Get Mystery Box with random crypto!

የባከኑ ህልሞች መተኛት አልሻም ማለም እፈራለው ይሄን ያንን ሳስብ ሳልተኛ ነቃለው መናገር ያሰበው | ታደሰ ደምሴ

የባከኑ ህልሞች

መተኛት አልሻም ማለም እፈራለው
ይሄን ያንን ሳስብ ሳልተኛ ነቃለው
መናገር ያሰበው ለማይገባኝ ቅኔ
ማለምን አልሻም ያንች ወዳጅ እኔ
ከሁሉ ከሁሉ ፈራለው ምኝታ
ህልም ብሎ እያሳየ ስለነሳኝ ፋታ

ህልም ነው እያለ አንቺን ያሳይሻል
በቢጫ ቀሚስሽ ስትበሪ ይስልሻል
ፀጉርሽን ነስንሰሽ ስትስቂ ያመጣሻል
ግን ልነካሽ ሳስብ መልሶ ያጠፋሻል
እኔ አንችን ልነካ ሲቀረኝ በሳንቲ
ሚሰውርሽ ከቶ ምን ሊያገኝ ነው እስቲ

እናም ምኝታየን እፈራለው እኔ
ህልም ብሎ እያሳየኝ የማልፈታው ቅኔ
እሳቀቅ ጀመረ ቢያርቅሽ አቅርቦኝ
ፍራሽም መቃብር እንቅልፍም ሞት መስሎኝ
እናምልሽ ውዴ....
አሁን ላይ ሳስበው የፍራቴን ነገር
ለካ አንቺን ማግኘቱ ይበልጥብኝ ነበር

ሰሞኑን ስነሳ በሰላም ተኝቼ
ይናፍቁኝ ጀመር የባከኑ ህልሞቼ።

በአቤኒ የተጻፈ


@ethiopia2123