Get Mystery Box with random crypto!

የጌታዬ እናት የጌታዬ እናት ማርያም የበረከት ምንጭ የሠላም መከራው በዝቶ ተጨንቀናል ድን | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የጌታዬ እናት

የጌታዬ እናት ማርያም
የበረከት ምንጭ የሠላም
መከራው በዝቶ ተጨንቀናል
ድንግል ነይልን ተማፅነናል

አ. ዝ------------------

ቀባሪ ሲያጡ አዛውንቱ
ሜዳ ሲወድቁ ህፃናቱ
እሳት ሰደዱ እንዲቆም

አማልጅን ድንግል ማርያም

አ.ዝ------------------

የራቀው ሰላም እንዲቀርበን
ፍቅር አንድነት እንዲከበን
ከልጅሽ ጋራ ነይልን
ኑሮአችን መልካም እንዲሆን

አ.ዝ------------------

ውሃ የሌለው ምንጭ ሆነናል
መሬት ታቅፈን ዘር አጥተናል

የኢትዮጵያ እናት እመቤት
ሁሉን ባርኪልን በረድኤት

አ.ዝ------------------

ድፍረት ጭካኔ አመፅ ሞልቷል
በጎ ደግ ሰው ከሃገር ጠፍቷል

ማን መልካም ነገር ያሳየናል
ወደ ማደሪያሽ አቅንተናል

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox