2020-04-11 19:51:40
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ ተግባራት
1• ማንኛውም ሐይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ከአራት ሰው በላይ የሚገኝባቸው እድርን፣ደቦን፣እቁብንናሌሎች ባህላዊ ስብሰባዎችን ማካሄድ ተከልክሏል። ነገር ግን ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ሁኔታዎች ሲኖሩ እየታዩ ሊፈቀዱይችላሉ።
2• በመጨባበጥ ሠላምታ መለዋወጥ ተከልክሏል።
3• ተማሪዎችና መምህራን በአካል መገናኘት ተከልክሏል።
4• ታራሚዎችተገቢው ጥንቃቄ ተደርጎ ከጠበቆቻቸው የሚገናኙ ሲሆን፤ ታራሚዎችን መጠየቅ ተከልክሏል።
5• በፖሊስ ቁጥጥር ስር ላሉ እስረኞች ስንቅ ከማቀበልውጪ መገናኘትተከልክሏል።
6• የአገሪቱ ድንበር ከካርጎ፣ከደረቅና ፈሳሽ የጭነት ተሽከርካሪዎች ውጪ ሌሎች ለሌሎች ዝግ ሆኗል።
7• የቤት ተከራዮችን ማስለቀቅ ወይም ኪራይ መጨመር ተከልክሏል።
8• ሠራተኞችን መቀነስና የሥራ ቅጥር ውልን ማቋረጥ ተከልክሏል።
9• ስፖርታዊ ጨዋታዎችና የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች ክልከላ ተጥሎባቸዋል።
10• የአገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች ካላቸው መቀመጫ ከ50 በመቶ በላይ ተሳፋሪ መጫን ተከልክሏል።
11.ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ሃሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት፣ማጋነን እና ማቃለል የተከለከለ ነው
12ወረርሽኙን ለመከላከል መንግስት ሊጠቀምባቸው የፈለጋቸውን ቤቶች፣ሆቴሎች፣መኪኖች እና ሌሎች አጋዥ ነገሮችን ባለቤቶቹ እንዲሰጡ በተጠየቁበት ሰዓት የመተባበር ግዴታ አለባቸው
13 ህዝብ በብዛት የሚገለገልባቸው. ቦታዎች እንደ ባንክ፣የንግድ ቦታ እና የመሳሰሉ ቦታዎች ርቀትን ሳይጠብቁ ቢያንስ 2ሜትር ሳይርቁ መቀመጥም ሆነ መቆም የተከለከለ ነው
930 views16:51