Get Mystery Box with random crypto!

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማሩን ሥራ መጀመሩን አስታወቀ። የዩኒቨርሲቲ የ | ESAT International

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማሩን ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ከሰተ ለገሰ፣ የመማር ማስተማሩን ሥራ የጀመሩት ከሚጠበቁት 13ሺህ ተማሪዎች ውስጥ አብዛኛዎቹን በመቀበል ላይ መሆኑንና የቀሩትንም እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል።

ተማሪዎቹ በመቀሌ ማኅበረሰብ እና ተማሪዎች ኅብረት አቀባበል እየተደረገላቸው ከየካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አንሥቶ ትምህርታቸውን መከታተል መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎች፣ መኝታ ቤቶች፣ ምግብ ማብሰያ እና መመገቢያ አዳራሾችን የኮሮና ወረረሽኝን ለመከላከል ታሳቢ ባደረገ መልኩ ቀድመው መሰናዳታቸውን ዶ/ር ከሰተ አስረድተዋል።

ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ዓመት ድረስ የሚማሩት እነዚህ ተማሪዎቹ የተቋሙን ሕግ እና ሥርዓት አክብረው ትምህርታቸውን መከታታል እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል።

ትምህርታቸው መከታተል ከጀመሩት መካከል ከደቡብ ክልል የመጣው የአዲሀቂ ካምፓሰ የሶሾሎጂ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ቸርነት ሺፈራው ትምህርት በመጀመሩ መደሰቱን ገልጾ፣ በንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት በኩል ግን እጥረት ስላለ እንዲስተካከል አስተያየቱን ሰጥቷል።

የእኛ ተማሪዎች ሕልም በሰላም እና ፍቅር ትምህርታችንን መከታተል እና ተመርቀን ራሳችንና ሀገራችን መጥቀም ነው ያለው ደግሞ የሁለተኛ ዓመት ሶሾሎጂ ተማሪ እንድሪስ አብዱ ነው።

ከኦሮሚያ ክልል የመጣው ተማሪ ጫላ ሳፋይ በበኩሉ ዩኒቨርሲቲው ለመማር ማስተማር የሚያስችል የግቢው መሠረተ ልማት ማሟላቱን ገልጿል።

በምግብ ሰዓት ግን በወረፋ ብዛት ምክንያት ለብዙ ሰዓታት እየጠበቅን መሆኑን ታውቆ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።

@ethiomereja1 ሼር