Get Mystery Box with random crypto!

የአሰቴር አወቀ 'ሶባ' አዲስ አልበም ዛሬ ለአድማጭ ይቀርባል፡፡ ዝነኛዋ ድምፃዊት አስቴር አወቀ | Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ

የአሰቴር አወቀ "ሶባ" አዲስ አልበም ዛሬ ለአድማጭ ይቀርባል፡፡

ዝነኛዋ ድምፃዊት አስቴር አወቀ ሶባ ስትል የሰየመችዉ አዲስ አልበም ዛሬ ከሰአት ከ10፡00 ሰአት ጀምሮ ለአድማጭ እንደሚቀርብ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረገችዉ የድምፃዊቷ የሙዚቃ ማኔጀር አዳነች ወርቁ ገልጻለች፡፡

በዚህኛዉም አልበም ወጣቱ የሙዚቃ አቀናባሪ ክብረአብ ጣሰዉን ጨምሮ አሌክስ ይለፍ "ሶባ" አልበም ላይ በቅንበር የተሳተፉ ሲሆን የአልበሙን ማሰተሪንግ ደግሞ አበጋዝ ክብረ ወርቅ እዲሰራዉ መደረጉም ታዉቋል፡፡

ካለፉት አመታት በተለየ መንገድ በሰዋሰዉ መተግበሪያ ላይ ተጭኖ የሚወጣዉ የዝነኛዋ ድምፃዊት አሰቴር አወቀ አልበም የድምፃዊቷን ስራዎች በካሴት እና በሲዲ ሲያደምጥ ለቆየዉ አድናቂዎች ግን የተለየ ሴሜትን ፈጥሯል፡፡

ሰለሆነዉ ማብራሪያ የሰጠችዉ የድምፃዊቷ ማኔጀር አሰቴር አድናቂዎቿ ሊሰማቸዉ የሚችለዉ አይነት ቅር መሰኘት በመጠኑም መኖሩን አልሸሸገችም።

ነገር ግን በሙዚቃ ዘርፉ የተፈጠረዉ ሁናቴ፤ አለም አቀፍ ተሞክሮዉ ጨምሮ ሙዚቀ እየወጣበት ያለዉ መንገድ እንዲቀየር በማድረጉ እና በኢትዮጵያ በዚህ መንገድ የተሰማራዉን ሰዋሰዉ መልቲሚዲያን ለማበረታታት ጭምር በማሰብ ሙዚቃዉ በመተግበሪያዉ እንዲወጣ መደረጉን አዳነች ለመሰንበቻ ፕሮግራም ተናግራለች፡፡

ዛሬ ከሚወጣዉ የአሰቴር አወቀ ሶባ አልበም ዉስጥም በዝነኛዋ የፊልም ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ዳይሬክት የተደረገዉ "ተመለስ" የሙዚቃ ቪዲዮም ቀድሞ ይለቀቃልም ተብሏል፡፡