Get Mystery Box with random crypto!

#Update በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

#Update

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ስራ ተጀመረ

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አንፈተንም በሚል  በዋናው ግቢ በዉስጥ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

ከዩኒቨሲቲውም ሆነ የሚመለከታቸዉ የፀጥታ ተቋማት  እውቅና ውጪ ባልተፈቀደ ሁኔታ ሰኔ  03 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በዩኒቨርሲቲዉ ሆነ በሰዉ ላይ ሊደርስ የሚችል ጉዳት ለማስቀረት የፀጥታ ኃይሉ ህግ የማስከበር ተግባሩን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን  በጥቂት የማህበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ችግር እንዳለና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መስተጓጎል እንዳለ በማስመሰል የሚሰራጩ መረጃዎች  ሀሰተኛና ተቀባይነት የሌላቸዉ ናቸው ተብሏል።በመሆኑም የተማሪ ወላጆችና መላው ህብረተሰብ  መረዳት ያለባቸው ከተፈጠረው አነስተኛ ግጭት ውጪ በተማሪዎች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት የሌለ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy