Get Mystery Box with random crypto!

በአንዋር መስጅድና አካባቢው በባለፈው ሳምንት ጁሙዓን ጨምሮ የታሰሩ ሙስሊምና ሙስሊም ያልሆነ ወገኖ | "ኡማ ቲቪ " Tv

በአንዋር መስጅድና አካባቢው በባለፈው ሳምንት ጁሙዓን ጨምሮ የታሰሩ ሙስሊምና ሙስሊም ያልሆነ ወገኖች በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል
...
ሀሩን ሚዲያ፥ ግንቦት 28/2015
...
በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት ግንቦት 18 እና ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓም አንዋር መስጅድ አካባቢና ከመኖሪያ ቤታቸው ከስራ ገበታቸው የተያዙ ሙስሊም እና ክርስቲያን ወገኖች ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በስድስት መዛግብትና በ1ኛ እና 2 ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ከሰላት በኋላ ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ድንጋይ በመወርወር በፀጥታ አካላት ጉዳት አድርሰዋል በማለት ተጨማሪ የ14 ቀነ ቀጠሮ ጊዜ እንዲጨመርለት ጠይቋል።
...
በነ ደስታ ፈይሳ መዝገብ 15 ሰዎች፣ በእነ ደምስ ዳንኤል መዝገብ 10 ሰዎች፣ በእነ ኑረዲን መዝገብ 11 ሰዎች፣በእነ ተሾመ ዘሪሁን መዝገብ 4 ሰዎች፣ ለብቻ በሀይሉ አበራ ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል።

ለተጠርጣሪዎች በነፃ ጥብቅና አገልግሎት በፈቃደኝነት ለሁሉም ተጠርጣሪዎች በጠበቃ ሙስጠፋ ሽፋ እና በጠበቃ ኢዘዲን ፈድሉ አማካኝነት ተጠርጣሪዎችን በመወከል ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ አይገባም፣ የዋስትና መብት ሊጠበቅ ይገባል፣ የተጠርጣሪዎች ማረፊያ አራት በአምስት በማይሞላ ክፍል ከ50 በላይ እስረኛ መኖሩን፣ የንፅህ መታጠቢያ መፀዳጃ ቤትን ችግር የህክምና እጦትን በማንሳት ሰፋ ያለ ክርክር ተደርጎ ፍርድ ቤቱም ከማረፊያ ቤትና መፀዳጃ ሻወር እንዲሁም ህክምናን ፖሊስ እንዲያስተካክል ለቀጣይ ቀጠሮ የምርመራ መዝገብ ይዞ እንዲቀርብ ለሰኔ 05 እና ለሰኔ 08 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
...
ጠበቃ ፍርድ ቤት እንዳይገባ የተደረገውን ለችሎት አሳስበን ችሎቱንም ድርጊቱን በመንቀፍ ለችሎት እንድናመለክት አሳስቧል። በዚሁ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ወቅትና ቦታ ተከሰው የነበሩ እነ አይመን መሀመድ እና 4 ሰዎች ደግሞ በዋስትና ተለቀዋል።ለብቻዋ የቀረበችው ፋጡማ ሁሴን ደግሞ የችሎት ቀንሽ ዛሬ አይደለም ሰኔ 01 ቀን 2015 ዓም ነው ተብላ ተመልሳለች።
...
ሀሩን ሚዲያ