Get Mystery Box with random crypto!

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አደሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍ የ | Ewunet Media(እውነት)

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አደሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አደሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ጥሪ አቀረቡ።

ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ 1443ኛውን የኢድ አል አደሀ/አረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ነገ በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን ታላቁን የኢድ አል አደሀ /የአረፋ በዓል በሰላም ወጥቶ አክብሮ በሰላም እንዲመለስ ጠይቀዋል፡፡

ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ሰላም የሁሉም መሰረት በመሆኑ ሁሉም ለሰላም ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ታላቁ የኢድ አል አደሀ /አረፋ በዓል በፍቅር፣ በአንድነትና በወንድማማችነት እንዲከበር ህዝበ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ አንድነቱንና ወንድማማችነቱን መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡

አገር፣ ቤተሰብ፣ ልማትና እድገት የሚኖረው ሰላም ሲኖር በመሆኑ ለሰላም ከፍ ያለ ዋጋ በመስጠት በሰዎች መካከል የትብብርና ወንድማማችነት መንፈስ ማስፈን ይገባል ብለዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ታላቁን የአረፋ በዓል ሲያከብር አቅመ ደጋሞችን በመጠየቅ፣ የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስ መሆን አለበት ነው ያሉት፡፡

ሀይማኖት የሚኖረው ሀገር ሲኖር መሆኑን በመረዳት በዓሉን ስናከብር በመተዛዘን፣ በመረዳዳትና አንድነትን በማጠናከር መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የሀይማኖት አባቶቹ 1443ኛው የኢድ አል አደሀ/አረፋ በዓል የሰላም የደስታ የብልጽግናና የመከባበር ይሆን ዘንድ የትብብር መንፈስ መጎልበት አለበት ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot

መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta