Get Mystery Box with random crypto!

ድንግል ድንግል ወላዲተ ቃል (2x) አሟሟትሽ በጥር ነሐሴ መቃብር ድንግል ያንቺስ ለብቻው ነው ት | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ድንግል ድንግል ወላዲተ ቃል (2x)

አሟሟትሽ በጥር ነሐሴ መቃብር ድንግል
ያንቺስ ለብቻው ነው ትንሣኤሽ ሲነገር ድንግል
ሥጋሽ በምድር ላይ የታለ እንደ ፍጡር ድንግል
አርጓል ወደ ሰማይ ከክርስቶስ መንበር ድንግል

ድንግል ድንግል ወላዲተ ቃል(2x)

ሥጋሽን ሲያሳርጉ መላእክተ ሰማይ ድንግል
ቶማስ በደመና ሲመጣ መንገድ ላይ ድንግል
መግነዝ ተረከበ ለሐዋርያት ሊያሳይ ድንግል

ድንግል ድንግል ወላዲተ ቃል(2x)

ትንሣኤሽን ሽተው ግራ ሲገባቸው ድንግል
ሐዋርያት ጾመው ተገለጥሽላቸው ድንግል
ተቀብራ አልቀረችም በምድር በደጇ ድንግል
ወደ ላይ አረገች እሷም እንደ ልጇ ድንግል

ድንግል ድንግል ወላዲተ ቃል(2x)

ለማየት ሲጓጉ የድንግልን ትንሣኤ ድንግል
እርገቷን አወቁ በብዙ ሱባኤ ድንግል
እኛም እንጸልይ ደጃችን እንዝጋ ድንግል
ከወላዲተ አምላክ እንድናገኝ ዋጋ ድንግል

ድንግል ድንግል ወላዲተ ቃል(2x)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox