Get Mystery Box with random crypto!

በ24 ሰዓት ውስጥ አራት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ አባዝተን እንሠጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ | ESAT International

በ24 ሰዓት ውስጥ አራት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ አባዝተን እንሠጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ካሜሮናውያንን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋን በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አንድ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ቀጥረው በማግኘት "2 ሚሊዮን ትክክለኛ የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ ይዘህ ከመጣህ በ24 ሰዓት ውስጥ በሁለት እጥፍ በማተም በአጠቃላይ አራት ሚሊዮን ዶላር ስለሚሆን 40 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ ላንተ ቀሪውን 60 በመቶ ገንዘብ ደግሞ ለራሳችን እንወስዳለን" ብለው እንዲስማማ በማግባባት የማታለል ወንጀል ሲፈጽሙ እንደነበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ካሜሮናውያኑ ኢትዮጵያዊውን ግለሰብ ያባዛነው የአሜሪካው ዶላር ናሙና ነው በማለት ትክክለኛውን ኖት አንድ መቶ ዶላር በመሥጠት ወደ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሄዶ ወደ ኢትዮጵያ ብር እንዲቀይረው በማደረግ ጭምር የሚያባዙት የገንዘብ ኖት ትክክለኛና ህጋዊ ተቀባይነት ያለው እንደሆነ በማስመስል ግለሰቡን ለማጭበርበር እንደቻሉ ከተገኘው ማስረጃ ለመረዳት ተችሏል።

ጉዳዩን አስመልከቶ መረጃ የደረሳቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትም ሁለቱ ካሜሮናውያንና በውጭ አገር ሆኖ ስምሪት የሚሰጣቸውን ግለሰብ ጨምሮ የሚያደረጉትን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በጥብቅ ሚስጥር በመከታተል ሃሰተኛ ገንዘብ ለማተም የሚጠቀሙባቸውን የተለያዩ መሣሪያዎች፣ የአሜሪካን ዶላር፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ገንዘብ፣ ድርሃምና የኬንያ ሽልንግ ትክክለኛ ገንዘቦችን ጨምሮ ሰነዶችና ፓስፖርቶች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አድርገዋል።

@ethiomereja1 ሼር