Get Mystery Box with random crypto!

የስደት ዘመንሽ መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣ ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ። በጠላት | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የስደት ዘመንሽ

መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣
ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ።

በጠላት ፈተና ከሀገር ተሰደሽ፣
ስትንከራተቺ አምላክን ታቅፈሽ፣
ከገሊላ አንስቶ እስከ ግብፅ በረሃ፣
የሚያዝንልሽ አጣሽ የሚሰጥሽ ዉኃ።
            አዝ
ሰሎሜ ትመስክር ያየሽውን ጭንቀት፣
ዮሴፍም ይናገር የሀዘንሽን ብዛት፣
እመቤቴ ማርያም ከአንድ ልጅሽ ጋራ፣
 በግብፅ በረሃ ያየሽዉ መከራ።
            አዝ
  ውርጭና ፀሓዩ ሲፈራረቅብሽ፣
  ረሀብና ጥሙ እንዲያ ሲያንገላታሽ፣     
  በለጋነት ዕድሜ በሄሮድስ ቅናት፣
  ከልጅሽ ጋር አየሽ መከራ ስደት።
            አዝ
   ልጅሽ አንዲምረን ስለእኛ እንዲራራ፣
   ለበረከት ሆነ ያየሽው መከራ፣  
   መልካም ፍሬ አፈራ ያነባሽው ዕንባ፣
   ምክንያት ለእኛ ሆነ ገነት እንድንገባ።
   
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox