Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር የሕዳሴ ውዝግብን ለመፍታት ለአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አደረጉ | HabeshaNet.

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር የሕዳሴ ውዝግብን ለመፍታት ለአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አደረጉ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ለመፍታት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲደረግ ለግብጽና ለኢትዮጵያ መሪዎች ጥሪ አደረጉ።

ለዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር በኮንጎዋ መዲና ኪንሻሳ ውጤታማ አለመሆኑን ተከትሎ ይህ ውይይት የመጨረሻ ሙከራ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

በኪንሻሳ ላይ ሱዳን እና ግብጽ የሕዳሴ ግድብ ድርድር ታዛቢዎችን ሚና ለመቀየርና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት በአደራዳሪነት እንዲገቡ ሃሳብ ቢያቀርቡም ኢትዮጵያ አልተቀበለችውም።

ኢትዮጵያ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር እንዲሆን ትፈልጋለች።

ይህንን የኢትዮጵያ ሃሳብም ሰሞኑን ሩሲያ እንደምትደግፈው የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ሩሲያ የሕዳሴ ግድብ ውዝግብ በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር እንዲፈታ ፍላጎት አላት በማለት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን ንግግር ያደረጉት በካይሮዋ መዲና ከግብጹ አቻቸው ሳሜ ሽኩሪ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሆነ ተዘግቧል።