Get Mystery Box with random crypto!

15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ታገዱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ታገዱ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ማገዱን አሰታወቀ።

ከጥቅምት 14/2015 እስከ ታህሳስ 30/ 2015 ዓ.ም ድረስ 15 ኤጀንሲዎች ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምንም አይነት ሪፖርት አለማድረጋቸውን ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ በላይ የዜጎችን መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡

በህግ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዜጎችን ለሥራ ስምምነት ወደተደረሰባቸው መዳረሻ ሀገራት ለመላክ ፍቃድ በመውሰድ ወደ ሥራ እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

ፍቃድ ወስደው የሚሰሩ የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችም በአዋጅ ቁጥር 923/08 እና በማስፈፀሚያ መመሪያ መሰረት ሊያሟሉ የሚገባቸውን አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸውን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 923/08 መሰረት ድርጊቱ የሥራ ፈቃድ ስረዛ የሚያስከትል መሆኑን ጠቅሶ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ አልቻሉም፡፡

ስለሆነም ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎ ከድርጊታቸው መማር እንዲችሉ ከግንቦት 11ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለመጨረሻ ጊዜ ለሦስት ወራት ታግደዋል ብሏል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy