Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በሸገር ሲቲ የመስጅዶች ውድመት ተከትሎ በአዲስ አበ | "ኡማ ቲቪ " Tv

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በሸገር ሲቲ የመስጅዶች ውድመት ተከትሎ በአዲስ አበባ በፀጥታ አካላት የተፈፀሙ ጥቃትን ተከትሎ አጠቃላይ ሂደትን በተመለከተ አራት ንዑስ ኮሚቴ አዋቀረ።

ኮሚቴው ዱዓቶች፣ ባለሀብቶች፣ የክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳይ አመራሮች፣ ሙሁራን እና አክቲቪስቶችን ያካተተ ሲሆን እነሱም:-

1) መረጃ አጣሪና ክትትል ኮሚቴ:- አስር አባለት ያሉት ሲሆን የጤና ባለሙያና የህግ ባለሙያን ያካተተ ስብስብ ነው።

2) የህግ ክፍል ኮሚቴ:- በሙስሊሞችና በመስጅዶች ላይ ኢ- ህገ መንግስታዊ ድርጊት የፈጸሙና ያስፈጸሙ የፀጥታ አካላትን ጨምሮ በሂደቱ ተገቢ ባልሆነ መልኩ የተሳሩ እህትና ወንድሞችን ጉዳይ የሚከታተልና የሚያስፈጽም ክፍል ነው።

3) የአማካሪ ቡድን:- ከመረጃ እና ክትትል ክፍል፣ ከህግ ክፍል እና ከተለያዩ ነጥቦች ጥልቅ እይታዎች እየቃኘ የተዋቀሩት ንዑስ ኮሚቴዎችና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትን የሚያማክር ይሆናል።

4) የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ:- ጥቃቱን ተከትሎ የተሰዉ ቤተሰቦችን ለመደገፍ፣ የተጎዱትን ህክምና እንዲያገኙ ለማስቻል እና በእስር ላይ የሚገኙ እህት ወንድሞችን ከህግ ክፍል ጋር በመሆን ነፃ የማድረግ ስራዎችን ይሰራሉ ተብሎ
ተዋቅሯል ።



በዚህ መሰረት ንዑሳን ኮሚቴዎቹ ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ ይገባሉ። ይህ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል በሀገር ውስጥ ሆነ ከሀገር ውጭ ለምትገኙ በሙሉ ከኮሚቴዎቹ ጎን እንድትቆሙ ጥሪ ቀርቧል።