Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል? በርካታ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከፈተና ቀን ጋ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል?

በርካታ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከፈተና ቀን ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን እየላኩልን ይገኛሉ።

ፈተናው በመጪው ሐምሌ ይሰጣል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ እስከአሁን የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ትክክለኛና ቁርጥ ያለ ቀን ይፋ አልተደረገም።

የፈተናው ቀን ይፋ የሚደረገው በማዕከል በኩል ከትምህርት ሚኒስቴር / ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሲሆን ይህም ለህዝብ በይፋ በመገናኛ ብዙኃን ይነገራል።

በመሆኑም ተማሪዎች ለፈተናው ጥቂት ጊዜ የቀረው መሆኑን በመገንዘብ ዝግጅት ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ እንላለልን።

በሌላ በኩል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የተፈታኞች የበይነ መረብ ምዝገባ /online Registration/ አፈጻጸም ግምግማ ባለፈው ሳምንት አካሂዷል፡፡

በተጨማሪም በተዘጋጀው የፈተና አስተዳደር መመሪያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን የበይነ መረብ ምዝገባው ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ የተደረገበትና ስኬትማ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ የፈተና አስተዳደር መመሪያ ለተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከውይይቱ የተገኙ ሀሳቦችም በሰነዱ ተካተው በድጋሚ ለውይይት እንደሚቀርብና ሲጸድቅ ተግባራዊ እንደሚሆን ተነግሯል።

የመውጫ ፈተና

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በተመሳሳይ በማዕከል ተዘጋጅቶ በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከዚህ ቀደም በመጪው ሐምሌ ይሰጣል ተብሎ በመንግሥት ኃላፊዎች መገለጹ ይታወሳል።

ይህም ፈተና የሚሰጥበትን ቀን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ዝርዝር መረጃ የሚያወጣ በመሆኑ፤ እስከዛው ዝግጅታችሁን አጠናክሩ።

@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only