Get Mystery Box with random crypto!

ኦነግ 6 አመራሮቹን ማገዱን አስታውቋል! የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ አ | HabeshaNet.

ኦነግ 6 አመራሮቹን ማገዱን አስታውቋል!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ አቶ አራርሶ ቢቂላ፣ አቶ ቶሌራ አደባና አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ ስድስት ከፍተኛ አመራሮቹን ለጊዜው ማገዱን አስታውቋል፡፡

በእግዱ ተካተዋል የተባሉ አመራሮች ነሐሴ 4 ቀን የድርጅቱ አመራሮች ጋዜጣዊ መግለጫ በሂልተን ሆቴል መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳዎድ ኢብሳ በበኩላቸው የተሰጠው መግለጫ የፓርቲያቸው እውቅና እንደሌለውና እርሳቸውም ስለ መግለጫው መረጃ እንደሌላቸው #ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ከዚህም አስቀድሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ስብሰባ በኀላ በተነሱ ጉዳዮችና ልዩነቶች ላይ የፓርቲው የህግና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲያጣራ መወሰኑን አመራሮቹ ገልጸው ነበር።