Get Mystery Box with random crypto!

' Filter ያልነካቸው ' ኤልያስ ሽታኹን (የልደት ዳር ጨዋታ) ~ ~ ~ | ታደሰ ደምሴ

" Filter ያልነካቸው "
ኤልያስ ሽታኹን
(የልደት ዳር ጨዋታ)
~ ~ ~ ~ ~
እንደክርቶስ ሐሙሴ ይመጣል::
"ይቺ ነገር ትለፈኝ "የምልበት ::
ደመም ላብም ብቻዬን የማፈስበት::
የአትክልት ስፍራው ከኤርታሌ ብሶ የሚያቃጥለኝ ቀን አለኝ::

እስከዛው ትርካ ....

አምዳምነቴ ልክ አልነበረውም::

እንዚህ ቀናቶች ለሰው የገረጡ ለኔ ግን ያጌጡ ናቸው::
አራት ኪሎ
- የሰካራም ልጅ የተባልኩበት
- የድሀ ልጅነቴ ስታይ የማስታውቅ እኔ
- ጉልበተኛ ሀብታም ጎረቤት
- ዉኃ የሚነጠባጠበት ቤት
- የልጅነት ፀብ (አንዳንዶች አርጀተውም እኔን ለማሳፈር ይመዙልኛል)"እንዲህ ብለህ ነበር"ይላሉ
- ፅዋ ማህበር (አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ)
- ውድድር
- ትልቅ ህልም ትንሽ አቅም
- መጨረሻቸው ለሊት የሆኑ ወኮች
- የክበብ ሽኩቻዎች
- ጅንጅና ስልት ንድፎች
- ያወቁትን ቤት መጥቶ ማውራት (ጥሩ ቦታ ነው የሚውለው እንዲባል)
- ከእኩዮች ጋር አንድ አይነት ፋሽን መስራት....

ይሄ ሁሉ በህሊናና በልብ የቀሩ ማስታወሻዎች ናቸው::
ዛሬ ደሞ ለሰው ውብ ለራስ ግን ኮሽኳሻ ናቸው::

- ገላዬ ቆሽሾ በድንጋይ እህቴ ታላቅ እህቴ (ደርግ በሏት) ብረት ምጣድ ላይ እያጋጨች ፈተገችኝ::

"ማንን ለማሰድብ ነው" እያለች::
ጎረቤት አይሰማት ሰደበችኝ::
"ሰፈሩ እንደሆነ ቡዳ ነው"
"እኔ እኮ..."ላስረዳ ስሞክር ወኃውን ሳየው ጠቁሯል:: እድፌ ጭቃ ያህል ወፍራም:: ዝም ::

“ደሞ ባንተ እንሰድብ ወይ”
(“ድው” ከብረት ምጣድ ጋር ታላትመኛለች)
እልህ ዕንባ ነበራት:: አሁን ሳስባት ታሳዝነኛለች::

ምንበላው አልነበረንም ግን ስማችን አሳሰባት እና ጉልበቴ እስኪላጥ አሸችኝ::

ልክ እንደነዚህ ወዝም ደርዝም የሌለው የሚመስል እልፍ ቀን አለኝ

@ethiopia2123
@ethiopia2123