Get Mystery Box with random crypto!

Ewunet Media(እውነት)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioewuneta — Ewunet Media(እውነት) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioewuneta — Ewunet Media(እውነት)
የሰርጥ አድራሻ: @ethioewuneta
ምድቦች: ቪዲዮዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.45K
የሰርጥ መግለጫ

🇪🇹እንኳን ወደ እውነት ሚድያ በሰላም መጣችሁ🇪🇹
በውስጥ መስመር ከፈለጉን @Ewuneta_bot
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ
👇
https://youtube.com/channel/UCjiq4hREIdyVsnPPKfSOkcg

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-12 11:25:15 የአማራ ልዩ ሃይል በሸኔ ከጀርባ ተመቷል

ኮንደሚኒየሙ ጉድ አመጣ

ህወሃት በኤርትራና ሶማሊያ ዘመቻ

ከፍቷል በጎንደር የቅማንት ታጣቂ
===================
05/11/2014 ማክሰኞ
(17:00 min) 7.8 MB
=====================

መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
4.4K views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:57:47 ላልቆጠቡ ሰዎች የቤት እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች በመገኘቱ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን አስተዳደሩ አስታወቀ

(ኢ.ፕ.ድ)

ሀምሌ 01 ቀን 2014 የወጣው የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ላይ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች በመገኘቱ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን አስተዳደሩ አስታወቀ።

በዚህ ዙሪያ አስተዳደሩ ማምሻውን መግለጫ አውጥቷል።

የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል ብሏል አስተዳደሩ በመግለጫው።

ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን ሲልም ገልጿል፡፡

አስተዳድሩ.ማምሻውን ያወጣው መረጃ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፤

ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ይመለከታል::

በከተማችን አዲስ አበባ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል አንዱ የቤት አቅርቦት እጥረት ሲሆን ይህንኑ ደረጃ በደረጃ ለማቃለል አስተዳደሩ የተለያዩ አማራጮችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የዚህ ሂደት አካል የሆነው የነባሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉበትን ወስብስብ ችግር ለይቶ በመፍታት ተመዝጋቢዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ እና የቤት እጥረት ጫና ለመቀነስ የተደረገው ሰፊ ጥረት ተጠቃሽ ነው፡፡
በዚህ ሂደት በግንባታ ላይ የነበሩ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል 25,491 ያህሉ በቅርቡ ለባለ እድለኞች የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት መካሄዱ ይታወቃል፡፡

ይህ የቤት ማሰስተላለፍ ስራ እንደ ከዚህ በፊቱ በቆጣቢወች መካከል አድሎና ብልሹ አሰራር እንዳይኖር ለማድረግ ግልፅነት በሚያሰፍን አግባብ ለማስተላለፍ ሲባል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ በመስራት ሂደቱን ግልጽና አሳታፊ ለማድረግ የተደረገው ተነሳሽነትና ጥረት እንዲሁም የባልሙያዎችን ሙያዊ ነፃነት አክብረን አስፈላጊውን ሂደት ተከትለን ተዓማኒነቱን እንዲያረጋግጡልን አድርገን ነበር:: በዚህ ሂደት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ አዲስ ሶፍትዌር እንዲበለፅግ እና ስለሶፍትዌሩ ታአማኒነት የኢኖቬንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር እንዲያረጋግጥልንም ተደርጓል::

በቀጣይም ከሁለት ጊዜ በላይ ታዛቢወች እና ባለሙያወች ፊት ቀርቦ እንዲያረጋግጡልን ተደርጎ ማረጋገጫ ሰጥተዋል::
ይህ ሁሉ ሂደት ከእለት ጉርሱ የቆጠበዉን እና በከፍተኛ ጉጉት የሚጠባበቀውን ሕዝብ በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ ቀና ሃሳብ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል::

ይሁን እንጂ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል::

በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡

ከዚህ በመነሳትም የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል::

ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

ለተፈጠረው ስህተት የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ ይጠይቃል።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ሐምሌ 4/2014 ዓ/ም
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
5.0K views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 15:25:35
የባለ እድለኞች ስም ዝርዝር

የተከበራችሁ የእውነት ሚዲያ ቤተሰቦች

የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች በዛሬ ዕለት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት የዕጣ ዕድለኞችን ስም ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃዎችን በዚህ የቴሌግራም ይቀርባል።

የቴሌግራም ቻናላችንን ሰብስክራይብ አድርገው ይከታተሉ።
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
6.2K viewsedited  12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 12:26:59 ደብረጺዮን እንቢ ያሉት የኢሳያስ ምክር

ክልሉ ለሁለት ሊከፈል ነው

ኢትዮጵያ ወደቧን አስመለሰች

ህወሃት በአማራ ተወካዮች ላይ ዘመቻ ከፈተ
===================
02/11/2014 ቅዳሜ
(15:14 min) 7.0 MB
=====================

መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
5.6K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 19:26:05 ኢሰመኮ፤ ኢትዮጵያ አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት ቀውስ ውስጥ መሆኗን አስታወቀ


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኢትዮጵያ አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ አስታወቀ። ኮሚሽኑ ይህን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

ኢሰመኮ ዓመታዊ ሪፖርቱን ዛሬ አርብ ሐምሌ 1፤ 2014 ይፋ ያደረገው መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። በዚሁ መግለጫ ላይ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ሀገሪቷ ያለችው ምንም የማይካድ አሳሳቢ የሆነ ሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ውስጥ ስለሆነ፤ በርካታ አሳሳቢ ጉዳዮች በየዘርፉ አሉ” ሲሉ የሀገሪቱን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ግምገማ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። 

በኮሚሽኑ የሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች ኮሚሽነሩ ዶ/ር አብዲ ጂብሪል፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን አሳሳቢ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል አንዱ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ “መንግስታዊ ባልሆኑ ተዋናዮች” የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየጨመሩ መምጣታቸውንም ጠቁመዋል። 

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት “በዋናነት መንግስታዊ ካልሆኑት ከታጣቂ ቡድኖች መምጣታቸው” ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር አስቸጋሪ እንዳደረገው ዶ/ር አብዲ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በዛሬው መግለጫ ላይ ይፋ በተደረገው የኢሰመኮ ሪፖርትም ይኸው እውነታ ተደጋግሞ ተስተጋብቷል። 

ለሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ቅድሚያ የሰጠው ሪፖርቱ፤ በህይወት የመኖር መብትን በዳሰሰበት ክፍል “ባለፉት 12 ወራት በህይወት የመኖር መብት እጅግ የከፋ አደጋ ውስጥ እንደወደቀ ቀጥሏል” ሲል አትቷል። ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም በኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ሶማሌ ክልሎች የተፈጸሙ የሲቪል ሰዎች ግድያን በማሳያነት ጠቅሷል።

ኢሰመኮ በአማራ እና በአፋር ክልል ለተፈጸሙ ግድያዎች በሁሉም ወገኖች ያሉ የጦርነቱን ተሳታፊዎች ተጠያቂ ሲያደርግ፤ በኦሮሚያ ክልል ለተፈጸሙት ግድያዎች ደግሞ “ኦነግ ሸኔ” የተባለው ቡድንን ወንጅሏል። በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከጭካኔ፣ ኢ-ሰብዓዊ እና አዋራጅ አያያዝ ቅጣት ነጻ የመሆን መብቶች መጣሳቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል። 

መብታቸው የተጣሰባቸው አብዛኛዎቹ ሲቪል ሰዎች መሆናቸውን እና በጦርነቱ ተሳትፈው የተማረኩ ተዋጊዎችም ለዚህ መብት ጥሰት መጋለጣቸውን አስታውቋል። ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቆየችባቸው ከጥር እስከ የካቲት ባሉት ሶስት ወራት ገደማ “መጠነ ሰፊ የዘፈቀደ እስር፣ ብሔርን መሰረት ያደረገ አድሏዊ አሰራር፣ እስራት እና ያለ አግባብ ከስራ እና ከደመወዘ መታገድ ተፈጽሟል” ብሏል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በትግራይ ክልልም ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት መሆኑን ኢሰመኮ አስታውቋል። ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ደንብ በማውጣት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ መሆኑን ያስታወቀው ኮሚሽኑ፤ ህወሓት ያወጣው አዋጅ “የሰዎችን መብቶች በከፍተኛ ሁኔታ የገደበ እና ከኢትዮጵያ ህገ መንግስት እና የወንጀል ህግ ጋር የሚጣረስ ነው” ሲል ነቅፎታል።

አዋጁ ከፌደራል መንግስት ጋር የሚደረግ የስራ ግንኙነት በወንጀል የሚያስጠይቅ እና ወላጆች በግዳጅ ልጆቻቸው የህወሓትን ሰራዊት እንዲቀላቀሉ የሚያስገድ መሆኑን ኢሰመኮ ገልጿል። በአስር ዘርፎች ተከፋፍሎ የቀረበው ዓመታዊ ሪፖርቱ፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በነበሩ ግጭቶች የሴቶች እና ህጻናት መብቶች መጣሳቸውንም አመልክቷል።  

በግጭቶቹ “በርካታ ሴቶች እና ህጻናት ላይ መጠነ ሰፊና ስልታዊ በሆነ መንገድ በተናጠል እና በቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች መፈጸማቸውን” ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። ጥቃቶቹ “ሰብዓዊ ክብርን ለማዋረድ ሆነ ተብሎ ታቅዶ በግልጽ የበቀል ስሜት የተፈጸሙ” መሆናቸውን የገለጸው የኮሚሽኑ ሪፖርት፤ ጥቃቶቹ በጦርነት አውድ ውስጥ በመፈጸማቸው የጦር ወንጀል ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። 

በመቶ ገጾች የተዘጋጀው ዓመታዊው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቱ፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ላይ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንም ዳስሷል። ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ካለፈው ዓመት ሐምሌ እስከ ግንቦት 2014 ባሉት ጊዜያት፤ 54 የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከቀናት እስከ በርካታ ወራት በእስር ላይ መቆየታቸው በሪፖርቱ ተገልጿል። ከእነዚህ መገናኛ ብዙሃን መካከል 15ቱ በትግራይ ባለስልጣናት በክልሉ የተያዙ መሆናቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

በትግራይ ክልል የታሰሩ የመገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ በክልሉ ስላለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ኮሚሽኑ መረጃ ስላገኘበት መንገድ፤ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጥያቄ ተነስቶ ነበር። ጥያቄው የቀረበላቸው የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል፤ እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ መቀሌ የሚገኘው የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ ላይ እንደነበር ገልጸዋል። 

ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም “ከተወሰኑ ወራቶች በፊት የትግራይ ባለስልጣናት መቀሌ ላይ ያለውን ጽህፈት ቤታችንን ዘግተውብናል። ያ ቢሮ ስለተዘጋ ከዚህ በፊት የነበረንን አይነት ክትትል ለማድረግ እንቅፋት ፈጥሮብናል” ብለዋል። ይሁን እንጂ ኮሚሽኑ አሁንም የርቀት ክትትል በማድረግ መረጃዎችን እንደሚያገኝ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።

ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot

መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
6.1K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 19:07:19 የአርብ የሚድያ ዳሰሳ

አጭበርባሪዎች የግለሰቦች ስልክ ላይ በመደወል እና ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ሽልማት ደርሷችኋል፣ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታችሁን አስተካክሉ እና ሌሎች መሰል መልእክቶችን በማስተላለፍ ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ እንደሆነ ጥቆማዎች ደርሰውኛል ሲል የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በሳምንቱ መጀመሪያ አስታውቋል። ግለሰቦች እንደዚህ ዓይነት መልእክቶች በሚደርሳቸው ወቅት አቅራቢያቸው በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከማረጋገጣቸው በፊት ምንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ በመጠንቀቅ እራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

ቻይና በማህበራዊ ሚዲያ ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች በተወሰኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለመናገር የብቃት ማረጋግጫ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ ደንብ አውጥታለች። የቻይና ብሔራዊ የሬዲዮና ቴሌቪዥን አስተዳደር ረዕቡ እለት ይፋ ያደረገው አዲስ ደንብ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የቀጥታ ስርጭት የሚያቀርቡ ተጽኖ ፈጣሪዎችን የሚመለከት ሲሆን ስለ ህግ፣ ጤና፣ ትምህርትና ፋይናንስ ትንታኔ፣ ማብራሪያና ሃተታ ለማቅረብ በዘርፉ የብቃት ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ያስገድዳል።

ዩትዩብ ቻናሎች የደንበኞቻቸውን ብዛት (subscribers number) እንዳይታይ የሚያደርጉበትን አሰራር በሐምሌ ወር መጨረሻ ከአገልግሎት እንደሚያስወጣ አስታውቋል። ዩትዩብ ይህን እርምጃ የሚወስደው ከታዋቂ ቻናሎች ጋር ተመሳስለው የሚከፈቱ ቻናሎችን ተጠቃሚዎች በቀላሉ እንዲለዩ ለማስቻል መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም የታዋቂ ቻናሎችን ስም አስመስሎ ለመክፈት ተግባር ላይ በሚውሉ ልዩ ሆህያት (special characters) አጠቃቀም ላይ ገደብ መጣሉን ዩቱዩብ አስታውቋል። በቪዲዮች ስር የሚሰጡ አስተያየቶችም ከመጋራታቸው በፊት በቻናሉ አስተናባሪዎች ግምገማ የሚደረግበትን ስርዐት መዘርጋቱንም አስነብቧል።

እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም በዩናይትድ ኪንግደም በተፈጸሙ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ የማጭበርበር ድርጊቶች 1.3 ቢሊዮን ፓውንድ በአታላዮች እጅ መግባቱን ዩኬ ፋይናንስ (UK Finance) የተባለ ተቋም ያወጣው ሪፖርት አስነብቧል። ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ በአታላዮች እጅ የገባው በዓመቱ በተፈጸሙ 195,996 ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ የማጭበርበር ድርጊቶች መሆኑ ተገልጿል። ይህም ቀደም ካለው ዓመት ጋር ሲወዳደር የ27 ፐርሰንት ብልጫ አለው።

ትዊተር ኩባንያ አካውንቶችን እንድዘጋ እንዲሁም ትዊት የተደረጉ ይዘቶችን እንድሰርዝ እያስገደደኝ ነው ሲል የህንድን መንግስት በፍርድ ቤት መክሰሱን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ትዊተር ክስ የመሰረተው የሀገሪቱን ህግ ተላልፈዋል የተባሉ አካውንቶችና ይዘቶች ላይ እርምጃ እንዲወስድ በህንድ መንግስት ከታዘዘ በኋላ ነው። የህንድ መንግስት ከዓመት በፊት ትዊተር የራሱን መመሪያዎች ሳይሆን የሀገሪቱን ህግ መሰረት አድርጎ እንዲሰራ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።

ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot

መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
4.5K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:43:18 ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አደሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አደሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ጥሪ አቀረቡ።

ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ 1443ኛውን የኢድ አል አደሀ/አረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ነገ በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን ታላቁን የኢድ አል አደሀ /የአረፋ በዓል በሰላም ወጥቶ አክብሮ በሰላም እንዲመለስ ጠይቀዋል፡፡

ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ሰላም የሁሉም መሰረት በመሆኑ ሁሉም ለሰላም ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ታላቁ የኢድ አል አደሀ /አረፋ በዓል በፍቅር፣ በአንድነትና በወንድማማችነት እንዲከበር ህዝበ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ አንድነቱንና ወንድማማችነቱን መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡

አገር፣ ቤተሰብ፣ ልማትና እድገት የሚኖረው ሰላም ሲኖር በመሆኑ ለሰላም ከፍ ያለ ዋጋ በመስጠት በሰዎች መካከል የትብብርና ወንድማማችነት መንፈስ ማስፈን ይገባል ብለዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ታላቁን የአረፋ በዓል ሲያከብር አቅመ ደጋሞችን በመጠየቅ፣ የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስ መሆን አለበት ነው ያሉት፡፡

ሀይማኖት የሚኖረው ሀገር ሲኖር መሆኑን በመረዳት በዓሉን ስናከብር በመተዛዘን፣ በመረዳዳትና አንድነትን በማጠናከር መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የሀይማኖት አባቶቹ 1443ኛው የኢድ አል አደሀ/አረፋ በዓል የሰላም የደስታ የብልጽግናና የመከባበር ይሆን ዘንድ የትብብር መንፈስ መጎልበት አለበት ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot

መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
4.2K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:54:14
ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ ማሳሰቢያ

ሰሞኑን የተለቀቀው ቪዲዮ ላይ የተገለፀው የሐዋሳ ዩንቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ተማሪም ተመራቂም አለመሆኑን እናሳውቃለን።

ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot

መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
4.6K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 13:50:13 የአቶ ደመቀ መኮንን ተማጽኖ

ህወሃቶች ድንገት ተለያይተዋል

የጠቅላዩ ንግግር ያስነሳው አቧራ

ተመስገን ያልተፈታበት ምክንያት

አሁን ላይ ሽንዞ አቤ ህይወታቸው አልፏል
===================
01/11/2014 እሮብ
(16:28 min) 7.5 MB
=====================

መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
4.8K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 11:29:12 ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot

መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
4.8K viewsedited  08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ