Get Mystery Box with random crypto!

#ቀን_ገንቢ ምዕራፍ ፩ : ክፍል ፪ ሁለት ዘሮች -------------- ሁለት ዘሮች ናቸው፡ | ታደሰ ደምሴ

#ቀን_ገንቢ
ምዕራፍ ፩ : ክፍል ፪


ሁለት ዘሮች
--------------


ሁለት ዘሮች ናቸው፡፡ በአካባቢው የተፈጠረ ንፋስ ከቅርፊታቸው ነጥሎ እያንሳፈፈ አጓጉዞ በላመ፣ በለሰለሰ አፈር ላይ ጎን ለጎን ቀላቀላቸው፡፡ ዘሮቹም ከለሰለሰ አፈር ላይ ማረፋቸውን በተረዱ ጊዜ በጉርብትና መንፈስ ውይይት ጀመሩ፡፡

አንደኛው ዘር፡ “በዚህ በእንደዚ ለመብቀን በተዘጋጀ ማሳ ላይ ሳርፍማ መብቀን እፈልጋለሁ፡፡ ሥሮቼንም ወደ ጥልቁ አፈር  በመላክ፤ ቅርንጫፎቼን ከምድር በላይ ከፍ አድርጌ እንደ ባነር በመዘርጋት የበልግ ወራት መድረሱን፤ ልምላሜ መምጣቱን ማወጅ ይገባኛል፡፡ የጠዋቷን ፀሐይም የተፈጥሮ ስጦጣየን መመገብ ይገባኛል እፈልጋለሁም፡፡” ሲል ሀሳብን ለባልጀራው ሰነዘረለት፡፡ እናም በቅሎ ማደግ ጀመረ፡፡

ሁለተኛው ዘርም በፈንታው እንዲህ አለ፡ መጀመሪያ ሀሳቡን ህምምም.. ሲል በመደመም ጀመረ፡፡ “ስሬን ወደ ጥልቁ አፈር ብለቀው በዛ ጨለማ ውስጥ ምን እንደሚገጥመኝ ከየት አውቅና ነው! ጉንቁሎቼን ባጎነቁልስ የቀንድ አውጣ ምግብ መሆኔ አይደለምን! እንዲሁም ደግሞ አበቦቼን ባፈነድቃቸው ህፃናቶች ቆርጠው ምድር ላይ በመጣል መጫዎቻ ያደርጉኛል፡፡ ስለሆነም ከዚህ ሁሉ የምጠበቅበት ምቹ ሁኔታ እስኪፈጠር መጠበቁ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም” ሲል የመብቀል የሕይወት ተልዕኮውን ገታው፡፡

ይህን ሀሳባቸውን ከተነጋገሩ ከሰዓታት በኋላ በአካባቢው ምግቧን ፍለጋ  ምድርን ስትጭር የነበረች ዶሮ ለመብቀል ምቹ ሁኔታን ሲጠብቅ የነበረውን ዘር አገኘችና ተመገበችው፡፡ ሥራን ለመስራት የማይመጣን ምቹ ሁኔታን መተበቅ ስራ እንዳንሰራ ከማድረግ ውጪ የሚፈጥረው ፋይዳ የለውም፡፡ እንቅፋትም እስከመጨረሻው ስለማየውቅ በዓለማችን እስካሁን ተሰሩ ወሳይኝ የሚባሉ ስራዎች በሙሉ በችግር ውስጥ እንጅ በተደላደለ ሁኔታ እንደልሆነ አብዛኛው መረጃ ይናገራል፡፡ There is no ideal condition for everything we can do what we have to do even in adverse condition. 

/ምስጋናው ግሸን/

#ሼር
@ethiopia2123