Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና !!!

የቴሌግራም ቻናል አርማ elasunews — ሰበር ዜና !!!
የቴሌግራም ቻናል አርማ elasunews — ሰበር ዜና !!!
የሰርጥ አድራሻ: @elasunews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.06K
የሰርጥ መግለጫ

get more subscriber

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 18:06:00 በአዲሱ የሥርዓተ-ትምህርት እንደ አዲስ የሚጨመሩና የሚቀነሱ የትምህርት አይነቶች ይኖራሉ ተባለ

በ2016 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ በሚገባው በአዲሱ የሥርዓተ-ትምህርት በ7ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ላይ ከዚህ በፊት ሦስቱ ሳይንሶች ተብለው ይሰጡ የነበሩት (ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባዮሎጂ) አሁን አጠቃላይ ሳይንስ ተብለው በአንድ ላይ የሚሰጡ ሲሆን የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል የኢኮኖሚክስ ትምህርት ደግሞ “ፐርፎርም ኤንድ ቪዥዋል አርት” በሚል መተካቱን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል በድጋሚ ከሚሰጡ የትምህርት አይነቶች በተጨማሪ ሥራና ቴክኒክ ላይ የሚያተኩሩ የማኑፋክቸሪንግና ኮንስትራክሽን የትምህርት አይነቶች በየደረጃው ተለይተው መጨመራቸውን ለኤዜአ ገልጸዋል።
435 views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:51:16 የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል እንዲወጡ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጠየቁ

የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል የጀመሩትን ውጊያ አቁመው ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱና በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ኃይሎችም ክልሉን ለቀቅው እንዲወጡ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጠይቀዋል።

ቪኪ ፎርድ ይህን ያሉት ህወሓትና የኢትዮጵያ መንግስት ዳግም ወደ ግጭት መመለሳቸውን ተከትሎ ዛሬ ሐሙስ ባወጡት መግለጫ ነው። በሁለቱ ኃይሎች እንደገና ወደ ግጭት መግባባት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን የማጣት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ethiopian insider
574 views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:01:09 "ህወሓት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሎበታል" - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ህወሓት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው።

አሁን እንደሚታየው አሸባሪውን ህወሓት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል። ምክንያቱም:-

1. የሽብር ቡድኑ ሰላማችንን እንዳያደፈርስና ሀገራችንን እንዳያፈርስ መከላከል ስለሚገባ፤

2. ሕወሐት ወደ ትግራይ የሚላከውን ርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ እንዳይደርስ፣ በተቃራኒው ርዳታው ለጦርነት እንዲውል እያደረገ በመሆኑ መንግሥት ርዳታው ለተረጂው ሕዝብ
እንዲደርስና ትግራይ ውስጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕዝቡን ከችግር የመከላከል ግዴታ ስላለበት፤

3. ሕወሐት በእኩይ ተግባሩ ሕዝብን በረሃብ ለመቅጣት ዐቅዶ ተደጋጋሚ ጦርነት የሚከፍተው በክረምት የግብርና ወቅት በመሆኑ መንግሥት ወረራውን እየተከላከለ ያለው ሕዝብን ከረሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ጭምር ነው።

ይሁንና በሕወሐት የሽብር ቡድን እየደረሰሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግሥት ለሰላማዊ አማራጭ ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ፣ አሸባሪውን ሕወሐት መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ
በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።

በመሆኑም ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገራችንን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይላችን በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል።

ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

አዲስ አበባ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
639 views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:00:09 በሩሲያ ያዘጋጀችው ግዙፉ “ቮስቶክ 2022” የጦር ልምምድ መካሄድ ጀመረ

በሩያ ግዛት በሚካሄደው የጦር ልምምዱ ላይ ሩሲያ፣ ቻይናና ህንድን ጨምሮ የ14 ሀገራት ወታደሮች ይሳተፋሉ። ቮስቶክ 2022 ልምምድ ላይ 50 ሺህ ወታደሮች እና የተለያዩ ጦር መሳሪያዎች ይሳተፋሉ።
https://am.al-ain.com/article/vostok-2022-military-drills-kick-off-in-moscow
593 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:58:51 "አማራ ሌላ ሀይል ነፃ ያወጣኛል የሚለውን መርሳት አለበት። እስከ መቼ ነው በህወሃት አናሳ ቡድን መጫዎቻ የሚሆነው?" - ጀ/ል ተፈራ ማሞ

ለአማራ መደፈር ችግሩ አመራር ማጣት ነው። ለዚህ ተጠያቂው ግን ራሱ የአማራ ህዝብ ነው። አማራ 30 አመት ሙሉ ወደ ላይ የሚያንጋጥጥ አመራር ተሸክሞ ነፃነት ይገኛል ማለት ዘበት ነው። ከእነዚህ አመራሮች መፍትሔ የሚፈልግ፣ እሱ ለባርነት የተዘጋጀ ህዝብ ነው። ለምንድነው ህወሃት የአማራን መሬት የሚወሩት? ለምንድነው ኤርትራ መሬት የማይገቡት?

እስከ መቼ ነው አማራ የተደራጀ የህወሃት አናሳ ቡድን መጫዎቻ የሚሆነው? በችግር ጊዜ ቀድሞ የፈረጠጠ አመራር ተመልሶ ልምራህ ሲል የሚቀበል አማራ፣ መቼም ነፃ አይወጣም። ልጆችህን ጠብቅ፣ አመራር ፍጠር። ዛሬ ፋኖ ሲታሰር፣ የፋኖ አመራሮች ሲሳደዱ ዝም ካልክ፣ ነገ የአማራ አመራር ከየት ይወጣል?

አማራ ሌላ ሀይል ነፃ ያወጣኛል የሚለውን መርሳት አለበት። ራሱ ነው ለራሱ መቆም ያለበት። ሚሊሻውም፣ ፋኖውም፣ ልዩ ሀይሉም በአኔድ ዕዝ መሆን አለበት። ጠላት የታጠቀውን መታጠቅ አለብን። የአማራ ህዝብ አመራሩን ለምን በተደራጀ የህወሃት አናሳ ቡድን አስደፈርከኝ ብሎ መጠየቅ አለበት። ከዚህ ውጭ አማራ እድሜ ልኩን ሲደማ ይኖራል።

አማራ ክልል ለሚፈጠር ችግር ፌደራል መንግስቱን blame ማድረግ አያዋጣም።

(ጀ/ል ተፈራ ማሞ - ለethio251 የተናገረው)
596 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:57:12 ሰበር ዜና

የኤየርትራ ጦር ዛሬ ጠዋት በትግራይ ሰሜናዊ #አዲያቦ አካባቢ መጠነ ሰፊ ጥቃት ፈጽሟል። የኤርትራ ጦር ወደ ጥቃት የገባው ህወሃት ባደረገው ትንኮሳ መሆኑ እየገለፀች ትገኛለች
571 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:35:18 #ነዳጅ

የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል።

ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በመስከረም ወር 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
754 views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:43:28 ሰበር መረጃ

በሱዳን ካርቱም ኤርፖርት ጎዳና አሁን በዚህ ሰአት በተቃውሞ እየተናወጠ ይገኛል።

የአልቡርሃን መንግስት ዛሬም በሱዳናውያን አብዮተኞች ከፍተኛ ተቃውሞ እና አመጽ ገጥሞታል።
በተለይ አሁን ሀገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ችግር በማየት ጠላቶቻችን ሴራቸውን እየጎነጎኑ ቢሆንም አሳቱ እራሳቸው ቤት መንደድ ጀምሯል

#EthiopianDailyNews
778 views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:35:22 ሁመራ ከተማ በተረጋጋ ሁኔታ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ገለፁ

ዶቼ ቬለ DW ዛሬ ቀን ላይ ያነጋገራቸው አንድ የከተማዋ ነዋሪ በህወሓት እና በኢትዮጵያ በመከላከያ ሰራዊት መካከል ዉጊያ ካገረሸ ወዲህ በአካባቢው በረከት እና ሸረሪና በሚባል ቦታ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።እሳቸው የሚኖሩበት ሁመራ ከተማ ግን በተረጋጋ ሁኔታ ህይወት በተለመደው ሁኔታ እየቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።

ነዋሪው እንደሚሉት ጠዋት ላይ የመሳሪያ ድምጽ ከሩቅ ይሰማ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን ምንም ነገር እንደሌለ ገልፀዋል።

በአካባቢው ውጊያው የተደጀመረው ሌሊት ሲሆን፤ እሳቸው ግን የሰሙት ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ነው። የእሳቸው የእርሻ ቦታ በረከት አካባቢ ሸረሪና የሚባል ቦታ መሆኑንም ተናግረዋል ።

ነዋሪው አያይዘውም ህብረተሰቡ ወደ ውጊያ ቦታ ለመሄድ ነቅሎ ነው የወጣው መከላከያ በቂ ነው ያለው ተብሎ ከምድራዊ ከምትባል ቦታ ነው የተመለስ ነው።

ማህበረሰቡ ለሰራዊቱ የተለያዩ ምግብ እና ውሃ ጭኖ እያደረሰ መሆኑንም ነዋሪው በስልክ ገልፀዋል።

ያም ሆኖ በሚኖሩበት በሁመራ ከተማ «ህይወት እንደ ቀጠለ ነው። ሁሉ ነገር እንደበፊቱ ነው።» ብለዋል ነዋሪው
ምንጭ፡- ዶቼ ቬለ DW
754 views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:34:21 በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን "በስቃይ ውስጥ ነው ያለነው የመኖሪያ ፈቃድ አውጡ በሚል ሰበብ እስር ቤት እያጎሩን ነው፡፡ እባካችሁ ድምጽ ሁኑን ፣ ሃገራችን እንድንገባ ይመቻችልን እየተሰቃየን ነው፡፡ ኤምባሲያችን ሊረዳን አልቻለም!"

በዉስጥ የደረሰን

-
716 views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ