Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ትግራይ.... የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል የየብስ | Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ

ወደ ትግራይ....

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል የየብስ ትራንስፖርት ለማስጀመር ለማኅበራት መመሪያ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ በሰላም ሚኒስትሩ የሚመራው የሚኒስትሮች ኮሚቴ እንደፈቀደ አገልግሎቱ ይጀመራል፡፡

በዚሁ መሰረት የአገር አቋራጭ፣ ልዩ አውቶቡስ፣ መደበኛ አውቶብስ እና ሌሎችም የትራንስፖርት ሰጪ ማኅበራት ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ መተላለፉ ተገልጿል፡፡

አገልግሎቱም ቀደም ሲል በነበረው መስመር መሰረት መቀሌ፣ አክሱም እና ሽረን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች ይጀመራል ነው የተባለው። (ኤፍ ቢ ሲ)
መረጃ በድምፅና ምስል ለማግኘት Subscribe ያድርገት
https://youtube.com/@Wasu_Mohammed