Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ temret_minster — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ temret_minster — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @temret_minster
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.79K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-19 14:02:28
#ማስታወቂያ

ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከእንግሊዝ የውጭ የጋራ ልማት ቢሮ (FCDO_ ጋር በመተባበር የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር (University Industry Linkage) ላይ የተመሰረቱ ችግር ፈቺ እና ወደ ኢንዱስትሪው ሊሸጋገሩ የሚችሉ የተጠናቀቁ የምርምር ውጤቶችን በማወዳደር ወደ ገበያ እንዲገቡ የፋይናንስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በመሆኑም በዩኒቨርሲቲዎች፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት፣ የምርምር ማዕከላት እንዲሁም ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየሩ የሚችሉ እና ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት አስተዋፆ የሚያበረክቱ የምርምር ውጤቶች ያላችሁ እና የመወዳደሪያ መስፈርቱን የምታሟሉ ተመራማሪዎች እና የፈጠራ ባለሙያዎች ከዚህ በታች በተቀመጠው መስፈንጠሪያ በመጠቀም እስከ የካቲት 11/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

https://docs.google.com/forms/d/1xE-l63ZDhFrtMqDuYGwzncbFgDk1xQ8Vj96ZKcOTw8U/edit?ts=63bfce75

ለበለጠ መረጃ ፡ 0948 862349 ወይም 0912 612679 ይደውሉ
882 viewsedited  11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 16:58:44 የትምህርትና  ስልጠና ፖሊሲ (ረቂቅ)


https://moe.gov.et/Publication
1.4K views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 16:58:44
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከብዘሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዘሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ካቢኔው በመደበኛው ስብሰባ የብዝሃ የቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክቶ የኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን አዲሱን ካሪኩለም አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን ዩንቨርሲቲው ባስጠናው ጥናት ዙርያ ሰፋ ያለ የተለያዩ የህዝብ ( የተማሪ ወላጆችን ጨምሮ) ምክክሮችና ውይይቶች ሲካሄዱበት ቆይቶ በዛሬው እለት በጥናቱ በቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ዙርያ ውሳኔውን አሳርፏል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ:- በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ጥናት መሰረት በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ

2ኛ:- በአማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ አፋን ኦሮሞ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ )ቋንቋ እንዲሰጥ

3ኛ:- ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉም የከተማው ትምህርት ቤቶች የአገር ውስጥ ቋንቋ መማራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉንም የትምህርት አይነቶችን በእንግሊዘኛ መማር እንዲችሉ እንዲደረግ

4ኛ:- ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች አረብኛና ፈረንሳይኛ በሃይስኩል ደረጃ አማራጭ ትምህርት ሆኖ እንዲቀጥል፡፡

5ኛ:- የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት መጀመሪያ እድሜ ከ4 ዓመት እንዲሆን

ለሙሉ መረጃ

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02wbX5E35M5d68Mv3uDYtoSbEsFDj4iSYVr7MRHSdAVQW3sYngvyjPPUnpo9TjULiol&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz
1.5K views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 18:37:10
በትግራይ ክልል ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እና ምልከታ ተካሄደ።
-----------------------------------------

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በትግራይ ክልል ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እና ምልከታ አድርገዋል።

የባለሙያዎቹ ቡድን ምልከታውን ያደረገው በማዕከላዊ ዞንና በሰሜን ምዕራብ ዞኖች ስር ባሉ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአክሱም ዩኒቨርስቲ ሽሬ እና አድዋ ካምፓስ ነው።

ቡድኑ በዞኖቹ ትምህርት ለማስጀመር ባሉ አስቻይ ሁኔታዎችና ትምህርት ቤቶቹ ባሉበት ቁመና ዙሪያ ከየዞኖቹ የትምህርት ስራ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

ከሁለተኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ፣ ምክትል ርዕሰ መምህራን ፣ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም ከ ዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር በተደረገው ውይይት በተፈጠረው ሰላም ትምህርት ለመጀመር እንደሚያስችል ተጠቁሟል።

በውይይቶቹም በትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርስቲዎች የተፈጸሙ ዘረፋዎችና ትምህርት ቤቶች የተፈናቃዮች ማረፊያዎች መሆናቸውና ሌሎችም ተግዳሮቶች ቢኖሩም ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት እንዲጀመር ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩ ተመለክቷል።

በመሆኑም የተጓደሉ መሰረታዊ ግብአቶች ተሟልተው ባጭር ጊዜ በዞኖቹ የተቋረጠው ትምህርት ሊጀመር እንደሚገባ በምልከታው ወቅት መግባባት ላይ ተደርሷል።
2.3K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 22:40:44
3.0K views19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 22:40:43
ገዳ ሮበሌ አንደኛ ደረጃ ና አዋሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በፓን አፍረካ የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚወዳደሩ ታወቀ፡፡

==============================

ታህሳስ 26/2015 ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ከ16 አመት በታች የፓን አፍርካን የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ የማጣሪያ ውድድር ዛሬ ተጠናቋል፡፡

በውድድሩም ሀገራችንን ወክለው በወንዶች ገዳ ሮበሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ በሴቶች አዋሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ክልል አሸናፊ በመሆን ተለይተዋል ።

በውድድሩ ፍጻሜ ላይ ለአሸናፊ ትምህርት ቤቶች፣ ለኮከብ ተጫዋቾችና ለኮከብ ግብ አግቢዎች በእለቱ ክብር እንግዶች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ውድድሩ የተሳካ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተባባሪ አካላት÷ዳኞች÷ለተሳታፊ ክልሎችና ከተማ አስተዳደር የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
2.7K views19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 21:04:20
በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚሰሩ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች የአዕምሮ ጤና፣ የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ

------------------- // -------------------

ታህሳስ 20/2015 ዓ. ም (ትምህርት ሚኒስቴር) ትምህርት ሚኒስቴር በሀገራችን በተከሰቱ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች የተጎዱ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የአዕምሮ ጤና፣ ስነልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ ስልጠናው በችግር ላይ ሆነንም ቢሆን ለነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት እንድንችል አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ሃላፊዋ ጨምረውም ለተጀመረው የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ስኬታማነት በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚሰሩ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች የአዕምሮ ጤና፣ የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በጦርነቱ የወደሙ ት/ቤቶችን በተሻለ ሁኔታ መልሶ ከመገንባት ጎን ለጎን ለመምህራንና ለትምህርት አመራሮች ይህን ስልጠና መስጠት በጣም አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ ሰፊ ስራ ክልሎችም ርብርብ እንዲደርጉ ጥሪ አድርገዋል፡፡

ለሙሉ መረጃ

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0uDoFiE6ntJzHLSMsfaBBuymDtaUnUNCpPFt9FSAv3b2yUPbmu41X7dr1T41NZhsyl&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz
958 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 17:26:47
የተማሪዎችን የንባብ ክህሎት ለማዳበር በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገለፀ
------------------------------------------------------

ታህሳስ 18/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር በተማሪዎች የንባብ ክህሎት ማነስ እና መፍትሄ ዙሪያ ከክልል እና ከተማ መስተዳድር ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ ነው፡፡

የምክክር መድረኩን ያስጀመሩት በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቋንቋዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ የተማሪዎች የንባብ ክህሎት ማነስ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እየተሄደበት ያለውን እርቀት እንደሚያስተጓጉል ገልጸዋል፡፡

ሃላፊዋ የተማሪዎች የንባብ ክህሎት እንደየ ክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ የተለያየ መሆኑን ገልፀው ካለበት ሁኔታ ለማንሳት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመድረኩም በንባብ ክሊኒክ ፓይለት ፕሮጀክት የጥናት ውጤቶች ለተሳታፊዎች ቀርበዉ ውይይት ተደረጎባቸዋል፡፡

ጥናቱን ያቀረቡት መንግሰቱ ታደሰ(ዶ/ር) እንደገለጹት የንባብ ክህሎትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራት ተማሪዎችን ካለማንበብ ወደ ማንበብ ማምጣት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

የንባብ ክሊኒክ ፕሮጀክት ባለሙያዎች ያላቸውን መሰረታዊ የንባብ ክህሎት ወደ መሬት አውርደው በመስራት ተማሪዎችን ውጤታማ ማድረግ የቻሉበት በመሆኑ በሞዴልነት ማስፋፋት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን የማንበብ ክህሎት ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።
1.0K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 17:36:10
መምህራን ቴክኖሎጂን በአግባቡ በመጠቀም የተሻለች አገር የሚፈጥር ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ማነጽ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ
....................................................................................

ታህሳስ 13/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) ከአንድ ሺ ለሚበልጡ የ2ኛ ደረጃ መምህራን በቴክኖሎጁ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት የጊዜውን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ አገሩን የሚገነባ ትውልድ መፍጠር ከመምህራን የሚጠበቅ ተግባር ነው።

በመሆኑም መምህራን የቴክኖሎጂ አቅማቸውን በማሳደግ በስርዓተ ትምህርቱ ላይ የተቀመጡ ዓላማዎችን ተማሪዎች በቀላሉና በተሻለ እንዲረዱ ማስቻል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ከፍተኛ የድጋፍና ክትትል ባለሙያ አቶ አለሙ ተስፋዬ በበኩላቸው የስልጠናው ዓላማ መምህራን ቴክኖሎጁን አማራጭ የትምህርት መረጃ መሳሪያ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራውን ለማጠናከር ነው ብለዋል።

ስልጠናው መምህራን የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን በማሳደግ አዳዲስ ዕውቀቶችን እንዳያብሩና በአንድ ጊዜ ብዙ ተማሪዎችን ለመድረስ እንደሚያስችላቸውም አቶ አለሙ ተናግረዋል።

ከሁሉም ክልሎች ለተመለመሉ የ2ኛ ደረጃ መምህራን በ11 የስልጠና ማዕከላት በተሰጠው በዚህ ስልጠና ከአንድ ሺ አንድ መቶ የሚበልጡ ተሳታፊዎች መገኘታቸውንም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ 3ሺ 12 የትምህርት ቤት አመራሮች አቅም ለማጎልበት ልዩ የአንድ ዓመት የስራ ላይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ ገልጸዋል።
634 views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 19:08:54
ወጣቶችን በቴክኖሎጂ መስክ ማሰልጠን እና ማብቃት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት ትልቅ ሚና አለው፦ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ
************************

ወጣቶችን በቴክኖሎጂ መስክ ማሰልጠን እና ማብቃት ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ትልቅ ሚና አለው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቷ ከአይኮግ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቤተልሄም ደሴ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው ያተኮረው ድርጅቱ በታዳጊ ልጆች በተለይም ሴት ልጆች ላይ የሚያተኩሩ የቴክኖሎጂ ትምህርት ሥራዎች እንዲሁም በቅርቡ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ ጋር ስላስመረቁት ዲጂትራክ ኢትዮጵያ የተሰኘ ፕሮጀክት ዙርያ መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንቷ አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ወጣት በሆነበት ሀገር የቴክኖሎጂ ዘርፎችን ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ ዓለም ውስጥ ይህንን ትውልድ በቴክኖሎጂው መስክ ማሰልጠን እና ማብቃት ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

የአይኮግ ፕሮጀክት የሆነው ዲጂትራክ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች እኩል የሆነ ዕድል ተሰጥቷቸው የኮዲንግ፣ የሮቦቲክስ እና ሌሎች አዳዲስ የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ ማስቻል እና በታለሙ አካባቢዎች ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች የማገናዘብ፣ የችግር ፈችነት እና የፈጠራ ክህሎት የማዳበር ትምህርት ያለውን ጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጥ መሆኑን ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አይኮግ ኢትዮጵያ በኮምፒውተር ኮዲንግ ላይ አተኩሮ የሚሰራ ሲሆን በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክ የምርምር ማዕከል በማቋቋም እየሠራ እንደሚገኝ ኢቢሲ ዘግቧል።
491 views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ