Get Mystery Box with random crypto!

ችሎት! እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዳኛ ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡ የፌደራል የ | HabeshaNet.

ችሎት!

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዳኛ ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እነ አቶ ጃዋር ባቀረቡት አቤቱታ ላይ መርምሮ ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚህም አቤቱታው በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ይህን ተከትሎም ችሎቱ ከዚህ በፊት በነበረው ዳኛ የሚታይ ይሆናል ተብሏል፡፡

በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ መዝገብ አስራ አራት (14) ሰዎች ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ዳዊት አብደታ የተባለው ተጠርጣሪ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠርጥሮ ችሎት አልቀረበም፡፡

Via Tarik Adugna (FBC)