Get Mystery Box with random crypto!

#WachemoUniversity በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ቅዳሜ ዕለት ተፈጥሮ የነበረው 'መጠነኛ አለመረጋ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

#WachemoUniversity

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ቅዳሜ ዕለት ተፈጥሮ የነበረው "መጠነኛ አለመረጋጋት" ወዲያውኑ መፈታቱን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በአንድ ተማሪ ላይ አካላዊ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ፤ በግቢው ውስጥ ቅዳሜ ቀን 11:00 አካባቢ "መጠነኛ አለመረጋጋት" ተፈጥሮ እንደነበር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሁለት ተማሪዎች ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እንዲያገኙ ተደርጎ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ መደረጉን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡

የተፈጠረው መጠነኛ አለመረጋጋትም ወዲያውኑ እንደተፈታ ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል፡፡

ከአለመረጋገቱ ጋር ባልተያያዘ በተቋሙ ለሁለት ቀናት ተቋርጦ የነበረው የአዲስ መስመር የውሃ አቅርቦት በዕለቱ ጠዋት (ቅዳሜ ሚያዝያ 28/2015 ዓ.ም) በድጋሜ ሥራ መጀመሩን ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል፡፡

ተቋሙ በቂ የውሃ አቅርቦት (ነባር እና አዲስ) የውሃ መስመር እንዳለው የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት ከውሃ አቅርቦት ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy