Get Mystery Box with random crypto!

Ewunet Media(እውነት)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioewuneta — Ewunet Media(እውነት) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioewuneta — Ewunet Media(እውነት)
የሰርጥ አድራሻ: @ethioewuneta
ምድቦች: ቪዲዮዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.45K
የሰርጥ መግለጫ

🇪🇹እንኳን ወደ እውነት ሚድያ በሰላም መጣችሁ🇪🇹
በውስጥ መስመር ከፈለጉን @Ewuneta_bot
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ
👇
https://youtube.com/channel/UCjiq4hREIdyVsnPPKfSOkcg

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-15 20:19:08 ሰበር የክልልነት ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ጉዳዩን የአመጽና የሁከት መነሻ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ

የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ መንግሥት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በተለያዩ ጊዜያት የሚነሱ የክልልነት ጥያቄዎችን በሀገሪቱ ሕግና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየሠራ ይገኛል፡፡

ነገር ግን አንዳንድ አካላት ይህንን ሂደት በሚቃረን መንገድ ሕጋዊ ጥያቄዎችን ሽፋን በማድረግ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር በህቡዕ ዝግጅት ማድረጋቸውን የጋራ ግብረ ኃይሉ ባደረገው ክትትል ስለተደረሰበት ተገቢው እርምጃ ይወስዳል፡፡

መግለጫው እንዳብራራው፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በስሩ የሚገኙ ዞኖችን በአዲስ መልክ ለማዋቀር እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ጌዲኦም በአዲስ መልክ ከሚዋቀሩ ዞኖች አንዱ ሲሆን፤ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በተጨባጭ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሰሞኑን የማወያያ ሰነዶች ተዘጋጅተው የዞኑ ነዋሪ እየመከረበት ይገኛል፡፡

ይሁንና የጌዲኦ ዞን የክልልነት ጥያቄ መፍትሔ የማይሰጠው ከሆን ጥያቄያችንን በኃይል እናስፈጽማለን የሚሉ አካላት በህቡዕ ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በተጨባጭ መረጃዎች አረጋግጧል፡፡

በህቡዕ የተደራጁት አካላት የጥፋት እቅዶቻቸውን ለማሳካት ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች በመክፈት የተዛቡና የፈጠራ መረጃዎችን እያሰራጩ መሆኑን ያመለከተው የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለጫ፤ ማኅበረሰቡንም በተሳሳቱ መረጃዎች ለማደናገር እየሞከሩ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

እነዚህ አካላት ያደራጇቸው ግለሠቦችና ቡድኖች ቤት ለቤት ጭምር እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ እያደረጉ እንደሚገኙ ይህም በደኅንነትና በጸጥታ አካላት እንደተደረሰበት አመልክቷል፡፡

የጋራ ግብረ ኃይሉ ለዚህ እኩይ ዓላማ የተደራጁና የተሰለፉ ግለሠቦችንና ቡድኖችን በደኅንነትና በጸጥታ መዋቅሩ አማካኝነት ለይቶ ክትትል እያደረገባቸው መሆኑን በማስገንዘብ፤ ከጥፋት ተልዕኳቸውም እንዲቆጠቡ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

ይህን ተላልፈው በሚገኙ ላይም ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ያስጠነቅቃል፡፡

አብዛኛው የዞኑ ኅብረተሰብ የጥፋት ተልዕኮ ያነገቡ አካላት ህቡዕ እንቅስቃሴ ተገቢ አለመሆኑን በማመን ለጸጥታና ደኅንነት አካላት ጥቆማ በመስጠት የሁከትና ብጥብጥ ተልዕኮው እንዲከሽፍ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የጠቆመው የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለጫው፤ በቀጣይም ከእንደዚህ አይነት የጥፋት ሴራ እራሱን በማቀብ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት ለመንግሥት አካላት መረጃ በመስጠት የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠይቋል፡፡

የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል

ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
2.0K views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:13:26 ሰበር የኮንዶሚኒየም እጣ

በአዲስ አበባ ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውደቅ ተደረገ

ሐምሌ 6፣ 2014 (እሮብ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ዕጣው የተሰረዘውም የከተማ አስተዳደሩ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱ በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት መኖሩ በመረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 01 ቀን 2014 በወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር ድርጊት በመከሰቱ ሁኔታውን እያጣራ እንደሚገኝ እና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
4.2K viewsedited  14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:29:55
አዲሱ ታሪፍ : የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ሐምሌ 7/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የተሻሻለ ታሪፍ
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
4.1K viewsedited  11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:09:33 የባልደራስ ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ!!

በሀገረ--አሜሪካ ለሁለት ወራት ቆይታ ያደረጉት የባለደራስ ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ፣ ዛሬ፣ ሐምሌ 6 2014 ወደ ኢትዮጰያ ተመልሰዋል።

ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ሲደርሱ የድርጅቱ አመራር አባላት አቶ ነብዩ ውብሸት እና ቀለብ ስዩም(አስቴር) ተቀብለዋቸዋል።

በአሜሪካ የነበራቸው ቆይታ በእጅጉ ሰኬት እንደነበር የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ነገ ሐምሌ 7 2014 ሥራ እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
3.9K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:23:41 በአዲስ አበባ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ዳዊት የሺጥላ እንዳሉት በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የአዉቶብስም፣ የታክሲም የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል፡፡

የማሻሻያ ዋጋዉም የታክሲ ትንሹ የ 50 ሳንቲም ጭማሪ ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ የ2 ብር ጭማሪ ለማድረግ መዘጋጀቱን ቢሮው አስታውቋል፡፡

በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ ከተደረገ ወዲህ በተለይም ታክሲዎች በራሳቸዉ ታሪፍ እየጨመሩ ከተሳፋሪዎች ጋር አላስፈላጊ እስጠገባ ዉስጥ ሲገቡ ይስተዋላል፡፡
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
3.7K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:18:03 ወለጋ ከሞት የተረፉት ጭንቅ

መንግስት የደርድሩን ስራ ጀመረው

በኮንደሚኒየሙ ተያዙ የተባሉት ስራ ላይ ናቸው

ግብጽን ያስደነገጠው
===================
06/11/2014 እሮብ
(16:24 min) 7.5 MB
=====================

መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
3.5K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:50:01 ኮሚሽነር #ምትኩ #ካሳ በሙስና ተጠርጥረው ተያዙ

  የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ኮሚሽነሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው ዛሬ በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በፌዴራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ለኢቲቪ እንዳሉት ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት "ኤልሻዳይ" ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በእንጅባራ እና በመሳሰሉ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።(EBC)
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
3.5K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 09:28:35 ህወሓት፤ ትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት የተፈረመው ስምምነት “አልገባኝም” ብሏል

የኢትዮጵያ መንግስት በህሓት ኃይሎች እና በፌደራል መንግስት መካከል በተፈጠረ ግጭት የወደመውን መሰረተ ልማት መልሶ ለመገንባት ከተባበሩት መንግስታት ጋር የሶስተኛ ወገን ትግበራ ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በኩል መንግስትን በመወከል ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ሲሆኑ በተመድ የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ (ዩኤንኦፒኤስ) በኩል ደግሞ ወ/ሮ ወርቅነሽ መኮንን ናቸው፡፡

መንግስት ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይደርስ አስተጓጉሏል ሲል ህወሓትን ከሰሰ

የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "ብሄራዊ የማገገሚያ መርሃ ግብሩ" የመሰረተ ልማት መልሶ የመገንባት፣ የአስፈላጊ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ለማሻሻል እና የጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ለመርዳት ያለመ ነው ብሏል፡፡

"በትግራይ ያሉ ሁኔታዎች እስኪሻሻሉ እና መንግስት ፕሮጀክቱን በራሱ መዋቅር ለማስፈጸም እስኪችል ድረስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ ፕሮጀክቱን በትግራይ ተግባራዊ ያደርጋል" ሲልም መግለጫው አክሏል።

ከመንግስት ጋር ስምምነቱን የተፈራረመው የተመድ የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ (ዩኤንኦፒኤስ)፤ ጦርነት በተጎዳው የሰሜኑ ክፍል እና ባብዛኛው በህወሐት ስር በሚገኘው የትግራይ ክልል የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ እንደሚገነባ መግለጹም ሚኒስተሩ አስታውቋል፡፡

ከጾታዊ ጥቃት የተረፉ ሰዎችን የሚረዳበት ሌላው የፕሮግራሙ ክፍል በሌላ አካል የሚተገበር ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በጉዳዩ ላይ ድርድር እየተካሄደ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

መንግስት በጦርነት የወደመው የትግራይ ክልልን መሰረተ ልማት መልሶ ለመገንባት ይህን ይበል እንጂ፤ ጉዳዩ በህወሐት በኩል ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም፡፡

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ፤ “ይህ ነገር ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት እንደሚሰራ አልገባኝም” ብለዋል፡፡

“መልስ ለማግኘት እየጮህኩ ነው!” ሲሉም ስምምነቱ ያልጠበቁትና የማይቀበሉት በሚመስል መልኩ ገልጸውታል፡፡

እንደረፈረንጆቹ በህዳር 2020 በመንግስት እና በህወሓት መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ብዙ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ አጋሮች ቀደም ሲል ሲሰጡት የነበረን እርዳታ ቀንሰው እንደነበረ ይታወቃል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች እርዳታ ጭነው ትግራይ መግባታቸውን ህወሓት አስታወቀ

መንግስት በሚያዝያ ወር የእርዳታ ወደ ትግራይ የመላክ ሂደት እንደገና በመፍቀድ እርዳታ የጫኑ መኪናዎች ወደ ክልሉ እንዲመለሱ መፍቀዱም ተከትሎ ወደ ትግራይ ሚገባው እርዳታ በእጅጉ የተሻሻለ መምጣ ይታወቃል።

ትግራይ አሁንም እንደ መብራት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እና ባንክ ያሉ አስፈላጊ አገልግሎቶችን የሌሉበት እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ የሚገኙበት ክልል እንደሆነ የተመድ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ይህንን ከግምት ውስጥ ያስገባው የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በግጭት እና በአሰቃቂ ድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 715 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እና ብድር ለመስጠት ባለፈው ወር መስማማቱ አይዘነጋም።
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
3.8K views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 14:19:08 ነገ መብራት ይጠፋል

የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኤሌክትሪክ አቅርቦት

ረቡዕ ሀምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል በጆሞ 2 ኮንደሚኒየም፣ በየስ ውሃ፣ በአለም ገና ማርስ ብስኩት እና አካባቢዎቻቸው ኤሌክትሪክ ይቋረጣል፡፡

በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot

መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
4.5K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 13:20:51 በደሴ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

ሐምሌ 5፣ 2014 (ማክሰኞ)

በደሴ ከተማ በተለምዶ ሳላይሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በደሴ ከተማ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር አለባቸው መለሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ ዛሬ 5 ሰዓት ከ30 ላይ ሳላይሽ በግ ተራ አካባቢ የቆራሌ ዕቃ በሚራገፍበት ሰዓት ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ፈንድቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

በፍንዳታው በግ ሲገዙ የነበሩ ሰዎችና የቀን ሠራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን÷ ተጎጂዎችም ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

እስከ አሁን የሞተ ሰው እንደሌለ ጣቢያችን ያረጋገጠ ሲሆን፥ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ፖሊስ መረጃ እሰጣለሁ ብሏል፡፡

በከድር መሀመድ
=====================
YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================
@EthioEwuneta @EthioEwuneta
4.5K views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ