Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ህገ ወጥ ተግባራትን የፈፀሙ የሀይማኖት አባቶች ከሥል | Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ህገ ወጥ ተግባራትን የፈፀሙ የሀይማኖት አባቶች ከሥልጣነ ክህነት እንዲነሱ ወሰነ

•  ከዛሬ ጀምሮ በአለማዊ ስማቸው ይጠራሉ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንደገለጹት የወሊሶውን ሕገ ወጥ የኤጴስ ቆጶሳት ሹመት ያስፈጸሙ 3 ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩ ግለሰቦች እና በሕገ ወጥ ሹመቱን ለመቀበል ወሊሶ የሄዱ 25 መነኮሳት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአንድነት ጉባኤ ተለይተው እንዲወገዙ ተወስኗል።

ፓትርያርክ በሌለበት የተሰጠውን መፍትሔ ፓትርያርክ ባለበት ሉዋላዊ ስልጣንን በመግፋትና መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረጋቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዟል። ቅዱስ ፓትርያርክ በሌለበት የሚሰጥን ሹመት ቅዱስ ሲኖዶስ ያወግዝ ዘንድ ሕገ ቤተ ክርስቲያን የተወገዘ ይሁን ስለሚል አውግዘናል::
መጠርያቸውም ሊቀ ጳጳስ እና ቆሞስ ተብሎ ይጠራ የነበረው አቶ ተብሎ እንዲተካ በሙሉ ድምጽ ተወስኗል።

ይህን ሕገ ወጥነት ያስተባበሩ ሥልጣነ ክህነት ያላቸው አካላት በሙሉ ተወግዘው ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲለዩ በተጨማሪ ተወስኗል።

ኢ-ሲኖዳሳዊ ሕገ ወጥ ተግባር በመፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ይኽንን ለመወሰን ተገዷል። የቅዱስ ሲኖዶስን መንፈሳዊ ስልጣንና ተግባር እንዲሁም ፍትሐ ነገሥትን ጥሰዋል።
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ የሕንድ ኦርቶዶክስ ማላንካራ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ተቋማት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

በጸጸት የተመለሱ አባ ጸጋ ዘአብ ብቻ በውግዘት ሳይለዩ በልዩነት ተይዘው በቅኖና ቤተ ክርስቲያን ጉዳያቸው እንዲታይ ተወስኗል።

ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በጠበቀ መንገድ በይቅርታ ከተመለሱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸው መሆኑን ተገልጿል፡፡