Get Mystery Box with random crypto!

ውጤቱን ዛሬ ምሽት 5:30 ይለቀቃ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተማሪዎች ከዛሬ ለሊት ጀም | Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ

ውጤቱን ዛሬ ምሽት 5:30 ይለቀቃ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተማሪዎች ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም #ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ ፡-

• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ  https://t.me/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል።

ማሳሰቢያ፡-

• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

• ተማሪዎች ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ #ከተመሳሳይ እና #የተዛባ_መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

ምንጭ ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት