻችን ከዕውቀት እንዳይነጥፉ፤ መናብርተ ጥበብ የሆኑ ዐይናሞችም መምህራን ማስፈለጋቸው አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ለመምህራኑ በአሁን ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ታስቦበት እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ የሚያበረታታ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ይሁን እንጂ የቤተ ክርስቲያኒቱን የአብነት ት/ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን የመጽሐፍት ኪራይ ክፈሉ፣ የምግብና የልብስ ዋጋ ስጡ ሳይሉ አደራቸውን እየተወጡ የሚገኙ ናቸው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን መምህራኑ የሚሰጡት አገልግሎት በጥልቅ ሲገመገም በመንግስተ ሰማያት ካልሆነ በስተቀር በዚህ ዓለም ላይ ዋጋው ይህን ያህል ነው ብሎ መገመት ያዳግታል፤ ምሥጋናውም ቢሆን ሲያንሳቸው ነው፤ ከምሥጋናም በላይ ሌላ ቃል ካለ ለእነሱ ይገባል