Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofastnew — Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofastnew — Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofastnew
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.66K
የሰርጥ መግለጫ

ከእየአቅጣጫው ሁሉም ዜናዎች በአንድ ቦታ የሚያገኙበት አዲስ ቻናል ነው‼

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-12 20:10:07 ስናን

ምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ እረቡ ገበያ በተባለ የግብይት ቦታ ከእንስሳት ቀረጥ ጋር ተያይዞ በተነሳ አለመግባባት የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።ድርጊቱ ትናንት መጋቢት 2/2015 ከቀኑ 7:00 አካባቢ መፈፀሙን የተናገሩት የአይን እማኞች ከሞቱት በተጨማሪ 1 ሰው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ብለዋል።
https://t.me/andethio
341 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 06:19:51 በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች ተገደሉ!

በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ በሚገኙ ጉቦሄማና ቦጨሣ በተባሉ አከባቢዎች በተከሰተ ግጭት 12 ሰዎች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች መሆናቸውን የገለፁ ነዋሪዎች ተናገሩ።

በጉዳዩ ላይ ከአካባቢው ባለሥልጣናት መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። በሌላ በኩል የጭሪ ወረዳ ጤና ጣቢያ ባለሞያ በጥይት ቆስለው ጤና ጣቢያ ለደረሱ ሰዎች የሕክምና አገልግሎት መስጠታቸውና ተጨማሪ ሕክምና ያስፈልጋቸዋል ያሉትን ደግሞ ወደ ከፍተኛ ሆስፒታል መላካቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሐዋሳ ቅርንጫፍ ስለ ጉዳዩ መረጃ እንዳላቸው ጠቅሶ በቅርቡ ሪፖርት ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
     ምንጭ:-VOA
845 views03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 06:10:34
አባይ በረሃ ላይ የደረሰ አሳዛኝ የመኪና አደጋ

አባት እና ልጅ አብረው ይሰራሉ አባት ሾፌር ልጅ ረዳት ሆነው ኑሮን ለማሸነፍ ቤተሰብን ለመደገፍ ይደክማሉ የካቲት 26/06/2015 ግን ለአባት እና ልጅ መልካም አልነበረም ጭነት ጭነው አባይ በረሃን እየወረዱ ባለበት ሂደት መኪና ፍሬን እምቢ ይላቸዋል አባትም በእሳቸው በኩል ገደል በልጃቸው በኩል ተራራ መሆኑን ያያሉ በልጃቸው በኩል ቢያጋጩ የልጃቸው ህይወት መጥፋቱን ግምት ውስጥ በማስገባት ልጃቸውን ዘለህ ውረድ በማለት በእሳቸው በኩል መኪናውን ይጥላሉ መኪናውም ገደል ይገባል የሾፌሩም ህይወት ያልፋል።

አባት ልጃቸውን ታድገው በራሳቸው በኩል ጥለው ወደ ጥልቁ ገደል ገብተው ላይመለሱ ለዘልአለም አሸልበዋል አባት ለልጁ ምን እንደሆነ በተግባር አሳይተዋል።

(ሰጡ ብርሃን)
29.6K views03:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 13:52:41 የመውጫ ፈተና

#ExitExam   የዩንቨርሲቲ መውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ያገኙትን መረጃ እናጋራቹህ

1. #ጥያቄ፡- የመዉጫ ፈተናው የሚሰጠዉ ከምርቃት ቧላነዉ ወይስ በፊት?

#መልስ፡- የመውጫ ፈተና አንድ ተመራቂ ተማሪ ከመመረቁ በፊት በትምህርት ህግ ማሟላት ያለበት መስፈርት ሰለሆነ ፈተናዉ የሚሰጠዉ ከ ምርቃት አስቀድሞነዉ፡፡

2.#ጥያቄ፡- ፈተናው በኦንላይንነዉ ወይስ ወረቀት?

- #መልስ፡- ፈተናው የሚሰጠዉ  ኦንላይንነዉ። ሁሉም ጥያቄዎች ምርጫ ብቻ ናቸው።የሒሳብ ጥያቄዎችም ስለሚኖሩ ተማሪዎች ወረቀት እና ኢስክሪፕቶ ይዞ ይገባሉ።

3.#ጥያቄ: - ፈተናዉ የሚሰጥብት በቋሚነት መቼነዉ?

#መልስ፡- ከ ሰኔ 20 እስከ ሐምሌ 20 ባሌ ጊዜ ዉስጥ ይሰጣል

4.#ጥያቄ፡ ስለ ሞጁል የተነሳ ጥያቄ

- #መልስ፡-የተለያዬ ሞጁል ሆኔ የሚለዉ ተማሪዉ ጊዜዉን ሰያባክን በዲፐርትመንት በኩል በሰነድ መልክ የተላከለትን (Core Competencies) ላይ ተመርኩዞ ተጨማሪ የማንበቢያ ማቴሪያሎችን እና የሚሰጡ ቲቶሪያሎችን በመከተታል ለፈተናዉ መዘጋጀት ይችላል ፡፡

5 #ጥያቄ፡- በፈተና ወቅት የሚሰጠዉ ሰዓት አጠቃቀሙ ምን ይመስላል የሚላዉ ነዉ፡፡

#መልስ፡- ለዚህ ፈተና አዲስ ሶፍትዌር ተፈብርኮ ተዘጋጅቷል። ለዚሁ አላማ ተብሎ የተዘጋጀ ማለት ነዉ።አዲስ ሶፍትዌር ለየት ሚያደርገዉ ለአንድ ጥያቄ ብቻ ሰዓት ሰጥቶ የሚያልፍ ሳይሆን ለአጠቃላይ ጥያቄ የተሰጠዉን ሰዓት ተፈታኙ ሚችለዉን ጥያቄዎችን እንዲሰራ ሙሉ ሰዓቱ የተሰጠዉ እስኪያልቅ የሚጠብቅ እና አስተራረሙ ደግሞ ተማሪው ሙሉ መዉጫ ፈተናውን ከጨረሰ በኋላ ነው ዉጤቱን የሚያየዉ፡፡እዛዉ ይታረማል ከፈተና ክፍል ሳይወጣ የሚለዉ ወሬ ሀሰት ነዉ ሁሉንም የትምህርት ፈተናዎችን ከጨረሰ በኋላ ዉጤቱን ማወቅ ሚቺለዉ፡፡

6 #ጥያቄ     ፦የጥያቄ ብዛት ምን ያህል ነው?

- #መልስ በ አጭሩ ለማስረዳት  በአንድ ዲፓርትመንት 17 ኮርስ ለመዉጫ ፈተና የሚሰጥ ከሆነ እነኚህ 17ቱ ኮርሶች ለ 5 ግሩፕ ተከፍለው ነው  ፈተናዉ ሚወጣው። ለ አንድ ግሩፕ 100 ጥያቄ ማለት ነዉ። ይህ ማለት ደግሞ ለ 5 ግሩፕ ከ 500 ይሆናል ማሌትነዉ፡፡
( የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት )
929 views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 21:27:37
የዝሆን  ሎተሪ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዛሬ  የካቲት 13 ቀን 2015 በሕዝብ ፊት ወጥቷል።
1.2K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 19:43:12 ከደቂቃዎች በፊት መገናኛ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 6 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ከ10 በላይ በርካቶች ጉዳት አጋጥሟቸዋል።
1.2K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 13:19:33 መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎችን ያስጠለሉ እና ቤት ያከራዩ የኦሮሞ ተወላጆች 15 ሺህ ብር ቅጣት ተጣለባቸው

በሸገር ከተማ የለገጣፎ ለገዳዲ ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች ቤታቸው የፈረሰባቸውን ሰዎች በማስጠለላቸውና ቤት በማከራየታቸው የ15ሺ ብር ቅጣት እንደተጣለባቸው ተናግረዋል።

በቅርቡ በተመሰረተው እና ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ነው በተባለው ሸገር ከተማ  ስር በተካተቱ ሰበታ፣ቡራዩ፣ለገጣፎ ለገዳዲ፣ሱሉልታ እና ገላን በተባሉ አከባቢዎች የአማራ ተወላጆች መኖሪያ ቤታቸው ፈርሶባቸው ጎዳና ወድቀዋል።

ከሰሞኑ ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ በኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች በሚታጀብ ግብረ ኃይል መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎችን በማስጠለላቸው እና ቤት በማከራየታቸው የ15 ሺ ብር ቅጣት በከተማ አስተዳደሩ እንደተጣለባቸው ነው የኦሮሞ ተወላጆች የተናገሩት።

የከተማ አስተዳደሩ የጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት ተገደው መክፈላቸውን የገለፁት የኦሮሞ ተወላጆቹ ያከራዩዋቸውን ሰዎችም ከቤታቸው እንዲያስወጡ መደረጋቸውንም ተናግረዋል።

ከአማራ ድምፅ ሚድያ ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት በለገጣፎ ለገዳዲ ኗሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች፡ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎችን ጎዳና ላይ እንዳይወድቁ በሚል ወደ ቤታችን በማስገባት ማስጠለላችን እንዴት ወንጀል ይሆናል ያሉ ሲሆን፣ ይህ የኦሮሞን ህዝብ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ለመለያየት የተሸረበ ሴራ ነው ብለዋል።

የኦሮሞን ህዝብ የጠቀሙ በመምሰል ለዘመናት በአንድነት የዘለቁ ወገኖቻችን ጋር እየለያዩን ነው ያሉን የኦሮሞ ተወላጆቹ፡ የአስተዳደር አካላቱ ከዚህ አይነት ድርጊታቸው በአስቸኳይ እንዲታቀቡ አሳስበዋል።

መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ቤት እንዳይከራዩ ጭምር ታግደው ጎዳና ላይ የወደቁ ሲሆን፣ አንድ አከባቢ ተሰባስበው እንዳይታዩ በፀጥታ ኃይሎች እንዲበተኑ ተደርገዋል።
1.3K views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 06:55:04 ትግራይ

ትግራይ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ በሰሜኑ ጦርነት "ተቋርጦ የቆየው ግንኙነት" እንደገና እንዲቀጥል ያቀረበላቸውን ጥሪ ውድቅ ማድረጋቸውን የትግራይ ክልል ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሲኖዶሱን ጥሪ በጋራ በሰጡት መግለጫ ውድቅ ያደረጉት፣ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ የምሥራቃዊ ትግራይ፣ የማዕከላዊ ትግራይ እና የመቀሌ አሕጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ የሲኖዶሱ ጥሪ ከዓመት በፊት ያቋቋምነውን "መንበረ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ጠቅላይ ቤተክህነት" ያገለለና ለጳጳሳት በግላቸው የተላከ መሆኑን ጠቅሰው ጥሪውን ተቃውመውታል ተብሏል። ሲኖዶሱ በበኩሉ፣ የትግራይ ጳጳሳት ውሳኔ በደብዳቤ ሲደርሰኝ ምላሽ እሰጣለሁ ማለቱን ዘገባው አመልክቷል።
(ዋዜማ ሬዲዬ)
1.1K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 15:59:37 የሕይወት እውነታዎች።

1. ጓደኞችን በሚመርጡበት ጊዜ በጣም መራጭ ይሁኑ።  በአሁኑ ጊዜ  ብዙ ሰዎች የጓደኝነት እና የታማኝነትን ትክክለኛ ትርጉም አያውቁም።

2. ዋጋህን እወቅ።  ደስታህን ከሚያበላሹ ሰዎች  እራቅ።

3. በቀላሉ የሚመጣው ሁልጊዜም አይቆይም።  የሚቆየው ሁልጊዜ ቀላል አይሆንም።

4. መተው በጭራሽ ቀላል አይደለም።ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ነው።

5.  የእነሱን ፍላጎት  ብቻ ከሚያስተናግዱ  ሰዎች  ጋር  ጊዜህን ማባከን አያስፈልግም።

6. ትናንት ማልቀስዎን አቁሙ እና ለነገ ፈገግታ ይጀምሩ።

7. የሚፈልጉትን ያህል የሚፈልግዎትን ሰው ያግኙ።

8. በህይወት ውስጥ እራስህን ለማግኘት ልታጣቸው የሚገቡህ አንዳንድ ሰዎች አሉ።

@Psycho
2.2K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 14:44:45
የአሰቴር አወቀ "ሶባ" አዲስ አልበም ዛሬ ለአድማጭ ይቀርባል፡፡

ዝነኛዋ ድምፃዊት አስቴር አወቀ ሶባ ስትል የሰየመችዉ አዲስ አልበም ዛሬ ከሰአት ከ10፡00 ሰአት ጀምሮ ለአድማጭ እንደሚቀርብ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረገችዉ የድምፃዊቷ የሙዚቃ ማኔጀር አዳነች ወርቁ ገልጻለች፡፡

በዚህኛዉም አልበም ወጣቱ የሙዚቃ አቀናባሪ ክብረአብ ጣሰዉን ጨምሮ አሌክስ ይለፍ "ሶባ" አልበም ላይ በቅንበር የተሳተፉ ሲሆን የአልበሙን ማሰተሪንግ ደግሞ አበጋዝ ክብረ ወርቅ እዲሰራዉ መደረጉም ታዉቋል፡፡

ካለፉት አመታት በተለየ መንገድ በሰዋሰዉ መተግበሪያ ላይ ተጭኖ የሚወጣዉ የዝነኛዋ ድምፃዊት አሰቴር አወቀ አልበም የድምፃዊቷን ስራዎች በካሴት እና በሲዲ ሲያደምጥ ለቆየዉ አድናቂዎች ግን የተለየ ሴሜትን ፈጥሯል፡፡

ሰለሆነዉ ማብራሪያ የሰጠችዉ የድምፃዊቷ ማኔጀር አሰቴር አድናቂዎቿ ሊሰማቸዉ የሚችለዉ አይነት ቅር መሰኘት በመጠኑም መኖሩን አልሸሸገችም።

ነገር ግን በሙዚቃ ዘርፉ የተፈጠረዉ ሁናቴ፤ አለም አቀፍ ተሞክሮዉ ጨምሮ ሙዚቀ እየወጣበት ያለዉ መንገድ እንዲቀየር በማድረጉ እና በኢትዮጵያ በዚህ መንገድ የተሰማራዉን ሰዋሰዉ መልቲሚዲያን ለማበረታታት ጭምር በማሰብ ሙዚቃዉ በመተግበሪያዉ እንዲወጣ መደረጉን አዳነች ለመሰንበቻ ፕሮግራም ተናግራለች፡፡

ዛሬ ከሚወጣዉ የአሰቴር አወቀ ሶባ አልበም ዉስጥም በዝነኛዋ የፊልም ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ዳይሬክት የተደረገዉ "ተመለስ" የሙዚቃ ቪዲዮም ቀድሞ ይለቀቃልም ተብሏል፡፡
2.1K views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ