Get Mystery Box with random crypto!

የ20 አመቱን ጥቁር አሜሪካዊ የተኮሰችበት ፖሊስ በግድያ ወንጀል ተከሰሰች | HabeshaNet.

የ20 አመቱን ጥቁር አሜሪካዊ የተኮሰችበት ፖሊስ በግድያ ወንጀል ተከሰሰች በሚኒሶታ አንድ ጥቁር አሽከርካሪን በጥይት የገደለችው ነጭ የቀድሞ የፖሊስ መኮንን በሁለተኛ ደረጃ የመግደል ወንጀል ክስ እንደተመሠረተባት አቃቤ ህግ ገለጸ፡፡

ኪም ፖተር በቁጥጥር ስር የዋለች ቢሆንም በኋላ ግን በ 100,000 ዶላር ዋስ ተለቃለች፡፡

ፖተር በስህተት ማደንዘዣ መስሏት ሽጉጧን በመምዘዝ ዳውንት ራይት ላይ መተኮሷን ፖሊስ ገለጿል፡፡

የራይት ቤተሰብ ጠበቃ ቤን ክራምፕ በበኩላቸው ግድያው "ሆን ተብሎ እና ህገ-ወጥ የኃይል እርምጃ በመጠቀም የተፈጸመ ነው" ብለዋል፡፡

ክስተቱን ተከትሎ ኪም ፖተርም እና የአከባቢው የፖሊስ አዛዥ ቲም ጋኖን ሥራቸውን ለቀዋል፡፡