Get Mystery Box with random crypto!

#MoE 'በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 49 ሺ ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ዘመቻ ከአንድ ወር በኋላ ይ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

#MoE

"በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 49 ሺ ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ዘመቻ ከአንድ ወር በኋላ ይጀመራል" - የትምህርት ሚኒስቴር፡፡

የትምህርት ምዘና ጥናት ውጤቶችን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ አውደ ጥናት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት ጥራት ውጤት ምዘና እንዲሁም የ4ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት ምዘና ጥናት ይፋ ሆኗል።

በናሙና በተወሰዱ ትምህርት ቤቶች በተደረገው ምዘና ዝቅተኛ ውጤት መገኘቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሥርዓቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ይዞ መቀጠል አይቻልም ያሉት ሚኒስትሩ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ባሉት 49 ሺ ትምህርት ቤቶች የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ዘመቻ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር ይፋ አድርገዋል፡፡ በዘመቻው ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የቀድሞ ተማሪዎች እና ማህበረሰቡ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አመልክተዋል፡፡

ርዕሰ መምህራንን ለማብቃት የሚያስችል ማዕከል እየተቋቋመ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ #EPA   #MoE
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy