Get Mystery Box with random crypto!

ለፈገግታ የኔልሰን ማንዴላ የዪኒቨርስቲ ሂወት ታሪክ በElshio_acadame እና Ethio_S | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

ለፈገግታ የኔልሰን ማንዴላ የዪኒቨርስቲ ሂወት ታሪክ በElshio_acadame እና Ethio_Students_only በመተባበር
__
ኔልሰን ማንዴላ በዪኒቨርስቲ ውስጥ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው፡፡ ስሙም ፒተር ይባል ነበር፡፡
አንድ ቀን ማንዴላ በአንድ ምግብ ቤት
ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ፕ/ሮ ፒተር በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ ። ዘረኛው
ፒተርም ''አቶ ማንዴላ! አሳማ ና 'ርግብ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" ሲላቸው ብልሁ
ማንዴላ "አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብለዋቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ ።
በዚህ የተናደዱት ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣ ያስባል አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ
"ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳወች ብታገኝ በአንደኛው ቦርሳ 'ገንዘብ' በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ 'ጥበብ' ቢኖረው የትኛውን ትወስዳለህ''? ብሎ ጠየቀው ማንዴላም "ገንዘብ እወስዳለሁ"…ብሎ መለሰለት ፡፡ ፕሮፌሰሩ በድል አድራጊነት "አንተ ሞኝ እኔ አንተን ቢያረገኝ 'ጥበብ' ያለበትን ቦርሳ "ምወስደው ነበር አለው" ሲለው ማንዴላ ፈገግ እያለ " ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው "አለው ።
በዚሁሉ ነገገር የተበሳጨው ፕ/ሮ ፒተር የማንዴላን ፈተና ወረቀት ላይ "ደደብ" የሚል ፁሁፍ ይፅፋል። ሌሎች ተማሪወች የታረመላቸውን
የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ "ደደብ" የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አዩና ተገረመ ወደ ፕ/ሮ ፒተር ሄዶ
"ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥከ ው ውጤቴን እረስተኸዋል" ብሎት እርፍ ፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy