Get Mystery Box with random crypto!

አሮጊቷ አገሬ... (ታደሰ ደምሴ) ድሮ... ያልተማሩ ምሁር በእንዝርት እየዳጡ በጥበብ ሸመኑሽ ል | ታደሰ ደምሴ

አሮጊቷ አገሬ...
(ታደሰ ደምሴ)

ድሮ...
ያልተማሩ ምሁር በእንዝርት እየዳጡ በጥበብ ሸመኑሽ
ልዕልናሽን ሽተው፣
ክብርሽን አግዝፈው፣
በጽኑ ክንዳቸው ማማ ላይ ሰቅለውሽ!
ቅጽርሽ ሳይደፈር እልፍ ዘመን ዋጀሽ!

ከዛማ በኋላ ...
ስምሽ ሲቀማጠል
ዘመን ሲቀባበል
የሆነ ወቅት ላይ ከጊንጥ ተዛመድሽ
ከጊንጥ ተጋባሽ
ከመልክሽ ያልመጣ ተኩላ ቢጤ ወለድሽ!

ከዛማ በኋላ...
አንቺም እንደሰው ፊት ወረት ወግሽ ሆነ!
የወለድሽው ድቃይ፣
ፈቃድሽን ተችሮ በምድርሽ ዘመነ!
ከእልፍኝሽ አዳራሽ በወግ ሰለጠነ!

ከዚያን ቀን ጀምሮ...
ጠቦቶቻቸውን የተቀሙ ሁሉ ለክስ ሲወጡ
በቀበሮ ችሎት፣
በእከከኝ_ልከክህ በጎችሽ ፍርድ አጡ!

ይሔው...
እልፎች ተሰውተው
ስጋ ደም ገብረው
በአጥንታቸው ካሳማ ማማ ላይ ቢሰቅሉሽ
ዘመን ያመጣቸው፣
ወረት የሾማቸው፣ ዲቃላ ልጆችሽ
ካስማሽን ነቅንቀው ዘጥብያ አወረዱሽ!

ይበልሽ...!
ይበልሽ...!
ከማ'ፀንሽ ወጥቶ ለሞትሽ የሚሞት አብራክ ሳይቸግርሽ
በአመንዝራ ቅሌት መርዛም ገላ ታቅፈሽ ማን ተጋደሚ አለሽ!

እይልኝ ጉድሽን...
"እረኛ ሁን" ያልሽው ከእሪያነት ያነሰ
ከበላተኞች ጋር መንጋውን ጨረሰ!

ይብላኝለት ለዛ...
ሙሴ ላጣው ህዝቤ ዘመን ላኮረፈው
በጅል የቅናት ፍሕም ለሚለበለበው!

ይብላኝነት ለዛ...
ህግ ባለባት ሀገር
"በህግ አምላክ" ብሎ ጮሆ ላልተሰማ
በስልጣን ጥማት ጦስ፣
ከቀየው ለሚጋዝ፣
በመከራ ገፈት ነፍሱን ለሚቀማ!

ይብላኝነት ለዛ....

#ሼር

@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123