Get Mystery Box with random crypto!

ከመንገድ ላይ እና ቤት ለቤት በርካታ ሰዎች ሙስሊምም ሙስሊምም ያልሆኑ ሰዎች ታፍሰው በተለያዩ እስ | "ኡማ ቲቪ " Tv

ከመንገድ ላይ እና ቤት ለቤት በርካታ ሰዎች ሙስሊምም ሙስሊምም ያልሆኑ ሰዎች ታፍሰው በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ።

ከነሱም ውስጥ እስከ አሁን ፍርድ ቤት ያልቀረቡና ምርመራ ቦታ ላይ በማስገደድ ጭምር ቪዲዮ እየተቀረጹና ዶክመንተሪ መስራት እየተዘጋጁ እንደሆነ ሰምተናል።

ይህ ትውልድ የምትደብቁትም ሆነ የምትነግሩት አዲስ ነገር የለም፣ ሁሉንም ያውቃል።

ትላንት ጅሀዳዊ ሀረካትን ያወገዘና እኛ ነን አሸባሪ ያለ ስርዓት ንፁሃን ባልዋሉበት በማሰርና ፍርድ ቤት ባለማቅረብ ከመቅጣት አልፎ ዶክመንተሪ ለመስራት ሽር ጉድ እየተባለ ነው።

የህዝብ ጥያቄ ዶክመንተሪ ሳይሆን መስጅዶቻችንን አታፍርሱብን፣ወደ ክብር ቦታቸው መልሱንል ነው።

ዶክመንተሪ ጊዜ ያለፈበት ካለፈው ጋር የፈረሰ ሀሳብ ነው።