Get Mystery Box with random crypto!

እራሴን አፋልጉኝ (ታደሰ ደምሴ) የሐምሌ ወር ጉም ነኝ ... ያለሁ የምመስል አሻግሮ ለሾፈኝ ገመ | ታደሰ ደምሴ

እራሴን አፋልጉኝ
(ታደሰ ደምሴ)

የሐምሌ ወር ጉም ነኝ ...
ያለሁ የምመስል አሻግሮ ለሾፈኝ
ገመናየ ባዶ...!
ነፍስ የሌለው ነፋስ ባሻው እያጋዘ ባሻው የሚያተነኝ!
:
:
"ጋግረነዋል!" ያሉ፣
መብሰሌን ተስፋ አርገው እልፎች ሲጠብቁኝ
እንኳንስ ልጋገር፣
እንኳንስ ልበስል፣
ከ'ቧቃ ሳልደርስ ወፍ እብስ ያረገኝ
የወፍጮ አፍ የተፋው የቋት ስር ዱቄት ነኝ!

እራሴን አፋልጉኝ ...!

ይሔው ባለመኖር፣
መኖርን ከከጀልሁ ብዙ ዓመት ተቆጥሯል!
ብዙ ወርህ ነጉዷል!
አዕላፍ ሰዓት ከስሯል!
ታዲያ...
"አለህ!" አሉኝ እንጂ፣
ተስፋ ደስታን ችሮኝ "ኖርሁ!" የምለው የታል!?

እራሴን አፋልጉኝ...
ከመታገል ልውጣ ከመኖር ልወዳጅ
ባስለቃሾቸ ፊት፣
እምባየን ገፍትሬ ፈገግታን ልቀዳጅ!

ለምክንያት ተፈጥሮ፣
እድሜ ባጉል ሲወድም እጅጉን ይቆጫል
እራሴን አፋልጉኝ!፣
ነገንኳ ልኑር! "ትናንትናስ" ከስሯል!

በቀሪ እድሜየ ላይ
ከእርጅና ፊት ጋ ህልሜ በስሎ ይታይ!

በመንጋ እየታሸሁ፣
በመንጋ እየታወርሁ፣
በባዶ በርሜል ወግ ዘመን ማክሰር ይብቃኝ
ከእኔነት ጨው ይውጣ፣
መራራየ እረክሶ ኑረት ይጣፍጥልኝ!
:
:
.... እራሴን አፋልጉኝ !

#ሼር

@ethiopia2123