Get Mystery Box with random crypto!

#ቀን_ገንቢ ምዕራፍ ፩: ክፍል ፩ የራስ ዋጋ(አንብቤ ከወደድሁት የጋበዝኋችሁ) ---------- | ታደሰ ደምሴ

#ቀን_ገንቢ
ምዕራፍ ፩: ክፍል ፩


የራስ ዋጋ(አንብቤ ከወደድሁት የጋበዝኋችሁ)
------------

በአንድ ሰሚናር ውስጥ ሁለት መቶና በላይ ሰዎች በታደሙበት ታዋቂው ንግግር አድራጊ ተጋብዞ በቦታው ተገኝቷል፡፡ ተናጋሪው ለለቱ ማስተላለፍ የፈለገውን መልዕክት ለማጠናከር ያግዘው ዘንድ ንግግሩን የጀመረው የሃምሣ ብር ኖት በእጁ ይዞ በማሳየት “ከመካከላችሁ ይህን የሃምሣ ብር ኖት የሚፈልግ ማን ነው!?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ ታዳሚውም በተከታታይ ሁሉም እጁን አንድ ባንድ አወጣ፡፡ ተናገሪው ቀጠለ “ከመካከላችሁ ለአንዳችሁ መስጠት እፈልጋለሁ ነገር ግን ከዛ በፊት” አለና የሃምሳ ብር ኖቱን በእጁ በማፋተግ እንዲጨማተር ካደረገ በኋላ “አሁንስ የሚፈልገው ይኖራል!?” ሲል በድጋሜ ጥያቄ አቀረበ፡፡
አሁንም የታዳሚዎች እጅ እፈልጋለሁ በሚል ስሜት ተዘረጋ፡፡ በጣም ጥሩ አለ ተናጋሪው እንደዚህ ባደርግስ ብሎ የሃምሣ ብር ኖቱን እግሩ ሥር ጥሎ በጫማው ምድሩ ጋር ካፋተገ በኋላ አሁን “እደምትመለከቱት በጣም ቆሽሿል:: ተጨማትሯልም:: አሁንስ ትፈልጉታላችሁ!? አሁንም የፈላጊዎች እጅ በአንድነት ተነሳ፡፡ “ወገኖች አሁን በጣም ወሳኝና መሰረታዊ ትምህርት እንደቀሰማችሁ አምናለሁ፡፡ ምንም እንኳን ብሩ ላይ ማናቸውንም ነገር ባደርግበት፣ ባቆሽሸውም፣ ባጨማትረውም፤ ብሩን የራሳችሁ የማድረግ ፍላጎታችሁ እንዳለ ነው፡፡ አልቀነሰም፡፡ ምክንያቱም የብሩ ኖቱ ቢጎሳቆልም ቢጎዳም እንደ ብርነቱ የሚሰጠውን ዋጋ ወይም ጠቀሜታ አልቀነሰበትምና፡፡ እስካሁንም ዋጋው ያው ሃመሳ ብር ነው፡፡” አላቸው፡፡

ብዙውን ጊዜ በሕይዎት ውጣውረድ በምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ፣ በሚፈጠሩት ክስተቶች መውደቅ መነሳቱ፤ መደቆሱ ያለና የሚኖር ነው፡፡ በተፈጠሩት የህይዎት ፈታኝ ክስተቶች ዋጋ ያጣን ያህል ሊሰማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ምንም ይሁን ምን፣ ያለፍንበት የሕይዎት ጎዳና ምንም ያህል አባጣ ጎርባጣም ቢሆን እኛ ማለት እኛ ነንና የእኛነታችንን፣ የራሳችንን ዋጋ አናጣምም ማጣትም የለብንም ፡፡


#ሼር

@ethiopia2123