Get Mystery Box with random crypto!

ግማሽ ያህል የምርጫ ጣቢያዎች አልተከፈቱም፣ በአፋርና በሶማሌ ምዝገባ አልተጀመረም | HabeshaNet.

ግማሽ ያህል የምርጫ ጣቢያዎች አልተከፈቱም፣ በአፋርና በሶማሌ ምዝገባ አልተጀመረም ሊካሄድ ሰባት ሳምንት ብቻ በቀረው ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ የመራጮች ምዝገባ ይካሄድባቸዋል ከተባሉት የምርጫ ጣቢያዎች ወደ ግማሽ የሚጠጉት አለመከፈታቸውን የምርጫ ቦርድ ገለጸ።

የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረ ከሦስት ሳምንት በላይ ሲሆነው በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ተከፍተው ድምጽ ሰጪዎችን ይመዘግባሉ ተብለው ከታቀዱት 50 ሺህ ያህል የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ምዝገባ እያካሄዱ ያሉት 25 ሺህ 151ዱ ሲሆኑ ከ24 ሺህ በላይ የሚሆኑት ግን ሥራ አልጀመሩም።